የገቢዎች ሚኒስቴር ገቢ ከመሰብሰብ ጎን ለጎን ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው
ጥር 23/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
በገቢዎች ሚኒስቴር ዋናው መስሪያ ቤት የሚገኙ አመራሮችና ሠራተኞች ከጥር 22 እስከ 23/2017 ዓ.ም በፈቃደኝነት ደም ለገሱ፡፡
የደም ልገሳው ከመካሄዱ ቀደም ብሎ ስለ ደም ልገሳ መርሃ ግብር ዓላማ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ተሰርቷል፡፡
ገቢ ከመሰብሰብ ጎን ለጎን ደም በመለገስ የማይተካውን የሰው ሕይወት ለማዳን ማኅበራዊ ኃላፊነትን መወጣት እንሚገባ በገቢዎች ሚኒስቴር የማኅበራዊ ጉዳይ ድጋፍና ክትትል ቡድን መሪ ሀናን ባዲ ገልጸዋል፡፡
በብሄራዊ ደም ባንክ የትምህርት እና ቅስቀሳ ባለሙያ የሆኑት ሲስተር አሰጋሽ ጎሳ በሚተካ ደም የማይተካ የሰው ልጅ ሕይወት ለማዳን የገቢዎች ሚኒስቴር ከብሄራዊ የደም ባንክ ጋር በመሆን ተከታታይነት ባለው መልኩ የደም ልገሳ መርሃ ግበሩ በየሦስት ወሩ እተከናወነ በመሆኑ ምስጋናቸውን ገልጸው ይህ ደም የመለገስ ባህል ወደፊትም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በደም ልገሳው የተሳተፉት የዋናው መ/ ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ደም በመለገሳቸው መደሰታቸውን ገልጽው ሌሎችም በዚህ በጎ ተግባር እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በእታገኝ አቦሰጥ
ፎቶ:- የትናየት እናዳያፍሩ