ወድጄሽ እንዳይ መስልሽ
ጋራ ሸንተረሩን ተራራን አቋርጦ
ልቤ የሚመጣው እኔን እዚ አስቀምጦ
ወዶሽ እንዳይመስልሽ አታስቢው ከቶ
.
.
እንደ ፀደይ ሰማይ ፊትሽ 'ሚናፍቀኝ
በጨረቃዋ ውስጥ ውበትሽሚታየኝ
ወድጄሽ አይደለም በዚህ አታስቢኝ
.
.
ልቤ ከኔ በላይ ስላንቺ የሚጨነቀው
አድማሱን ተሻግሮ እንደወፍ ሚበረው
ወድጄሽ አይደለም ፍጹም አታስቢው
.
.
ሌተቀን ስላንቺ ቆሞ እየፀለየ
አንቺን ብቻ ሚለዉ ከኔ በተለየ
በፍቅርሽ ውቂኖስ በናፍቆት ሚቀዝፈው
ወዶሽ እንዳይመስልሽ አንቺን አንቺን ያለው .
.
እናልሽ ፍቅርዬ...
ስላንቺ ምጨነቀው ምን ትሆንብኝ ብዬ
ወድጄሽ አይደለምእውነታው ሆድዬ
በናፍቆት ወጀብ እንዲህ ስንገላታ
ወድጄሽ እንዳይመስልሽ አታስቢው ላፍታ
.
.
አንደበቴ ታስሮ ልቤ ከባከነ
አንቺን ብቻ ብሎ በሀሳብ ከበገነ
ታድያ እንዴት ሆኖ ይሄ መውደድ ሆነ
.
.
አውነታውን ስሚ...
በፈረሱ ልቤ በፍቅር ተፈናጠሽ
በሀሳብ ሜዳ ላይ ሽምጥ እየጋለብሽ
የልቤን ዙፋን በሀይል ተቆናጥጠሽ
በፍቅር አክሊል በክብር አንግሼሽ ነው
እኔ ለኔ ትቼ ስላንቺ የምኖረው
.
.
አየሽ የኔፈቅር በልቤ ውስጥ ያለው
መውደድ ብቻ ሳይሆን ጥልቅ ሀያል ፍቅር ነው
ጋራ ሸንተረሩን ተራራን አቋርጦ
ልቤ የሚመጣው እኔን እዚ አስቀምጦ
ወዶሽ እንዳይመስልሽ አታስቢው ከቶ
.
.
እንደ ፀደይ ሰማይ ፊትሽ 'ሚናፍቀኝ
በጨረቃዋ ውስጥ ውበትሽሚታየኝ
ወድጄሽ አይደለም በዚህ አታስቢኝ
.
.
ልቤ ከኔ በላይ ስላንቺ የሚጨነቀው
አድማሱን ተሻግሮ እንደወፍ ሚበረው
ወድጄሽ አይደለም ፍጹም አታስቢው
.
.
ሌተቀን ስላንቺ ቆሞ እየፀለየ
አንቺን ብቻ ሚለዉ ከኔ በተለየ
በፍቅርሽ ውቂኖስ በናፍቆት ሚቀዝፈው
ወዶሽ እንዳይመስልሽ አንቺን አንቺን ያለው .
.
እናልሽ ፍቅርዬ...
ስላንቺ ምጨነቀው ምን ትሆንብኝ ብዬ
ወድጄሽ አይደለምእውነታው ሆድዬ
በናፍቆት ወጀብ እንዲህ ስንገላታ
ወድጄሽ እንዳይመስልሽ አታስቢው ላፍታ
.
.
አንደበቴ ታስሮ ልቤ ከባከነ
አንቺን ብቻ ብሎ በሀሳብ ከበገነ
ታድያ እንዴት ሆኖ ይሄ መውደድ ሆነ
.
.
አውነታውን ስሚ...
በፈረሱ ልቤ በፍቅር ተፈናጠሽ
በሀሳብ ሜዳ ላይ ሽምጥ እየጋለብሽ
የልቤን ዙፋን በሀይል ተቆናጥጠሽ
በፍቅር አክሊል በክብር አንግሼሽ ነው
እኔ ለኔ ትቼ ስላንቺ የምኖረው
.
.
አየሽ የኔፈቅር በልቤ ውስጥ ያለው
መውደድ ብቻ ሳይሆን ጥልቅ ሀያል ፍቅር ነው