ከራስህ አትሽሽ!
ራሳችንን በማንቀበልበት ጊዜ ሳናስበው ራሳችንን ጥለን ወደ ሌላኛውና የእኛ ወዳልሆነው ማንነት እንድንሄድ ይገፋፋናል፡፡ በዚህ አይነት ተጽእኖ ውስጥ እንድንወድቅ የሚያደርጉን ሁኔታዎች በዙሪያችን ሞልተዋል፡፡ እነዚህ “ጥሪዎች” መነሻቸው በውስጣችን የሚገኘው ተቀባይነት የማግኘትና ራስን የመቀበል ስነ-ልቦናዊ ፍላጎት ነው፡፡
በውስጣችን ያለውን የመወደድና ተቀባይነት የማግኘት ፍላጎት ለማሟላት ብዙ ነገሮችን ለማድረግ ይቃጣናል፡፡ ሳናስበውም ራሳችንን ማለቂያ የሌለው ጉዞ ውስጥ ገብቶ እናገኘዋለን፡፡ ይህ እንዳይሆን በውስጣችን ያሉትን ስነ-ልቦናዊ ፍላጎቶች በማወቅ ትክክለኛ የመፍትሄ መንገድ መፈለግ አለብን እንጂ ራስን ባለመቀበል ስቃይ ውስጥ መማቀቅ የለብንም፡፡ የሚከተሉትን ከራሳችን እንድንሸሽ የሚያደርጉንን ስውር ስነ-ልቦናዊ ምክንያቶች እንመልከት፡፡
1. ተቀባይነት ፍለጋ
አንዳንድ ሰዎች ቤተሰባቸውን ለማስደሰት፣ ልባቸውን የሳበው ፍቅረኛ እንዲቀበላቸው፣ እንዲሁም በአንድ ቡድን ውስጥ ተቀባይነት ለማግኘት ራሳቸውን ለመለወጥ ሲጣጣሩ ይታያሉ፡፡ የዚህ አይነቱ ራስን የመለወጥ ሙከራ ግን መጨረሻው ድካምና “ራስን ማጣት” ነው፡፡ ብቸኛው መፍትሄ ራስን ተቀብሎና ሆኖ መኖር ነው፡፡
2.ዘመናዊነትን ፍለጋ
የዘመኑን ፋሽን፣ የዘመኑን ቁመናም ሆነ የዘመኑን የንግግር ዘይቤ ሁሉ ተከታትለንና አውቀንበት መኖር ብንችል መልካም ነበር፡፡ ሁኔታው ግን ያን ያህል ቀላል አይደለም፡፡ “ዘመናዊ ሰው መስዬ ካልታየሁ ተቀባይነት አላገኝም” ከሚለው ማለቂያ የሌለው የውስጥ ጥማት ከሚመነጭ ትግል መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው፡፡
3.ስኬታማ መስሎ የመታየት ጥማት
አንዳንድ ሰዎች በተለያዩ የኑሮ ዘርፎች ስኬታማ መስሎ ለመታየት የማያደርጉት ጥረት የለም፡፡ ስኬት ግን የታይታና የአንድ ጊዜ ክስተት ሳይሆን ሂደትና የኑሮ ዘይቤ ነው፡፡ የስኬት መነሻው መሆን ያለበት በመጀመሪያ ራስን ሆኖ መገኘት ነው፡፡ በመቀጠልም ባመኑበት ጎዳና ወደ መሰማራትና ራስን ወደ ማሻሻል ሊያድግ ይገባዋል፡፡