🔥የንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ አንድ መቶ ስምንተኛ (108ኛ) ዓመታት የንግሥና መታሰቢያ‼️
#ዝክረ_ታሪክ
ከአንድ መቶ ስምንት (108) ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ እለት ታሪክን የኋሊት
የታላቁ ንጉሥ ነገሥት ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ልጅ የሆኑት ወይዘሮ ዘውዲቱ ምኒልክ ‹‹ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ወለተ ለዳግማዊ ምኒልክ ስይምተ እግዚአብሔር›› ተብለው በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በሊቀ ጳጳሱ በአቡነ ማቴዎስ እጅ ቅብዐ መንግስት ተቀብተው የንግሥትነት ዘውድ የጫኑት ከዛሬ አንድ መቶ ስምንት (108) ዓመታት በፊት (የካቲት አራት (4) ቀን ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠኝ (1909) ዓመተምህረት) ነበር፡፡
በዚሁ ዕለትም የራስ መኮንን ወልደሚካኤል ልጅ የሆኑት ተፈሪ መኮንን ‹‹ራስ ተፈሪ›› ተብለው ታላቁን «የሰለሞን ኒሻን» ተሸልመው እና ለአልጋ ወራሽ የሚገባው ክብርና ስርዓተ-ፀሎት ተደርጎላቸው ‹‹ልዑል አልጋ ወራሽ ራስ ተፈሪ መኮንን›› ተብለው ተሰየሙ፡፡
ዘውዲቱ ምኒልክና ተፈሪ መኮንን የዳግማዊ ምኒልክ ዙፋን ወራሽ እንደሆኑ የታወቀው ልጅ ኢያሱ ሚካኤል መስከረም አስራ ሰባት (17) ቀን ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠኝ (1909) ዓመተምህረት ከዙፋኑ በተሻሩበት እለት ነበር፡፡
#የኋላው_ከሌለ_የለም_የፊቱ‼️
#ይህ_የኛ_የኢትዮጵያውያን_ታሪክ_ነው‼️
https://www.facebook.com/share/18PEDeEYuQ/
04/06/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra