ዜና: ህወሓት #የትግራይ ህዝብ የሰላም ምኞት ዕውን እንዲሆን ሁሉም ገንቢ ሚና እንዲጫወት ሲል ጥሪ አቀረበ
በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (#ህወሓት) ቡድን የትግራይ ህዝብ እና የትግራይ ልሂቃን ቀዳሚ ምርጫው ሰላም ነው ሲል ትላንት ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ጠ/ሚኒስት አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።
ህወሓት የጠ/ሚኒስትሩን ጥሪ ተከትሎ ትላንት ጥር 28 ቀን መግለጫ ያወጣ ሲሆን በመግለጫውም የትግራይ ህዝብ ቀዳሚ ምርጫ ሰላም ነው ብሏል፤ የትግራይ ህዝብን የሰላም ምኞት አውን ለማድረግ ሁሉመ ገንቢ ሚና ይጫወት ሲል ጠይቋል፤ ከማንኛውም አካል ጋር በሰላም ዙሪያ ለመስራት ዝግጁ ነኝ ሲል አስታውቋል።
ህወሓት በመግለጫው ባለፉት መቶ አመታት የትግራይ ህዝብ ያደረጋቸው ጦርነቶች “ህልውናውን ለማረጋገጥ እና ለጭቆና አጅ አልሰጥ በማለት ነው” ሲል በመግለጽ “የትግራይ ህዝብ ያደረጋቸው ተጋድሎዎች ያኮሩታል እንጂ አያስቆጩትም” ብሏል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=6731