ፓርቲዎቹ መንግሥታዊ ሽብር እና የጦር ወንጀል የሆነውን የድሮን ጥቃት፣ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ፣ የፖለቲካ ልኂቃን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ምሑራን፣ የመገናኛ ብዙኅንና የሰብዓዊ መብት ተማጋቾች እንዲያወግዙት ጥሪ አቀረቡ‼️
==========
እናት ፓርቲ፣ መኢአድ፣ ኢሕአፓ እና አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ፣ በቅርቡ በአማራ ክልል፣ ምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ፣ አነገሽ በተባለ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሐሙስ ገበያ በተባለ ሥፍራ የካቲት 13 ቀን የተፈጸመው የድሮን ጥቃት "የመንግሥታዊ ሽብር ማሳያ" ነው በማለት ዛሬ በጋራ ባወጡት መግለጫ አውግዘዋል።
ፓርቲዎቹ፣ በጥቃቱ ታዳጊ ሕጻናትን ጨምሮ 16 ንጹሃን ሰዎች እንደተገደሉና ሌሎች 11 ሰዎች ክፉኛ እንደቆሰሉ ገልጸዋል። ፓርቲዎቹ፣ መንግሥት ፖለቲካዊ ድክመቱን ለመሸፈን የጸጥታ ኃይሉን "ወደ ፖለቲካው በመሳብና እንዲኽ ያሉ በጦር ወንጀል ጭምር የሚያስጠይቁ የንጹኃን ጭፍጨፋ፣ መሰወርና የዘፈቀደ ግድያዎችን እንዲፈጽም የእጅ ጥምዘዛ ያህል እያስገደደውና እያሳሳተው ይገኛል" በማለት ከሰዋል።
ፓርቲዎቹ፣ "መንግሥታዊ ሽብር" እና "የጦር ወንጀል" ሲሉ የጠሩትን የድሮን ጥቃት፣ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ፣ የፖለቲካ ልኂቃን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ምሑራን፣ የመገናኛ ብዙኅንና የሰብዓዊ መብት ተማጋቾች እንዲቃወሙት ጠይቀዋል።