ማን ይናገርልህ?
ማንም የማያውቀው ነገር ግን አንተ የምታውቀው የግል ክህሎት፣ የግል ችሎታ አለህ፣ አውጥተህ ለመጠቀም ጊዜ ትጠብቃለህ። ስለራስህ እንድታወራ መድረክ ቢዘጋጅልህም ትህትናን በመሰለው የበታችነት ስሜት ስለእራስህ ለማውራት ታፍራለህ፤ ትፈራለህ። እራስን ማድነቅ፣ ስለራስ ብርታትና ጥንካሬ ማውራት፣ የእራስን መልካም ጎን ዘወትር በአውንታዊነት ማንሳት ግብዝነት ወይም እራስ ወዳድነት ይመስልሃል። አንዳንዴ ሰው እንዲያወራልህ የምትጠብቅበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፤ ሰው የሚያወራልህ ግን ስላደረክለት ወይም ካንተ ስላገኘው ነገር እንጂ ስላንተ ማንነት ሊያወራልህ አይችልም። ስለሆነ ሰው አውርተህ አትጠግብም ይሆናል፤ ስለመልካምነቱ፣ ስለቅንነቱ፣ ስለጥንካሬው፣ ስለጨዋታ አዋቂነቱ፣ ስለመረዳት አቅሙ። ስለራስህስ አውርተህ የማትጠግብበት፣ መስክረህ የማትረካበት ሁኔታ ቢፈጠርስ ሊሰማህ የሚችለውን ስሜት፣ ልታገኘው የምትችለውን በእራስ መተማመን አስበው።
አዎ! ጀግናዬ...! ነውር አሳፋሪ የሚባሉት የእራስ አገላለፅ ዘይቤዎች ልኬት አላቸው። ማንም የሌላውን መብት ሳይጋፋ፣ የሌላውን ስሜት ሳይነካ ስለእራሱ መናገር ቢችል ነውር ሊባል አይችልም፤ እራስን መግለፅ በእራሱ ጥበብ ነውና። ሰው ስለእራሱ ማውራት አለበት፣ ለለእራሱ መመስከር ይኖርበታል፣ ለእራሱ ሊሟገት ይገባል። ካልሆነ ግን ማንም ስለእርሱ የሚያውቀውን ትንሽ ነገር እንኳን ሊመሰክርለት አይችልም። አንተ ስለራስህ ካልተናገርክ፣ ለእራስህ ካልወገንክ፣ ስለእራስህ ካላወራህ ማን ያውራልህ? ማን ይናገርልህ? ማን ይወግንልህ? ማንስ ይደግፍህ? ለእራስህ ኩራት መሆን ካልቻልክ ማንም ኩራት የሚሆንህ ሰው የለም። በትህትናህ ሰዎችን ልታገለግል ትችል ይሆናል እራስህን ግን አሳልፈህ አትሰጣቸውም፤ ስላንተ የማያውቁትን ለማሳወቅ አትሸማቀቅም፤ ስለራስህ ለመናገር አታፍርም።
አዎ! የምታወራው ስለሌላ ሰው ሳይሆን ስለራስህ ነውና አትሸማቀቅ፤ የምትመሰክረው ስለምታውቀው ማንነት ነውና ሃፍረት አይያዝህ፤ የምታስረዳው እራስህን ነውና በእራስ መተማመን አይለይህ። ስለ ብዙ ነገር ብዙ አውርተናል፤ ስለማይመለከተን ብዙ ተንትነናል፤ ስላማናውቀው ብዙ አሽቃብጠናል፤ ስለምናውቀው እራሳችን በልበ ሙሉነት ብናወራ ነውርነት ሊኖረው አይችልም። ከስምህ በላይ ስለእራስህ የምትናገረው ነገር ያስፈልግሃል፤ ከስራህ በዘለለ የሚመሰክርልህ ሁነኛ ጠበቃ ያስፈልግሃል። እራሱን መግለፅ የማይችል፣ ስለማንነት ለመተንተን የሚሸማቀቅ፣ እሱነቱን በጉልህ ለማስረዳት የሚያፍር ሰው እራስን ስለማወቅና እራስን ስለመግለፅ ሁነኛ ጥቅሞች በቅጡ ያልተረዳ ሰው ነው። ስለእራስህ ስላወራህ የሚከስህ ሰው የለም፤ እራስህን መግለፅ ስለቻልክ፣ ለእራስህ ያለህን ፍቅር፣ ለእራስህ በምትሰጠው አክብሮትና ቦታ ምክንያት ለፍርድ የሚያቆምህ የለም። በነፃነት ስለእራስህ አውራ፤ እራስህን አነቃቃው፤ አበረታታው፤ አወድሰው። አንተ አንተ ለመሆንህ የማንንም ማረጋገጫ አልጠበክምና ስለአንተ እንዲያወራልህም ማንንም አትጠብቅ።