የቤዛነትን ትርጉም ንገረን ላላችሁኝ እነሆ
ቤዛነት ምንድን ነው?
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ልጆች በሰው ልጆች ምትክ ያደረገው ሥራ ቤዛነት ይባላል። ቤዛ በአገባቡ "ስለ" ነው። ምሥጢሩ ምትክነትን ይገልጻል። ቤዛ "ቤዘወ-አዳነ" ከሚለው ግሥ ሲወጣ መድኃኒት ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። በሁለቱም ለክርስቶስ ቢነገር ያስኬዳል። መድኃኒታችንም ነውና። ቤዛ-ስለ በሚለው አገባብ ከተተረጎመ ስለእኛ በመስቀል ተሰቅሎ ማዳኑን ይነግረናል። ክርስቶስ ያደረገው ሥራ ሁሉ ስለእኛ ነው። በትርጓሜ በሐተታ በእንቲኣነ (ስለእኛ) እየተባለ የሚገለጸው እንደ ኃጥኣን ስቶ፣ እንደ ሰማዕታት ዕሴትን ሽቶ ያደረገው አለመሆኑን ለመግለጽ ነው።
ይህ ክርስቶስ ያደረገው የቤዛነት ሥራ የባሕርይ ሥራ ነው። ቅዱሳን ደግሞ አምላካቸው ክርስቶስን መስለው ስለሌላው ሰው ብለው የሚቀበሉት መከራ ቤዛነት ነው። ግን የጸጋ ቤዛነት ነው። "ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም" የሚለው ቃል ሰዎችም በአቅማቸው አንዱ ለአንዱ ቤዛ መሆን እንዲችሉ የተነገረም ጭምር ነው። ግእዙ "አልቦ ዘየዐቢ ወይኄይስ እምዝ ፍቅር ከመ ብእሲ ዘይሜጡ ነፍሶ ቤዛ ነፍሰ ቢጹ" ይለዋል (ዮሐ.15፥13)። ቅዱሳን ክርስቶስን አብነት አድርገው ስለሌሎች ሰዎች ሲጸልዩ፣ ሲጾሙ፣ ሲሞቱ አይተናል። ጌታም የእነርሱን ፍቅር አይቶ ኃጥኣንን ሲምር በብዛት ተጽፏል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሐዲስ ኪዳን ላይ ስንገባ በሰፊው እንመለከተዋለን።