አስታውሳለሁ… ከዛሬ አመት በፊት ነበር፤ አንድ አባቱ በጥበቃ ሥራ የተሰማሩና እናቱ ጉሊት እየሠሩ ቤተሰቡን የሚያስተዳድሩ፣ ታናሽ እህቱ የኦቲዝም ታማሚ የሆነች ሚስኪን ቤተሰብ አባል የሆነ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የ4ኛ አመት የኢንጂነሪንግ ተማሪ ወንድማችን በጠና ታሞ መታከሚያ አጥቶ ነበር። እናንተን ደጋጎችን ተባበሩት ብያችሁ ፖሰትኩት።
አንድ ስልክ ተደወለልኝ። የአሚን ጠቅላላ ሆስፒታል ባለቤት ዶ/ር ሙሐመድ ሽኩር ነበር። ሰላምታ ካቀረበልኝ በኋላ «ስልኬን አታውቀውም ወይ?» አለኝ። «አውቀዋለሁ!» አልኩት። «ካወቅከው፤ ከመፖሰት እና ወደ'ኔ ከመደወል የቱ ይቀላል?» አለኝ። «እንዳትቸገር በማሰብ ነው!» አልኩት።
እንዲህም አለኝ፦ «ሕክምና ብዙ ጊዜ ይፈጃል። ሆኖም ግን ሕክምናውን እስካጠናቀቀ ድረስ እኛ አስደስተን እንሸኘዋለን። ሙሉ ወጪውን እንሸፍናለን!» አለኝ። እኔም ደስ አለኝ።
ይህ የ3ኛ ወገን ምስክር ሳያስፈልግ እኔ በራሴ የማውቀው ነው። ብዙ ኸይር ሥራዎች ላይ እንደሚሳተፍ አንዳንድ ወንድሞች ያጫውቱኛል።
እንዲህ አይነቱ በጎ ሰው Antex Textile PLC የተሰኘ ባለቤቱ ቻይናዊ የሆነና በሃገራችን የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማራ ትልቅ ድርጅት ባዘጋጀው "Best Influencer Work (BIW)" Prize በኢኮኖሚ ዘርፍ እየተወዳደረ ይገኛል።
ድርጅቱ በሁለት መስኮች ማለትም በኢኮኖሚ እና በሰላም ዘርፍ ለሚመረጡ ሁለት ተፅዕኖ ፈጣሪ አሸናፊዎች ለእያንዳንዳቸው 10 ሚሊዮን ብር እሸልማለሁ ብሏል።
በኢኮኖሚው ዘርፍ ለ10 ሚሊዮኑ ሽልማት እየተወዳደሩ ከሚገኙት መካከል አንዱ የሆነው የአሚኑ ዶ/ር ሙሐመድ ሽኩር፤ ይህን ሽልማት ካሸነፍኩ ሙሉ በሙሉ ገንዘቡን ለህዝባዊ ጤና ጣቢያዎች ለማዋላጃና ጨቅላ ህፃናት ሕክምና ክፍሎች እለግሳለሁ ብሏል።
ስለዚህ በእናትና በህፃናት ማን ይጨክናል?
በሃብት ላይ ሃብት ለማካበት ሽልማቱን አልፈለገውም። አሁንም የበለጠ ድጋፍ ለማድረግና የበጎነት ሥራ ለመሥራት ነው።
ዶ/ር ሙሐመድ ሽልማቱ የሚገባው ቢሆንም እኔ ግን ለነዚህ ወላጅ እናቶችና ጨቅላ ህፃናት ስልም ጭምር እመርጠዋለሁ።
እናንተስ⁉️
በዚሁ አጋጣሚ በሰላም ዘርፍ እየተወዳደሩ ካሉት እጩዎች መካከል አንዱ «ድምፃችን ይሰማ» ነው። ምንም እንኳ በአካሄዱ ላይ ግድፈቶች መኖራቸው ባይካድም ከቀረቡት እጩዎች አንፃር 100% ቁጥር አንድ ሊመረጥ ይገባል።
የድምፅ መስጫው ጊዜና መንገዱ ሲነገር በምን መልኩ ድምፅ መስጠት እንዳለባችሁ አሳውቃችኋለሁ። እስከዛው ዝግጁ!
||
t.me/MuradTadesse