ሚኒስቴሩ ሥነ-ምግባርን ለመገንባት እና ሙስናን ለመከላከል ባደረገው ጥረት ተሸላሚ ሆኗል
ታሕሳስ 2/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
የገቢዎች ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም የሰራተኛውን የስነ-ምግባር ልዕልና በመገንባትና ሙስናን ለመከላከል በሰራው ስራ ከመንግስት ተቋማት አንደኛ በመሆን ዛሬ በሀገራችን በተከበረው የዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን ላይ እውቅና ተበርክቶለታል፡፡
እውቅናው የተበረከተው የፌዴራል የሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን 21ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ - ሙስና ቀንን «ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል የነገ ስብዕና ይገነባል» በሚል መርህ ከፌዴራል ተቋማት፣ የክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የስነ-ምግባር ባለሞያዎች እንዲሁም ወጣቶች በተገኙበት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ባከበረበት ወቅት ነው፡፡
በመድረኩ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አፅቀሥላሴ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ፣ የምክር ቤት አባላት፣ የፌደራል የስነ-ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር)፣ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ሚኒስቴሩ ከፌዴራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በተቀናጀ መንገድ አብሮ ከመስራት አንጻር የተሻለ አፈጻጸም በማምጣት እና አንደኛ በመውጣቱ ተሸላሚ የሆነ ሲሆን ሽልማቱን የገቢዎች ሚኒስቴርን በመወከል የሚኒስቴሩ የታክስ ስርዓት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ መስከረም ደበበ ከኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አፅቀሥላሴ እጅ ተቀብለዋል፡፡
በታደሰ ኢብሳ
ፎቶ፡- የትናየት እንዳያፍሩ