አሁን ላይ'ኮ በራሳችን ሃገር ነፃነት አጥተናል። በሰላም ከቤተሰብና ወዳጅ ዘመድ ጋር መገናኘት እየቀረ ነው። አልፎ አልፎ በስልክ ለመገናኘትም በግድ ነው። የተከበረውን የሰው ልጅ ማረ'ድና ያንን እንደ ጀብዱ ቀርፆ ማሰራጨት ብዙ ትርጉም አለው። ህዝቡ ከርስ በርስ ጥላቻና ከጅምላ ፍረጃ ወጥቶ የጋራ ጠላቱን ለይቶ ለፍትሕ በማቅረብ ነገሩን በጥበብ ሊያየው ይገባል። የመንግስት አካላትም ይህን በየቦታው ያለ። አለመረጋጋት እንደት መፍታት እንዳለባቸው ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው። እስከ መቼ በሰቀቀን?