ብሄራዊ የታክስ ሪፎርም ግብረ ሀይል የአምስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ
ታህሳስ 8/ 2017 ( ገቢዎች ሚንስቴር )
ብሄራዊ የታክስ ሪፎርም ግብረ ሀይል የህዳር ወርና ያለፉትን አምስት ወራት የገቢ ዘርፍ ማሻሻያ እቅድ አፈጻጸምን በገቢዎች ሚንስቴር በመገኘት ገምግሟል።
የታክስ ግብረ ሀይሉ ከገቢ እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ባሻግር በሚንስቴሩ የተክናወኑና በመክናወን ላይ ያሉ የሪፎርም ስራዎችንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በሚኒስቴሩ እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርም ስራዎች የሚበረታቱና የገቢ ማሻሻያው አንድ አካል መሆናቸውን የጠቆሙት የግብረ ሀይሉ አባላት በተለይ በቴክኖሎጅና ምቹ የስራ ቦታን ከመፍጠር ጋር በተያያዘ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በሂደት የመንግስትን ወጭ የሚቀንሱና ለተገልጋዩና ለሰራተኛው ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ መሆናቸውን አንስተዋል።
በመጨረሻም የታክስ ግብረ ሀይሉ በአምስት ወራት የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶች በቀጣይ ስድስት ወራትም በተመሳሳይ ውጤታማ ሆኖ እንዲቀጥል አቅጣጫዎችን በመለዋወጥ ግምገማውን አጠናቋል።
ምንጭ፡- ሚኒስትር ጽ/ቤት
ፎቶ፡- እስካለም ሰፊው