እንደ ቦታቸው ተረዳቸው!
ከጀርባህ ሆነው በሚያወሩ፣ በስኬትህ በሚቀኑ፣ በከፍታህ በሚበሳጩ፣ ተግባርህን በሚያቃልሉ ሰዎች በፍፁም አትናደድ። ምክንያቱም ስሜታቸው እንጂ ውስጣቸው መድረስ በሚፈልገው ስፍራ ሊናደድ አይችልምና። ምክንያቱም የንግግራቸው ይዘት በእራሱ ካንተ እንዳነሱ፣ ከኋላህ እንደቀሩ፣ ከአቅማቸውን እንደጎዱ አመልካች ነውና። ማንም ሰው ያለምክንያት ከጀርባ ሆኖ የሌላውን ሰው ስም ለማጥፋት አይሞክርም፤ በሌላው ውድቀት ለመደሰት አያኮበኩብም፤ በሌላው ችግርና ፈተና የእራሱን ህይወት ለማሻሻል አይሯሯጥም። በእራሱ የሚተማመን፣ በሳልና ብልህ ሰው የወንድሙ ደስታ ደስታው ነው፤ የጓደኛው ስኬት ስኬቱ ነው፤ የወገኑ ሰላም፣ የህዝቡ እረፍት ሰላሙ፣ እረፍቱ ነው። ማንም ክፉ የሚያስብ፣ ከኋላ ቢዶልት፣ ደባ ቢያደባ ከጀርባ ሆኖ የሚያሸንፈው ትግል አይኖርም። ስም በማጥፋት፣ ገፅታን በማጠልሸት፣ ጫናዎችን በማብዛት የእርሱ ስም የሚገነባ፣ ገፅታው የሚስተካከል ቢመስለውም ቅሉ ግን የተዛባው እይታው ለከፋ ውድቀት ይዳርገዋል።
አዎ! ጀግናዬ..! እንደ ቦታቸው ተረዳቸው! ወዳጅህ መስለው የጠላት ስራ የሚሰሩብህ፣ በልብ ጓደኝነት ሰበብ ከጀርባ የሚያደቡብህ፣ አጀንዳቸው ሁሉ ያንተ እድገትና ለውጥ በሆነባቸው ሰዎች አትበሳጭ፣ አትዘን፣ አትናደድ። ክፉዎች ሁሌም ስፍራቸው ከኋላ ነው፤ ተንኮለኞች ዘወትር ምልልሳቸው በዝቅታ ነውና እንደ ቦታቸው ተረዳቸው። የምቀኝነት እሳቤ የውድቀት መንገድ ነው፤ የንፉግነት ማንነት የትንሽነት ልክ ነው። መልካምነት ልብን ይጠይቃል፤ ሰው መሆን ይፈልጋል። ለእራስ እንዲሆን የሚመኙትን በሰው ሲመለከቱ ከኋላ ከመንሾካሾክና በድብቅ ክፋትን ከመዶለት ይልቅ በግልፅ የደስታው ተካፋይ መሆን የመልካምነት መለኪያ ነው። ልበ ቀና ደግ ሰው ሃሳቡ በእራሱ በጎነትን ያድለዋል።
አዎ! በወዳጅህ ደስታ ተደሰት፣ ከስኬቱ የምስራች ተቋደሰው፣ የከፍታውን ብስራት አካፍልለት። ትልቅነት በቅንነት፣ ብስለትም በአጋዦነት የሚገለፅ ነው። አርቆ የሚያስብ፣ ህልመኛና ባለራዕይ ሰው ትልቅ ስፍራ በደረሱ፣ ስኬትን በተቆናጠጡ፣ ከከፍታው በደረሱ ሰዎች አይቀናም፤ አይናደድም፤ አይበሳጭም። መንገዳቸውን መማሪያ፣ ስኬታቸውንም እንደ መነቃቂያ ይወስደዋል። ሁሉም ታስቦ የሚደረግ ነገር የእራሱ በቂ ምክንያት አለው። ሰዎች ያለምክንያት በለውጥህ አይበሳጩም፣ በእድገትህ አይናደዱም፣ በደስታህ አይቃጠሉም። አስከፊው ከፋት የስሜት ጭካኔ፣ የስሜት ደባ፣ የስሜት ጥላቻ ነው። ተንኮልን ከውስጡ የሚያወጣ፣ ጥሎ ለማለፍ ሁሌም የሚሯሯጥ፣ ሰው ሲያልፍለት አይኑ የሚቀላ ሰው አደገኛ ነውና ተጠንቀቀው። ግብህ ላይ ካተኮርክ፣ ልዩነት መፍጠር ከጀመርክ፣ ብዙዎች የሚመኙትን ነገር እጅህ ወደማስገባት ከተጠጋህ የኋላ ጫናና ክፋቶች ይበዛሉና ለእራሰህ ታመን፣ በጅማሬህ ቀጥል፣ ጫናዎችን ተጋፈጥ፣ ጥላቻውንም ጥልህ እለፍ።