የማታንቀላፉ ሁኑ!
ውጪ ከቤታችሁ በር አፋፍ ላይ ሁለት አይነት ሰዎች ይጠብቋችኋል። በቁጥር የበዙት ከአሁን ከአሁን ስለመውደቃችሁና ተስፋ ስለመቁረጣችሁ ለመስማት በጉጉት ይጠብቃሉ፣ በቁጥር እጅግ ያነሱትና በጣት የሚቆጠሩት ደግሞ ተስፋ አለመቁረጣችሁን፣ አለመበገራችሁንና ማሸነፋችሁን በትልቅ ጉጉት ይጠባበቃሉ። ማንን ማሳፈር ትፈልጋላችሁ? ማንንስ ማስደሰት ትፈልጋላችሁ? የእናንተን ምርጫ ውጪ የቆሙ ሰዎች አይወስኑላችሁም። ሁሉም በእጃችሁ ነው። ውድቀታችሁን አብዝተው የሚፈልጉ ሰዎች አስቀድመው የወደቁ ሰዎች ናቸው፣ በእናንተ ተስፋ መቁረጥ፣ በእናንተ ጀምሮ ማቋረጥ የሚደሰቱ ሰዎች ቀድሞውኑ የተበለጡና ተስፋቢስ ሰዎች ናቸው። አስቀድማችሁ አንድ ነገር አስቡ። የጀመራችሁት ጠላታችሁን ለማሳፈር ወይም ወዳጃችሁን ለማስደሰት አይደለም። የጀመራችሁት የገዛ ነፃነታችሁን ለማወጅ ነው፣ የጀመራችሁት የራሳችሁን ደስታ በራሳችሁ ለመጀመር ነው፣ የጀመራችሁት አቅማችሁን አውቆ ለማሳወቅ ነው። ሰውን ለማስደሰትም ሆነ ለማስቀየም ብላችሁ አትዘናጉ። የእናንተ ትልቁ አጀንዳ ጊዜያዊው የሰው ስሜት ሳይሆን ዘላቂው የእናንተ ስሜት ነው።
አዎ! የማታንቀላፉ ሁኑ፣ የማትበገሩ፣ እጅ መስጠት የማትወዱ፣ አለት ላይ የተገነባ ማንነት ያላችሁ፣ ፅናት መገለጫችሁ፣ ትዕግስት መለያችሁ የሆነ ብርቱ ሰው ሁኑ። ምቀኛችሁ ይፈር ወዳጃችሁ ይኩራ፤ ጠላታችሁ ይዘን ወዳጃችሁ ይደሰት። ለማንም ቁልፋችሁን አትስጡ። ራሳችሁ ስትፈልጉ ብቻ ክፈቱት ካልፈለጋችሁም ቆልፋችሁ አስቀምጡት። ሺህ ሰው እየጠላችሁ አንድ ሰው ቢወዳችሁ ጉዳያችሁ ከሚጠሏችሁ ሰዎች ጋር ሳይሆን ከዛ ከሚወዳችሁ አንድ ሰው ጋር ነው። ምንም አይነት ሰው ብትሆኑ የሚወዳችሁንም የሚጠላችሁንም ሰው ማግኘታችሁ አይቀርም። የራሳችሁ ወዳጅ ስትሆኑ ለወዳጃችሁ ቦታ መስጠት ትጀምራላችሁ፣ በራሳችሁ ስትተማመኑ ብቻ ብርታት ጥንካሬያችሁን አደባባይ ማውጣት ትችላላችሁ። ማንቀላፋት መገለጫችሁ እንዲሆን አትፍቀዱ፤ ስንፍና እንዲሰብራችሁ አትፍቀዱ። ቆቅ መሆንን ልመዱ። ለማንም በቀላሉ አትሸወዱ፣ ጨለማውን መቆያ አታድርጉት።
አዎ! ጀግናዬ..! ብዙዎች እንደ ተኙ ጊዜ ጥሏቸው ሄዷል፣ ብዙዎች በምኞት ታስረው ሃሳብ ብቻ ሆነዋል፣ ብዙዎች ከጥንካሬያቸው ይልቅ በስንፍናቸው እየተመፃደቁ ነው። አንተ ግን ከብዙዎች መሃል ተነጥለህ ውጣ፣ እያንቀላፋህ ፀሃይ አትጥለቅብህ፣ ሰበብ እያበዛህ ዓለም አትደብዝዝብህ፣ ተዘናግተህ ባዶህን እንዳትቀር፣ ትልቁ ሃይልህን ቸል አትበለው፣ ድክመትህን በመሸፋፈን ራስህን አታድክም። ከራስ በላይ ለሰው መኖር ድክመትህ ከሆነ ፊትለፊት ተጋፈጠው፣ ከወዳጅ በላይ ለጠላት ቦታ መስጠት ካበዛህ እይታህን ቀይር። አንዳንዶች ምንም ነገር የሚያልፍ አይመስላቸውም። የሆነ ጊዜ ጠላትህ የነበረ ሰው ወደፊት ወዳጅህ እንደማይሆን እርግጠኛ መሆን አትችልም፤ የዛሬ ወዳጅህም እንዲሁ ነገ ጠላትህ ሊሆን እንደማይችል እርግጠኛ መሆን አትችልም። በተለዋዋጭ ዓለም ማንቀላፋት አያስፈልግም። ነቅተዋል የተባሉ ሰዎችም ብዙ ተሸውደዋል። የማታንቀላፋ ንቁ ሰራተኛ ሁን። ዓለም ልትረሳህ ብትሞክርም አንተ ግን መኖር በውጤትህ አሳይ።