ለሴት እህቶቼ ከልቤ በልመናም ጭምር የምመክራችሁ ነገር፤ ፎቷችሁን አትፖስቱ። የፖሰታችሁትንም አጥፉ። በዚህ የፈሳድና የቴክኖሎጂ ዘመን አንድ ቀን በዚህ ድርጊታችሁ ታለቅሳላችሁ፣ ታፍራላችሁ፣ ትፀፀታላችሁ፣ የትዳር ህይዎታችሁና ማኅበራዊ ህይዎታችሁም ሊቃወስ ይችላል። ከዚህ በላይ በዝርዝር መናገር አይጠበቅብኝም። ሐራም ነው ሐላል ነው ብቻ እያልኩ እንዳይመስላችሁ። እንኳን ሐላል ያልሆነውን የተፈቀደ ቢሆን እንኳ ላላሰባችሁት የፈሳድ አላማ ስለሚውል ይቅርባችሁ። አልገባችሁም ምን እንደሚካሄድበት! የገባው በጥቅሻ ይገባዋል! የልጆቻችሁንም ፎቶ አትፖስቱ። ኋላ ምን እንደሚሆኑ አታውቁም። ዛሬ ላይ ለውሳኔ አልደረሱም። እናንተ ክፉ ነገር ባታስቡበትም ኋላ ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም። ኋላ ራሳቸው አድገው ጎልመሰው መፖሰት ይኑርባቸው አይኑርባቸው ይወስናሉ። ዛሬ ፖስታችሁባቸው እነርሱ ኋላ ካልፈለጉ ላንንተም ጸጸት ነው፣ ለነርሱም መሳቀቅ ነው።
||
t.me/MuradTadesse
||
t.me/MuradTadesse