Репост из: Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
የዓለማችን የናጠጠ ባለሃብትና ባለስልጣን በ3 ከፈን ጨርቅ‼
========================================
This the end!
||
✍ ትናንት ወደ አኺራ የሄደው ኸሊፋ ቢን ዘይድ የዘይድ ቢን ሱልጧን አል-ነሕያን የመጀመሪያ ልጃቸው ነው። ዘይድ ሱልጧን የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬት (UAE) እንደ ሃገር ከተቋቋመችበት የፈረንጆቹ 1973 ጀምሮ እስከ ኖቬምበር 2, 2004 ድረስ ፕሬዝዳንት ነበሩ። ትናንት የሞተው የመጀመሪያ ልጃቸው ኸሊፋ ደግሞ ከ1990ዎቹ ጀምሮ እርሳቸው እስከ ሞቱ ድረስ አልጋ ወራሽ ሆኖ የተለያዩ ሥራዎችን የሠራ ሲሆን፤ ከኖቬምበር 3, 2004 ጀምሮ ትናንት እስከ ሞተ ድረስ የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት በመሆን አገልግሏል። በረሃማዋን ሃገር አልምተዋል ተብለው ይወደሳሉ። ትናንት የሞተው ኸሊፋ ጥሬ ሃብቱ 18 ቢሊዮን ዶላር ነው። አሁን ላይ ባለው ከረንሲ 936 ቢሊዮን ብር እንደማለት ነው። እንዲገባችሁ የሃገራችን ኢትዮጵያ የባለፈ አመት በጀቷ 476 ቢሊዮን ብር ሲሆን፤ የዘንድሮው ደግሞ 18 በመቶ አደገ ተብሎ 561 ቢሊዮን ብር ነው። በአጭሩ የአንዱ ግለሰብ ሃብት ብቻውን ከ120 ሚሊዮን በላይ ህዝብ አላት ለቢባልላት ለእኛ ሃገር የሁለት አመት በጀት ሊሆናት ምንም አልቀረው። ለንጽጽር እንዲመቻችሁ ከፈለጋችሁ፤ አሁን ላይ ስልጣን ላይ የሚገኘው 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሃብቱ ከ8–9 ሚሊዮን (ቢሊዮን አይደለም) ዶላር ገደማ ነው። ይህ ማለት ትናንት የሞተው የ"UAE" ፕሬዝዳንት ሃብቱ ቢከፋፈል፤ የ2, 000 ጆ ባይደኖች ሃብት ይሆናል ማለት ነው። አያችሁ ልዩነት‼
በዓለም ላይ ረጅሙ የሚባለው ቡርጂ ኸሊፋ ህንጻም የተሰየመው በርሱ ነው። እንደ ፎርብስ መጽሔት ከሆነ ደግሞ ይህ ሰው 97.8 ቢሊዮን የነዳጅ ዘይት በርሜል ክምችት አለው። አጠቃላይ የአል-ነሕያን ቤተሰብ ሃብታቸው 150 ቢሊዮን ዶላር (7.8 ትሪሊዮን ብር ገደማ) እንደሆነ ይነገራል።
♠
✔ ታዲያ ይህ ሰው ሞተ። የራሱ ሃብት ብቻውን አንድ ትሪሊዮን ገደማ ነው። የቤተሰቡንም የምትታዘቡት ነው። ቀጣዩ መሪ ታናሹ ወንድሙ ነው። ስልጣኑም ሃብቱም በቤተሰቡ እጅ ነው። ግን ሲሞት ከዚህ አንድ ትሪሊዮን ገደማ ሃብት ውስጥ የተከተለው 3 ነጠላ ጨርቆች ብቻ ናቸው። ቀብሩንም ከታች እንደምትመለከቱት አፈር ነው። ባለሃብቶቹና ባለስልጣኖቹ ቤተሰቦቹ ጥለውት ተመልሰዋል። ይህቺ 3 ነጠላ ጨርቅና ሥራው ግን አብረውት ናቸው። ጨርቆቹ ከሆኑ ቀናት በኋላ ይበሰብሳሉ። ሥራውን ግን ቀሪ ነው።
ታዲያ ምን እንማራለን⁉️ ይህ ነው ኢስላም! ባለ ስልጣንና ባለሃብት ስለሆነ ብቻ የተደረገለት ነገር የለም። ያው እንደ ዲሆቹ በ3 ነጠላ ጨርቅ ተሸፍኖ ከአፈር ጋር ተጨምሯል። ቀብሩም ላይ እንደምትመለከቱት ህንጻ የለም። ጎዳና ላይ እየለመነ ህይዎቱን ሲገፋ የነበረ ዲሃና የርሱ ቀብር አንድ ናቸው።
የዓለም መሪዎች እስኪመጡ ይጠበቅ… ወዘተ የሚባል ነገር የለም። ሞት አይደለ? ኸላስ ወዲያው ይሸኛል። አለቀ! ይህ ነው ኢስላም‼ እንደት ደስ ይላል ውበቱ በአላህ‼ መስጂድ ውስጥ ለባለሃብቶችና ባለስልጣናት ተብሎ የተለዬ ሶፍ የለም። ከድሃ ጋር ጎን ለጎን ትሰግዳለህ፣ ከድሃ ጋር ትቀበራለህ፣ ይልቅ መልካም ሥራ ካላቸው ዲሆች ጋር እንዲቀሰቅስህ አላህን ለምነው!
√ «የኣደም ልጅ ሲሞት ከ3 ነገሮች ውጭ ሥራው ይቋረጣል። ቋሚ ሶደቃ፣ ጠቃሚ ዕውቀት፣ ዱዓእ የሚያደርግ መልካም ልጅ!» ተብሏልና በሐዲሥ ከወዲሁ አመቻች።
(إذا مات ابنُ آدمَ انقطع عملُه إلا من ثلاثٍ : صدقةٍ جاريةٍ ، وعلمٍ ينتفعُ به ، وولدٍ صالحٍ يدعو له)
[ሙስሊም: 1631]
*
✔ ፕሬዝዳንቱን ቤተሰቡ ሸኘውና ተመለሰ፣ ሃብቱም ተመለሰ፣ ሥራው ግን ቀረ።
የነቢዩ ﷺ ኻዲም አነስ ኢብኑ ማሊክ ባስተላለፈው ሐዲሥ ላይ ውዱ ነቢይ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
( يَتْبَعُ المَيِّتَ ثَلاَثَةٌ ، فَيَرْجِعُ اثْنَانِ وَيَبْقَى مَعَهُ وَاحِدٌ : يَتْبَعُهُ أَهْلُهُ وَمَالُهُ وَعَمَلُهُ ، فَيَرْجِعُ أَهْلُهُ وَمَالُهُ وَيَبْقَى عَمَلُهُ ) .
«ሟችን 3 ነገሮች ይከተሉታል፤ ሁለቱ ይመለሱና አንዱ ከርሱ ጋር ይቀራል። ቤተሰቡ፣ ገንዘቡና ሥራው ይከተሉታል። ቤተሰቡና ገንዘቡ ሲመለሱ ሥራው ይቀራል።»
[አል-ቡኻሪይ: 6514፣ ሙስሊም: 2960]
ይሄው ነው መራሩ እውነታ‼ This is the end‼
አላህ የሁላችንንም መጨረሻ ያሳምርልን።
በመጨረሻም ይህቺን የዐረብኛ ጽሑፍ ልጨምራችሁና ጽሑፌን ላስርግ።
(مَا أَغْنَىٰ عَنِّي مَالِيَهْ ۜ
«ገንዘቤ ከእኔ ምንንም አላብቃቃኝ፤ (አልጠቀመኝም)፡፡
هَلَكَ عَنِّي سُلْطَانِيَهْ
«ኀይሌ ከእኔ ላይ ጠፋ» (ይላል)፡፡)
[አል-ሐ-ቅ'ቃህ: 28-29]
የሃሩን ረሺድን አጭር ታሪክ ላክላችሁ።
يا من لا يزول ملكه .. ارحم من قد زال ملكه ..
الموت لا يفرق بين كبير وصغير .. ولا غني وفقير .. ولا عبد وأمير ..
هارون الرشيد
ذاك الذي ملك الأرض وملأها جنوداً ..
ذاك الذي كان يرفع رأسه .. فيقول للسحابة : أمطري في الهند أو في الصين .. أو حيث
شئت .. فوالله ما تمطرين في أرض إلا وهي تحت ملكي ..
هارون الرشيد .. خرج يوماً في رحلة صيد فمرّ برجل يقال له بُهلول ..
ሃሩን ረሺድ በአንድ ወቅት ጋልቦ እየተጓዘ ሳለ ቡህሉል በሚባል ሰው አጠገብ ሲያልፍ፤
فقال هارون : عظني يا بُهلول ..
«ቡህሉል ሆይ! ምከረኝ/ገስጸኝ እስኪ?» አለው።
قال : يا أمير المؤمنين !! أين آباؤك وأجدادك ؟ من لدن رسول الله صلى الله عليه وسلم إلى أبيك؟
«አንተ የአማኞች መሪ ሆይ! ከአላህ መልዕክተኛ ﷺ ጀምሮ እስከ አባትህ ድረስ ያሉት አባቶችህና አያቶችህ የት ናቸው?» አለው።
قال هارون : ماتوا ..
«ሙተዋል!» አለው።
قال : فأين قصورهم ..؟
«ህንጻዎቻቸው የት ናቸው?» አለው።
قال : تلك قصورهم ..
«ይሄው ህንጻዎቻቸው!» አለው።
قال : وأين قبورهم ؟
«መቃብሮቻቸውስ?» አለው።
قال : هذه قبورهم ..
«ይሄው መቃብራቸው!» አለው።
فقال بُهلول : تلك قصورهم .. وهذه قبورهم .. فما نفعتهم قصورهم في قبورهم ؟
«እኚህ ህንጻዎቻቸው ናቸው። እኚህ ደግሞ መቃብሮቻቸው ናቸው። ህንጻዎቻቸው በመቃሽሮቻቸው ውስጥ ምን ጠቀሟቸው?» አለው።
قال : صدقت .. زدني يا بهلول ..
«(ምንም አልጠቀሟቸው!) ልክ ነህ!» አለው።
قال :أما قصورك في الدنيا فواسعة * فليت قبرك بعد الموت يتسع
||
t.me/MuradTadesse
twitter.com/MuradTadesse