🔥#ዝክረ_ታሪክ‼️
የአጼ ቴዎድሮስ አንድ መቶ ሰባኛ (170ኛ) ዓመት የንግሥና መታሰቢያ‼️
****
ከአንድ መቶ ሰባ (170) ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ እለት ታሪክን የኋሊት
«ማማው ደብረ ታቦር ታላቁ ታላቁ
አይታጠፍ ቃሉ አይፈታም ትጥቁ»
ደጃዝማች ካሣ ኃይሉ የግዛት ባላባቶችን በጦርነት አሸንፈው ‹‹ዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ›› ተብለው የነገሱት ከዛሬ አንድ መቶ ሰባ (170) ዓመታት በፊት የካቲት አምሥት (5) ቀን ሺህ ስምንት መቶ አርባ ሰባት (1847) ዓመተምህረት ነበር፡፡
ደጃዝማች ካሣ ኃይሉ በሺህ ስምንት መቶ አርባ አምሥት (1845) ዓመተምህረት የጎጃሙን ባላባት ደጃዝማች ጎሹ ዘውዴን ‹‹ጉራምባ›› ላይ እንዲሁም በጎንደር ቤተ-መንግሥት ንጉሥ አንጋሽና ሻሪ የነበሩትን ራስ አሊ (የወቅቱ ባላባቶች ሁሉ አለቃን) ‹‹አይሻል›› ላይ ካሸነፉ በኋላ ንጉሥ መሆናቸው እንደማይቀር እየታወቀ መጣ፡፡
የካቲት ሦስት (3) ቀን ሺህ ስምንት መቶ አርባ ሰባት (1847) ዓመተምህረት የስሜንና የትግራይ ገዢ የነበሩት ደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያምን ‹‹ቧሂት›› ላይ ድል ካደረጉ ከሁለት ቀናት በኋላ (የካቲት አምሥት (5) ቀን ሺህ ስምንት መቶ አርባ ሰባት (1847) ዓመተምህረት) ደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያም ሊነግሱባት አስጊጠው ባሰሯት ደረስጌ ማርያም ቤተ-ክርስቲያን እጨጌው በግራ ጳጳሱ በቀኝ በኩል ተቀምጠው መጽሐፈ ተክሊል እየተነበበ በጳጳሱ በአቡነ ሰላማ እጅ ተቀብተው ‹‹ዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ›› ተብለው የታላቋ ኢትዮጵያ ንጉስ ነገስት ሆኑ።
#የኋላው_ከሌለ_የለም_የፊቱ‼️
#ይህ_የኛ_የኢትዮጵያውያን_ታሪክ_ነው‼️
05/06/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra