️ ንስር አማራ🦅


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


የተቀደሰን ነገር በእግሩ ለሚረግጥ ፥ተመልሶም ያጎረሰውን እጅ ለሚናከስ ርኩስ መጫወቻ የማይሆን የነቃ ማህበረሰብ እስክንፈጥር ድረስ ብዕራችን አይነጥፍም።
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፥ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ።
💚💛❤️
እኛን በውስጥ ለማናገር @NISIREamhra2
@NISIREamhraa_bot 👈 ይችን አድራሻ ይጠቀሙ🦅
ንስር አማራ🦅
#የግፉአን_ድምፅ
t.me/NISIREamhra

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


🔥#ናደው_ክፈለ_ጦር‼️

የአገዛዙን ተልዕኮ ለለማስፈፀም“
#የሰላም_ካውንስል” በሚል ተመልምለው ወደ አዲስ አበባ  በመጓዝ ላይ የነበሩ ቁጥራቸው ከ30 በላይ የሚሆኑ ከሰሜን ሸዋ በጉዞ ላይ የነበሩ ተወካዮች በአማራ ፋኖ በሸዋ በናደው ክፍለጦር ፋኖዎች ተይዘው ተወስደዋል።

#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

05/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥#ሰበር_ዜና‼️
#ቦካክሳ_ከተማን_በፋኖ_ተያዘች‼️

የአማራ ፋኖ በወሎ /ቤተ-አማሓራ/ የምስራቅ አማራ ኮር 1 በአርበኛ እንድሪስ ጉደሌ የሚመራው  ባለሽርጡ ክፍለጦር እና ልጅ እያሱ ኮር ራስ  አሊ ክፍለ ጦር 1ኛ ሻለቃ የደቡብ ወሎ ዞን ቦከክሳ ከተማን ታላቅ ጀብድ በመፈፀም ከወራሪውና ከዘራፊው ስርዓት ነፃ በማውጣት ተቆጣጠሩ፡፡

በተደረገው ተጋድሎ የስርዓቱ ዙፋን ጠባቂ  ሰራዊት እንዲሁም ሆድ አደር  ሚሊሻና አድማ ብተና ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል፡፡

በዚህም ከሞት የተረፈው የዙፋን ጠባቂው ሰራዊት ከቦከክሳ ወደ ቢስቲማ እየፈረጠጠ ይገኛል፡፡  

በዛሬው የህልውና ተጋድሎ 18 የዙፋን ጠባቂው ኃይል እስከወዲያኛው ሲደመሰስ 10 የሚሆነውን ኃይል ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል፡፡ በዚህም ተጋድሎ  1500 የክላሽ ተተኳሽ እስከ ነፍስ ወከፍ መሳሪያ መመረክ ተችሏል።

የጀግኖቹን በትር መቋቋም ያቃተዉ የባንዳ ጥርቅም የግለሰብን ሀብትና ንብረት እየዘረፈ፣ እያወደመ እና የዘወትር ልምዱ የሆነዉን በንፁሀን  ላይ በርካታ ግፎችን እየፈፀመ፣ የግለስብ ቤቶችን እያቃጠለ ፈርጥጧል፡፡

ይህን አመርቂ ድል እንድንጎናፀፍ ያደረገን አስቻይ ሁኔታ ደግሞ በቅርቡ የተመሰረተው የአማራ ፋኖ በወሎ /ቤተ-አማሓራ/ አንድነት ነው፡፡ ይሄን የሰሩና ይህ እንዲሆን ለተጉ የድርጅታችን አመራሮች ከልብ እናመሰግናለን።

"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"

ፋኖ መምህር መሀመድ ሞገስ የአማራ ፋኖ በወሎ /ቤተ-አማሓራ/ የምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ

©የአማራ ፋኖ በወሎ/ቤተ-አማሓራ/

#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

05/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥ደንደገብ_ባሶሊበን‼️‼️

ዛሬ በ05/06/2017ዓ/ም የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ከጥዋቱ 1:00 ከበባ በማድርግ በሶሊበን ወረዳ በደንደገብ ቀበሌ ልዮ ስሙ ከብዳም ጎጥ ከአቶ ገድፈውን ቤት ከ70 በላይ ኩንታል ስንዴ ጭኖ ወስዷል:: አቶ ገደፍው የባሶ ሊበን ወረዳ የደንደገብ ቀበሌ ጊዜያዊ አስተዳደር ሲሆን ከትግል ማንም አያቆመኝም በማለት የአማራ ፋኖ በጎጃም የሀሐዲስ አለማሁ ክ/ጦር የአብራጅት ብርጌድ ጋር በመሆን ስርዓቱን እታገላለሁ ብሏል:: ከጠላት ያበራችሁ በተለይ ሚሊሻ አዳም ብተና እና ፓሊስ የፋኖን በትር መቋቋሞ ሲያቅታችሁ ዝራፊያ የማያወጣ እንደሆነ ብትረድ ጥሩ መሆኑን እያሳወቅን አደብ ያዙ እንላለን::ለፈፀማችሁት አስነዋሪ ተግባር ነገ እንጠያየቃለን!


©አብራጅት ብርጌድ!!!!


#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

05/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥አርበኛ ቃለአብ ወርቅዬ‼️

አርበኛ ቃለአብ ወርቅየ ይባላል።አማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አምሓራ) ምዕራብ ወሎ ኮር አምሓራ ሣይንት መቅደላ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ነው።

ጥንቅቅ ያለ ምሁር፣ እንደ ሼህ ሼረፈድን ያለ ቁጥብ ተናጋሪ፣ እንደ መምህር አካለወልድ አሰላሳይ እና እንደ ንጉሥ ሚካኤል ቆፍጣና እንዲሁም ስሩፍ ጀግና ነው።

በፋኖ ትግል ውስጥ በፖለቲካውና በኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ከሚገኙ ጀግኖች መካከል አንዱ የምዕራብ ወሎ ክስተት የሆነው አርበኛ ቃለአብ ነው።
ድል ለአንተና ለጓዶችህ!
ድል ለአማራ ሕዝብ!

© መረብ ሚድያ


#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

05/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥#መረጃ‼️

  የአፋጎ 5ኛ ክ/ጦር ደጃች አስቦ ቡሬ ዳሞት ብርጌድ አሳምነው ሻለቃን ጠላትን በቅጥ በቅጥ ስተረረገው ውላለች።በዚህም ልዩ ስሙ አባጌ የምትባል የገጠር ቀበሌ ከጠላት ጋር ሲፋለሙ የዋሉ ሲሆን በዚህ ውጊያም 7 በላይ ሙት እና ቁጥሩ ያልታወቀ ቁስለኛ ይዞ ወደ መጣበት ተመልሷል ሲሉ የሻለቃዋ ዘመቻ መሪ መቶ አለቃ አማኑኤል ገልፀውልናል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ጠ*ላት ከቤት በማውጣት ንፁሀንን እረ**ሽኖ ያገኘውን  እየተደባደበ ተመልሷል።

     አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዳስ ተስፋ!!
©የአፋጎ 5ኛ ክ/ጦር የሚዲያ ባለሙያ ፋኖ ዮሴፍ ሀረገወይን

#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

05/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥"ጠላት በድንጋ ክላሹን ተማርኳል"‼️

በመርጡለ ማርያም ከተማ  የመሸገውን የአገዛዙን  ሰራዊት ምንጣፍ በሚጎትቱ ፖሊስና ሚኒሻዎች ላይ የእነብሴ ሳር ምድር ወጣቶች በድንጋይ ጭንቅላታቸውን ፈንክተው ክላሻቸውን ማርከው የአባይ ሸለቆ ብርጌድን ተቀላቅለዋል።

የህዝባቸውን የጅምላ እስር  በአይናቸው የተመለከቱት ወጣቶቹ የመርጡለ ማርያም ከተማ ወጣቶችን፣ሴቶችን፣ ነጋዴዎች፣የመንግስት ሰራተኞችና የፋኖ ቤተሰቦችን ሲያሳድዱ ሲያንገላቱ በነበሩት ባየ በሚባል ማኒሻ ፣ውቡ በሚባል ፖሊስ ላይ እርምጃ ወስደውባቸዋል።

የገጠሩን ትግል ከከተማው ማህበረሰብ ጋር በማቀናጀት አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን የአባይ ሸለቆ ብርጌድ በመረጃው አክሎ ገልጿል።

#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

05/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥#ዝክረ_ታሪክ‼️
የአጼ ቴዎድሮስ አንድ መቶ ሰባኛ (170ኛ) ዓመት የንግሥና መታሰቢያ‼️
****
ከአንድ መቶ ሰባ (170) ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ እለት ታሪክን የኋሊት

«ማማው ደብረ ታቦር ታላቁ ታላቁ
አይታጠፍ ቃሉ አይፈታም ትጥቁ»

ደጃዝማች ካሣ ኃይሉ የግዛት ባላባቶችን በጦርነት አሸንፈው ‹‹ዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ›› ተብለው የነገሱት ከዛሬ አንድ መቶ ሰባ (170) ዓመታት በፊት የካቲት አምሥት (5) ቀን ሺህ ስምንት መቶ አርባ ሰባት (1847) ዓመተምህረት ነበር፡፡

ደጃዝማች ካሣ ኃይሉ በሺህ ስምንት መቶ አርባ አምሥት (1845) ዓመተምህረት የጎጃሙን ባላባት ደጃዝማች ጎሹ ዘውዴን ‹‹ጉራምባ›› ላይ እንዲሁም በጎንደር ቤተ-መንግሥት ንጉሥ አንጋሽና ሻሪ የነበሩትን ራስ አሊ (የወቅቱ ባላባቶች ሁሉ አለቃን) ‹‹አይሻል›› ላይ ካሸነፉ በኋላ ንጉሥ መሆናቸው እንደማይቀር እየታወቀ መጣ፡፡

የካቲት ሦስት (3) ቀን ሺህ ስምንት መቶ አርባ ሰባት (1847) ዓመተምህረት የስሜንና የትግራይ ገዢ የነበሩት ደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያምን ‹‹ቧሂት›› ላይ ድል ካደረጉ ከሁለት ቀናት በኋላ (የካቲት አምሥት (5) ቀን ሺህ ስምንት መቶ አርባ ሰባት (1847) ዓመተምህረት) ደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያም ሊነግሱባት አስጊጠው ባሰሯት ደረስጌ ማርያም ቤተ-ክርስቲያን እጨጌው በግራ ጳጳሱ በቀኝ በኩል ተቀምጠው መጽሐፈ ተክሊል እየተነበበ በጳጳሱ በአቡነ ሰላማ እጅ ተቀብተው ‹‹ዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ›› ተብለው የታላቋ ኢትዮጵያ ንጉስ ነገስት ሆኑ።

#የኋላው_ከሌለ_የለም_የፊቱ‼️
#ይህ_የኛ_የኢትዮጵያውያን_ታሪክ_ነው‼️

05/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥#ሸዋ_መከረ_ሀገር_ጠነከረ‼️

ሸዋ ባላመጠ ይውጣል ባመቱ
መገዘዝ ተራራ እመጓ ነው ልቡ ጥይት በጀበርና ዝናር ተንተርሶ
ሸዋ ሰው ይሰራል እንደ እግዜር አፍርሶ...‼️

የነገስታቱ ልጆች በአንድነት እየመጡ ነው....‼️

#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

05/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥ዐማራ በቀላሉ የማይታይ ረቀቂ ሕዝብ ነው‼️

"ጣሊያን ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ለመያዝ በድጋሜ የወረራ ሙከራ ባደረገበት በዚያ በድሮው ዘመን ወይም ወቅት በመሠረታዊነት ይዞት የመጣው የውጊያ ሥልት
#ዐማራን ቀድሞ #ማጥፋት ሲሆን ለዚህም ይረዳ ዘንድ ዐማራን በአካል አገኘኸውም አላገኘኸውም ዝም ብለህ ያለመታከት ዙሪያ ገባውን መተኮስ ያስፈልጋል ምክንያቱም ዐማራ መምጫው አይታወቅም፣ ከዚያ ነው ስትለው ከዚህ ነው፣ እርግጠኛ መሆን አትችልም፣ዐማራ አይታይም የሚል ነበር፡፡ ጣሊያን እንደፈራውም አልቀረ ዓላማውን ሳያሳካ ድባቅ ተመትቶ ወደ መጣበት ተመልሷል፡፡

የኛዎቹ የሀገር ውስጥ ጣሊያኖችና ባንዳዎች ደግሞ ዐማራን እናጠፋለን ብለው ፕሮግራም ነድፈው፣ ፖሊሲ ቀርጸው፣ ሕግ አውጥተው፣ የጥላቻ መርዝ በገፍ አምርተው፣ ላለፉት አምሳ ዓመታት ያለ የሌለ ኃይላቸውን እየተጠቀሙ፣ የቻሉትን ሁሉ አድርገው ዐማራን ማጥፋት ይቅርና ከፊቱ መቆም እንኳ እንደማይቻል ሲያረጋግጡ ዐማራ የለም የሚል የጅልና የተሸናፊነት ልክ ዝቅ ሲሉና ወርደው ሲንከባለሉ አይተናል፣እያየንም ነው፡፡
አዎ እውነት ነው፡- ዐማራ ሊጠፋ ቀርቶ ጨርሶ ከፊቱ መቆም በራሱ በፍርሓት የሚያርድና የሚያስፈራ የረቀቀ ማንነት ያለው የቃልኪዳን ሕዝብ ነው፤ የዐማራ ሕዝብ በክፉ የሚያስቡት ሁሉ እንዲህ በቀላሉ ሊያዩትና ሊገነዘቡት የማይችሉት የረቀቀ መላክ ነው፡፡"

ዐማራ አሸናፊ ሊሆን የሚችለው በአንድነት ስንቆም ብቻ ነው።
ዐማራነት ተሸንፎ
👉አሸናፊ የሆነ ጎንደር
👉አሸናፊ የሆነ ሸዋ
👉አሸናፊ የሆነ ወሎ
👉አሸናፊ የሆነ ጎጃም ሊኖር አይችልም ፣ ለማሸነፍና ራስን ለማስከበር ያለው ብቸኛ አማራጭ በዐማራነት ቆመን መግጠም ብቻ ነው‼️
©🦅
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

04/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥ዝምተኛው ሸዋ ጠላትን እየተቀባበለ ወቃው‼️

የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክፍለጦር  ነበልባል ብርጌድ ታሪካዊ የሚባል ድል ተቀናጅቷል።

ከዛሬ አራት ቀን በፊት በወራዋ የካቲት መግቢያ በቀን 1/6/2017ዓ.ም ከሞጆ መስመር እሬሽን ጭኖ የመጣው ወንበዴው የአብይ የግል ሰራዊት ስመ መከላከያ በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ቦሎ ጊዮርጊስ መሽጎ የነበረውን አረመኔ ሰራዊት በአጃቢነት ቀንታ ወደ በረኸት ወረዳ በረሃውን አቋርጦ ከሰም ጅረቱን አልፎ ሲግበሰበስ ባለታሪኮቹ በሃምሳ አለቃ ፍቃዱ ጥላሁን ከልክሌ ዋና ጦር አዛዥነት የሚመሩት ከመብረቅ ብልጭታ የሚፈጥኑት ነበልባሎቹ ከሰም ድልድይን ጠላት እንደተሻገረ ገልደሚያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ግትልትሉን የአብይን ወታደር በፈፀሙበት መብረቃዊ ጥቃት ሰባቱን በጥቁር አስፓልት ከምድር ቀላቅለውት ጠላትን በማበራዬት ጀባ አሉት።

ነበልባሎቹ ያዋከቡትን የአብይ ግብስብስ ሰራዊት በመቶ አለቃ ይላቅ ብርሃነ ዋና ጦር አዛዥነት የሚመራው የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክፍለ ጦር ተስፋ ብርጌድ ሀይለማርያም ብርጌድ ነበልባል ብርጌድ በተናበበ መንገድ በየመንገዱ ደፈጣ በማድረግ ከአረርቲ ወደ በረኸት መተህ ብላ የሚጓዘውን አፋሽ ሰራዊት እየተቀባበሉ ለአራት ቀን ወንበዴው የሚተኩሰውን ከባድ መሳሪያ ዙ-23 ሞርተር ጀነራል መድፍ ቢኤም በገፍ ቢተኩስም የሸዋ ፈርጦቹ ጠላትን ያሠበበት ሳይደርስ በገፍ ሙትና ቁስለኛ አድርገውት ያበራዩት እንደሆነ እና ጠላት በደረሰበት ሽንፈት በበረኸት ወረዳ የንፁሃን ቤትና ንብረት አቃጥሎ የተረፈው የጠላት ሀይል ወደ አረርቲ ከተማ ፊቱን አዙሮ በዛሬው እለት4/6/2017ዓ.ም ሲፈረጥጥ የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክፍለ ጦር ነበልባል ብርጌድ በየቦታው በጣሉት ደፈጣ ከጠዋት ጀምረው የብርጌዱ ቃኚና መሃንዲስ ተወርዋሪ ፋኖች በበረኸት ወረዳ ቆስጤ ገብረኤል እና ምንታምር ቀበሌ መሀከል በከፈቱበት መብረቃዊ ጥቃት የአገዛዙ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሆኖ በደረሰበት ጥቃት ተደናግጦ በየአቅጣጫው ተበታትኖ ወደ ከሰም አስፓልት ተከትሎ ሲፈረጥጥ ከቆስጤ በታች ደፈጣ የያዙት ሌላኛዎቹ ቀጫጭኖቹ የነበልባል ፋኖ በመክት የሚመሩት ሺአለቃ ሁለት አንድ ሻንበል አገዛዙን የመሣሪያ ቃታቸውን በመፈልቀቅ ምላጫቸውን እየነካኩ ጠላትን እየቀነደሹ አስፓልቱን ሙሉ ሙትና ቁስለኛ አድረገውት  መስመር ሲለቁለት ተናባቢዎቹ በፍቅር የተሞሉት ነበልባሎች በፋኖ ቸሩ የሚመሩት ሺአለቃ አራት አንድ ጋንታ ከሰም ድልድይ በየመንገዱ ሲመቱ  ተርፈው ወደ አረርቲ ከተማተ የሚፈረጥጠውን የአብቹ ሰራዊት የጥይት ሀሩር በከሰም በረሃ አፈሰሱበትተ የአብቹ ሠራዊት በበረሃው ውሃ ውሃ እያለ በነበልባሎቹ ጥይት እየተጋተ ሙት በሙት ሆነው የተረፈው ወደ አረርቲ የፈረጠጠ መሆኑን የአማራ ፋኖ በሸዋተ ከሰም ክፍለ ጦር የነበልባል ብርጌድ ፋኖ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኢንጂነር ታደሠ ወንድሙ አሳውቀዋል።

    ድል ለአማራ ፋኖ!!!
  አዲስ ተስፋ !!!
አዲስ አዲስ ትውልድ!!!
  
ዘላለማዊ ክብር ስለነፃነት ለተሰው ሰማዕታት።

©የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክፍለ ጦር የነበልባል ብርጌድ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን
   
#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

04/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra




🔥#አዲስ_አበባ_መረጃ!

አዲስ አበባ ዛሬ አራት ቦታዎች ላይ የቦንብ ጥቃት ተፈፅሟል። በዚህ ጥቃት የደነገጠዉ አገዛዙ በመዲናዋ በርካታ ቦታዎች ላይ ፍትሻ ሲካሄድ እንደነበረ የንስር አማራ ምንጮች ገልፀዉልናል።


በዚህ የተደናገጠዉ የመዲናዋ ከተማ አስተዳደር ለስድስት ቀናት ያህል የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ ከልክሏል።

ከዛሬ የካቲት 04/2017 ዓ.ም ከዚህ ሰዓት ጀምሮ እስከ የካቲት 09/2017 ዓ.ም ድረስ በመዲናዋ በየትኛውም አካባቢ ሞተር ሳይክል ማሽከርከር የማይቻል መሆኑን ቢሮው ተናግሯል፡፡

#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

04/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra

11.3k 0 12 12 113

አስደሳች ዜና‼

ብአዴን አደራጅቶ፣መሣሪያ አስታጥቆ በማዕከላዊ ጎንደር ጭልጋ መተማ መስመር አሽከርካሪዎችንና ተሳፋሪዎችን እንዲዘርፉ፣እንዲያግቱና እንዲረሽኑ ተልዕኮ ተቀብለው እገታ፣ዝርፊያና ግድያ ሲፈጽሙ የነበሩ ቡድን ላይ በፋኖ የተጠና እርምጃ በመወሰዱ አብዛኛው የብአዴን ወንጀለኛ ቡድን ሲደመሰስ የቡድኑ መሪ በፋኖዎች ተይዟል።


#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

04/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥የእቴጌ ጣይቱ ብጡል መቶ ሰባተኛ (107ኛ) የሙት ዓመት መታሰቢያ‼️

#ዝክረ_ታሪክ

ከአንድ መቶ ሰባት (107) ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ እለት ታሪክን የኋሊት

በዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ጉልህ አስተዋጽኦ ካበረከቱት ነገሥታት  መካል አንዷ የሆኑት እቴጌ ጣይቱ ብጡል ኃይለማርያም ያረፉት ከዛሬ አንድ መቶ ሰባት (107) ዓመታት በፊት (የካቲት አራት (4) ቀን ሺህ ዘጠኝ መቶ አስር (1910) ዓመተምህረት) ነበር፡፡

ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ከታመሙ በኋላ ስልጣኑን በእጃቸው አስገብተው ፖለቲካውን ለመዘወር ያላመነቱት ብርቱዋ ሴት እቴጌ ጣይቱ ብጡል  ይህ ተግባራቸው ከሸዋ መኳንንት ጋር አጣላቸው እና ወደ እንጦጦ ማርያም ሄደው እንዲቀመጡ ተወሰነባቸው፡፡

በመጨረሻም ከአብዛኛዎቹ የባለቤታቸው የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ውሳኔዎች ጀርባ የነበሩትና አዲስ አበባን የመሰረቱት ብርቱዋ እመቤት እቴጌ ጣይቱ የካቲት አራት (4) ቀን ሺህ ዘጠኝ መቶ አስር (1910) ዓመተምህረት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

#የኋላው_ከሌለ_የለም_የፊቱ‼️
#ይህ_የኛ_የኢትዮጵያውያን_ታሪክ_ነው‼️

04/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥''ዘመቻ ፋኖ ሀምሳ አለቃ ሀይማኖት አፍወርቅ/ካይሮ''‼️

         እነማይ ወረዳ
     የካቲት 04/2017/ዓም

፨ የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ስር የሚገኜው ስመ ገናነው
#አባ ኮስትር ብርጌድ የካቲት 04/2017/ዓም ዘመቻ ፋኖ ሀምሳ አለቃ ሀይማኖት አፍወርቅ/ካይሮ በሚል በቢቸና ከተማና በእነማይ ወረዳ ማህበረ ብርሀን ቀበሌ፣ወይራ ቀበሌ እንዲሁም በእናረጅ እናውጋ ወረዳ ጠባሚት ቀበሌ ከባድ ውጊያ በማድረግ ድል በድል ሆኖል።

፨ የአርበኛው በላይ ዘለቀን የጦር ስም የያዘው አባ ኮስትር ብርጌድ በዛሬው እለት የካቲት 04/2017/ዓም የወንድማችን ፋኖ ሀምሳ አለቃ
#ሀይማኖት አፍወርቅ የትውልድ ቦታ ውቢቷ ቢቸና ከተማን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር በቢቸና ከተማ አስተዳደር ቢሮ፣ፖሊስ ጣቢያ ቢሮ፣ሚኒሻና አድማ ብተና ይጠቀምበት የነበር ካንፕ ላይ ባደረገው እልህ አስጨራሽ ውጊያ ከብርጌዱ ሻለቆች የተሰባሰበ ጥምር ሀይል፣የአባ ኮስትር ብርጌዱ ልዮ ኮማንዶ፣የብርጌዱ ፈጥኖ ደራሽ ሀይል እንዲሁም 2ኛ ሻለቃ በጋራ በመሆን በቢቸና ከተማ በርካታ የአገዛዙ ቅጥርኛ ሰራዊት እና ዘራፌ ሀይል ደምስሰዋል።

፨ አባ ኮስት ብርጌድ
#ዘመቻ ፋኖ ሀምሳ አለቃ ሀይማኖት አፍወርቅ/ካይሮ በሚል ባደረገው ውጊያ በቢቸና ከተማ ከተደመሰሱት ከአገዛዙ ቅጥርኛ የሚሻ አባላት የተረፉ #ባንዳ ባየ ለወየሁ እና #ባንዳ ለወየ ሰይድ የሚባሉ 2(ሁለት) የሚኒሻ አባላት ተማረከዋል ።

፨ አባ ኮስትር ብርጌድ በዛሬው እለት በአካሄደው ውጊያ በእነማይ ወረዳ ማህበረብርሀን ቀበሌ መሽጎ በሚገኜውን ሰው በላ ዘራፌ ሰራዊትን 1ኛ ጠቅል ሻለቃ በሁለት አቅጣጫ ስትገርፈው አድራለች።በእነማይ ወረዳ ወይራ ቀበሌ መሽጎ በሚገኜውን የብርሀኑ ጁላ ሰራዊትን 3ኛ ሻለቃ እና 5ኛ ኢንጅነር ተሾመ ሻለቃ ጠላትን ሲወቁት አርፍደዋል።በእናረጅ እናውጋ ወረዳ ጠባሚት ቀበሌ 4ኛ ሻለቃ ጠላትን ስታራግፈው አርፍዳለች።

፨ በሌላ የውጊያ መረጃ የካቲት 04/2017/ዓም የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ክፍለ ጦር ስር የሚገኜው ሶማ ብርጌድ አባ ኮስትር ብርጌድ እያካሄደ በነበርው ውጊያ ተጨማሪ የጠላት ሀይል ከደብረወርቅ ከተማ እንዳይሄድ በማድርግ በእናርጅ እናውጋ ወረዳ ተንጉማ ወፍና ቀበሌ ለይ ውጊያ አካሂዶል።ሶማ ብርጌድ በእናርጅ እናውጋ ወረዳ አጋምና የመጀመረያ ትምህርት ቤት የአገዛዙን የካቢኒ ቤተሰብና የአገዛዙ ቅጥርኛ የሚኒሻ እና ፖሊስ አባላት ቤተሰብ በመማር ማስተማር ላይ የነበሩ እንዲበተኑ አድርጓል።

፨ ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ስር የሚገኜው ዛንበራ ብርጌድ በደጀን ወረዳ ወረቅአምባ፣የናኛት እና ቆል ቀበሌ ውጊያዎችን ሲያካሂድ አርፍዶል።ዛንበራ ብርጌድ ባደረገው ውጊያ 10(አስር) የብርሀኑ ጁላ አራጅ ዘራፌ ሰራዊት የአገዛዙ ቅጥርኛ ሰራዊት እስከወዳኜው ሸኝቷል።በዚህ ውጊያ 8(ስምንት)የአገዛዙ አራጅ ዘራፌ ቅጥረኛ ሰራዊት ከባድና ቀላል ቁስለኛ ሆነዋል።

፨ ዛንበራ ብርጌድ በደጀን ወረዳ ፀደን አማሪት ቀበሌ ከሳምንታት በፌት ባደረገው ውጊያ ከባድ ቁሰለኛ ከነበሩት የአገዛዙ ቅጥረኛ የሚኒሻ አባላት በዛሬው እለት የካቲት 04/2017/ዓም መሞታቸው ተረጋግጦል።

፨ ዛንበራ ብርጌድ ከሚያስተዳድረው ደጀን ወረዳ ኩራር ቀበሌ አካባቢ የአገዛዙ ቅጥርኛ ሰራዊት አባል የነበር 1(አንድ) ሚኒሻ ገደል ላይ ገብቶ መቶ መገኜቱ ተረጋግጦል።

፨ የምንወድህ ወንድማችን ጓዳችን
#ፋኖ ሀምሳ አለቃ ሀይማኖት አፍወረቅ/ካይሮ መቸውም አንረሳህ አንተን የጀመረከውን ትግል ዳር እናደረሳለን እንወድሀለን😭😭😭

©ከአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ፋኖ ይበልጣል ጌጌ

#ዘመቻ ፋኖ ሀምሳ አለቃ ሀይማኖት አፍወርቅ/ካይሮ ይቀጥላል!!

አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ!ለአማራ ህዝብ!

#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

04/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra




🔥#ሟች_ከመሞቱ_በፊት #ፋኖ_ሌባው እንገናኝ ብሎ ነበረ😂‼️

ስለምንገናኝ ችግር የለውም ግምባር ግምባርህን እንልሃለን አላለም እግዞ ገንዘብ ግን የማያደርገው የለውም::
የባንዳ መጨረሻው ይሄ ነው‼

ዘላለም አለሰው ይባላል ቡሬ ዙርያ የደረቋ ፋኖ ነበር ኋላ ላይ ግን በክህደት ወደ ሚነሻ ተቀላቅሎ የቡሬንና የማንኩሳን አካባቢ ፋኖ ያሉበት ቦታ ድረስ መከላከያን እየመራ እየወሰደ እያስመታ በክህደት ስራውን ቀጠለ።በቲክቶክ እየወጣም በፋኖ ላይ መዛት መሳደብ ማንቋሸሽ ጀመረ።

መጨረሻም በአረንዛው ዳሞት ብርጌድ ቢተው ሻለቃ የማያዳግም እረምጃ ተወስዶበት እስከወዲያኛው ተሸኝቷል💪

#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

04/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra

13k 0 2 35 248

🔥#የጥንቃቄ_አስቸኮይ_መረጃ‼️


🔥#ብልፅግና ቡድን የበተናቸው መረጃ እና ደህንነቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️

ማቻከል ወረዳ አማኑኤል ከተማ ብልጽግና የበተናቸው 3 መረጃ የሚመርጁ ሆድ አደሮች ተይዘዋል ፣ለእያንዳንዳቸው 90,400 ብር ተከፍሏቸዋል።

ከጎጃም ከተለያዩ ቦታዎች በአፈሳ ተሰብስበው ጎንደር ተወስደው የሰለጠኑ 2,900 ሰላይ ባንዳወች ተበትነው ፋኖን እና የተለያዩ የነቁ አማራዎችን በመጠቆም እያስገደሉ ነው።

እነዚህ ሆድ አደር ግለሰቦች በአስቸኳይ በፍቃዳቸው እጃቸውን ለፋኖ እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። ሁሉም ፋኖ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የማቻከል የበላይ ዘለቀ ብርጌድ አሳስቧል ።

#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

04/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥የንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ አንድ መቶ ስምንተኛ (108ኛ) ዓመታት የንግሥና መታሰቢያ‼️

#ዝክረ_ታሪክ

ከአንድ መቶ ስምንት (108) ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ እለት ታሪክን የኋሊት

የታላቁ ንጉሥ ነገሥት ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ልጅ የሆኑት ወይዘሮ ዘውዲቱ ምኒልክ ‹‹ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ወለተ ለዳግማዊ ምኒልክ ስይምተ እግዚአብሔር›› ተብለው በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በሊቀ ጳጳሱ በአቡነ ማቴዎስ እጅ ቅብዐ መንግስት ተቀብተው የንግሥትነት ዘውድ የጫኑት ከዛሬ አንድ መቶ ስምንት (108) ዓመታት በፊት (የካቲት አራት (4) ቀን ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠኝ (1909) ዓመተምህረት) ነበር፡፡

በዚሁ ዕለትም የራስ መኮንን ወልደሚካኤል ልጅ የሆኑት ተፈሪ መኮንን ‹‹ራስ ተፈሪ›› ተብለው ታላቁን «የሰለሞን ኒሻን» ተሸልመው እና ለአልጋ ወራሽ የሚገባው ክብርና ስርዓተ-ፀሎት ተደርጎላቸው ‹‹ልዑል አልጋ ወራሽ ራስ ተፈሪ መኮንን›› ተብለው ተሰየሙ፡፡

ዘውዲቱ ምኒልክና ተፈሪ መኮንን የዳግማዊ ምኒልክ ዙፋን ወራሽ እንደሆኑ የታወቀው ልጅ ኢያሱ ሚካኤል መስከረም አስራ ሰባት (17) ቀን ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠኝ (1909) ዓመተምህረት ከዙፋኑ በተሻሩበት እለት ነበር፡፡

#የኋላው_ከሌለ_የለም_የፊቱ‼️
#ይህ_የኛ_የኢትዮጵያውያን_ታሪክ_ነው‼️

https://www.facebook.com/share/18PEDeEYuQ/

04/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra

Показано 20 последних публикаций.