ሁሉን ያስችልሃል!
፨፨፨፨/////፨፨፨፨
መንፈሳዊነት ስድብን ያስችላል፤ የትቺትን ሃይል ያሳንሳል፤ የዘለፋን አቅም ያከስማል። መንፈሳዊነት በፈሪሃ እግዚአብሔር (አላህን በመፍራት) የተቃኘ ማንነትን ያጎናፅፋል። በአምላክህ ስትተማመን ፍረሃትህ ይወገዳል፤ ስሜትህ ይስተካከላል፤ ውስጥህ ይነፃል፤ ትናንትህ የፀዳ፣ ዛሬህ የፈካ፣ ነገህም በብሩህ ተስፋ የተሞላ ይሆናል። ለመንፈሳዊ ህይወትህ ተገቢውን ትኩረትና ጊዜ ስጥ። ሃይማኖታዊ አስተምህሮዎችን ማዳመጥ፣ ቅዱሳት መፅሃፍትን ማንበብ፣ በጎ ምግባራትን መፈፀም፣ ሰዎችን መርዳት፣ መልካም ልበ ቀና ሰው ሆኖ መገኘት የመንፈሳዊነት መሰረት ነው። እውቀት እንደሚኖር ሁሉ መንፈሳዊነትም በህይወት የሚገለጥና በመሬት ላይ የሚታይ ነው። ብዙ ተምረናል፣ ብዙ አውቀናል፣ ብዙ ተግባራትን ፈፅመናል፣ ብዙ ቦታ ተገኝተናል ነገር ግን የማይኖር ተምህርት፣ የማይተገበር እውቀት፣ ፍሬ የሌለው ተግባር፣ ተርፍ የሌለው ቦታ መገኘት ከድካም ውጪ ጥቅም የለውም።
አዎ! ጀግናዬ..! ሁሉን ያስችልሃል። ወደ እራስህ መመለስህ፣ ከአምላክህ ጋር መነጋገርህ፣ እውነተኛው ስሜትህን ማዳመጥህ፣ ለውስጣዊ ማንነትህ ጊዜ መስጠትህ፣ በመንፈሳዊነት መቃኘትህ፣ በአምላክ ህግጋት መመራትህ፣ ከሰው በላይ ፈጣሪህን መፍራትህ፣ ለእርሱ ለመታመን መጣርህ በእርግጥም ሊጎዳህና ሃይልህን ሊያሳጣ የመጣውን የትኛውንም አሉታዊ ተፅዕኖ ያስችልሃል፤ የሚወረወርብህን ያልተገባ ቃል ያሳልፍሃል፤ ከሚደርስብህ ጫና ነፃ ያወጣሃል። የሰው ልጅ በሙሉ በደል አለበት፣ ሀጢያት አለበት። በደሉም አንድም አምላክን ሲሆን ሌላውም የሰውን ልጅ መበደሉ ነው። አለምም ለየትኛውም ሰዋዊ በደል ቅጣትን ትበይናለች፤ አምላክ ግን ይቅርታን ያስቀድማል፤ ጊዜን ይሰጣል፤ በትዕግስት ይጠብቃል፤ በመንፈሳዊነት ሊቃኘን ይሞክራል።
አዎ! ሁሉን እችላለሁ ብትል የሚያስችል ቸሩ አምላክ ነው፤ የመጣብኝን ሁሉ እሻገራለሁ ብትል የሚያሻግር ደግ ፈጣሪ ነው። እውቀትን ያደለን፣ ብርታትን ያጎናፀፈን፣ ደግ ልቦናን የሰጠን አምላክ እውቀታችንን የምንኖርበት ጥበብ፣ በብርታታችን የምናተርፍበት ንቃተ ህሊና፣ ደግ ልቦናችንን የምንጠቀምበት ብሩክ ሃሳብ ይሰጠን ዘንድ መልካም ፍቃዱ ይሁን። ሰላምህን በመንፈሳዊነት አግኘው፤ ፍቅርን ከአምላክ በረከት አትርፍ። መንፈሳዊነት አለምን ያስረሳኛል፤ መኖር ከሚገባኝ ህይወት ያግደኛል፤ ማፍራት ያለብኝን ንብረት ያሳጣኛል የምትል ከሆነ ከዚህ አመለካከት ውጣ። በመንፈሳዊነትህ የሚጨመርልህ እንጂ የምታጣው አንዳች ነገር የለም። በአዎንታዊ አመለካከቶች የምትቃኘው፣ በፈጣሪ የተወደዱ፣ ለሰው ልጆች የሚጠቅሙ፣ ህይወትህን የሚያረጋጉ ተግባራትን የምትፈፅመው በመንፈሳዊነት ሃይል ነው። በሔድክበት ሁሉ ከደግነትህ አትለይ፤ በምታደርገው ሁሉ ቅንነት አይለይህ፤ ላገኘሀው ሰው ሁሉ መልካም ሁን። ምናልባት ርህራሔህ ሊያስጠቃህ ቢችልም አምላክ ልብህን አይቶ በበረከት እንደሚሞላህ እመን።