🔥የዝያድባሬው አንበሳ ሜጨኛው ኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ💪
ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ከአባታቸው ከአቶ ሙሉነህ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አዛለች ጥሩነህ በምእራብ ጎጃም መርዐዊ ከተማ በ1944 አ/ም ተወለዱ ።
የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምሕርታችውን ካጠናቀቁ በኋላ እናት አገራችውን በውትድርና ለማገልገል በነበራቸው ፅኑ ፍላጎት በኢትዮጵያ አየር ኃይል በአውሮፕላን አብራሪነት ሙያ እ.ኤ.አ. በ1971 ዓም ተቀጠሩ ። በኢትዮጵያ አየር ኃይል የሚሰጠውን መሰረታዊ የወታደራዊ ስልጠና እና በሳብ ሳፋየር የመጀመሪያ ደረጃ በረራ ማሰልጠኛ አውሮፕላን የሚሰጠውን የበረራ ስልጠና በሚገባ በማጠናቀቅ ፤ በቀጣይ በቲ-28 ዲ አስመራ ፣ ቲ-33 ደብረ ዘይት እንዲሁም በአሜሪካን አገር ደግሞ ቲ- 39 እንዲሁም በቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት የሚግ - 21 ስልጠናዎችን የተከታተሉ ሲሆን በ1974 ዓም በአገራችን በተፈጠረው የርእዮተ ዓለም ለውጥ ምክንያት የኢትዮጵያ አየር ኃይል የታጠቃቸውን ሩሲያ ሰራሽ ጀቶች በአጭር ጊዜ ተምሮ በማጠናቀቅ የአየር ኃይሉን ብቃት ወደ ነበረበት በመመለስ ለውጊያ ዝግጁ ከሆኑት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች መካከል ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ አንዱ ነበሩ ።
ዕብሪተኛውና ተስፋፊው የዚያድ ባሬ ጦር ያለ የሌለ ኃይሉን በማረባረብ የቀብሪ ዳሃር ከተማን ለመቆጣጠር የክብር ዘቡን ባንቀሳቀሰ ጊዜ የወራሪውን ኃይል ለመደምሰስ ግዳጅ በመቀበል የሶማሊያን የወራሪ ኃይል አከርካሪ ከሰበሩት የአየር ላይ ጀግኖች መካከል አንዱ ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ነበሩ ። በዚሁ ግንባር በሚግ -23 ተዋጊ አውሮፕላን ወደ ምድር ዝቅ ብለው በመብረር የተመረጡ ኢላማዎችን በማደባየት ላይ እንዳሉ ከጠላት በተተኮሰ የአየር መቃወሚያ ያበሩት የነበረው አውሮፕላን ሲመታ እሳቸው በጃንጥላ በመዝለል ተርፈው በምድር በነበረው የወገን ሰራዊት እና በበራሪ ጓዶቻቸው ከፍተኛ ጥረት እንዲሁም በነበራቸው ወታደራዊ ብቃት ከጠላት አምልጠው የጦር ሜዳ ጀብዱ ሜዳይ ተሸላሚ ለመሆን በቅተዋል ።
ኮ/ል ታደሰ በሰሜን ግንባር በተደረገው ከፍተኛ ተጋድሎ አገራቸው የጠየቀቻቸውን መስዋእትነት ሁሉ ለመክፈል በተለያየ አውደ ውጊያ ላይ በመሰለፍ ግዳጃቸውን የተወጡ ጀግና ነበሩ ። ከውጊያ ባሻገርም ብቃት ያላቸው ተዋጊ አብራሪዎችን ያፈሩ ስመጥር የበረራ አስተማሪም በመሆን ለትውልድ የሚተላለፍ ችሎታቸውን ለግሰዋል ።
በ1983 ዓም የህወሃት ዘረኛ ቡድን መላው አገሪቷን በተቆጣጠረ ጊዜ ኰ/ል ታደሰ ሙሉነህ እንደሌሎች የሰራዊቱ አባላት ሁሉ ወደ ባዕድ አገር ተሰደው የቆዩ ሲሆን ኤርትራ የራሷን አየር ኃይል ስታቋቁም ለ18 አመታት በበረራ አስተማሪነት አገልግለዋል ።
በተጨማሪም የህውሃት ስርዓት አገራችን ላይ እያደረሰ ያለውን የጥፋት ተልዕኰ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ የአርበኞች ግንባርን በመቀላቀል ከ1993 ዓም ጀምሮ ግንባሩን የመሩ ሲሆን በኋላ ግን በእነ ዶክተር ብርሀኑ ነጋ ሴራ ከሻቢያ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት በኤርትራ መንግስት በቁጥጥር ስር ውለው እስከ ቅርብ ጊዜ ለስምንት አመታት በግዞት እስር ላይ በመቆየታቸው ሳቢያ ጤናቸው በመታወኩና ቀስ በቀስም ለህይወታቸው አደገኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ ከእስር ተለቀው ለሚወዷት እናት አገራቸው አፈር በቅተዋል ። ይሁን እንጂ የጤናቸው ጉዳይ በሚያሳዝን ሁኔታ እያሽቆለቆለ የመጣ ሲሆን በአገር ውስጥና በህንድ አገር ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ጥር 27 ቀን 2011 ዓም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል ።
ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ አገር ወዳድ ፣ ላመኑበት ነገር ፈጽሞ ወደኋላ የማይሉ ፣ በስራቸው ትጉህ ፣ እጅግ ትሁትና ሰውን አክባሪ የነበሩ ሲሆን ባለትዳር እና የስድስት ልጆች አባት ነበሩ ።
የቀብራቸውም ስነ- ስርዐት በትውልድ ስፍራቸው ምእራብ ጎጃም መርዓዊ ቅ/ማሪያም ቤ/ክርስቲያ ጓደኞቻቸው ወዳጅ ዘመዶቻቸውና እና በርካታ የቀድሞው የኢትዮጵያ አገር መከላከያና የፖሊስ ሰራዊት አባላት በተገኙበት በታላቅ ስነ - ስርዐት ተፈጽሟል ።
ኮ/ሎ ታደሰ ሙሉነህ ! ሞት ለሰው ልጆች የማይቀር እዳ ነውና ፤ ትውልድ የማይረሳው አኩሪ ጀግንነትና በጐ ስራህ ምንግዜም ሲታወስ ይኖራል ።
ለዚህም የጀግኖቿን ውለታ የማትረሳው፣ ጥንትም ጀግና የማይነጥፍባት የጎጃሟ ፈርጥ መራዊ ከተማ መሰናዶ ትምህርት ቤቷን "ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ 2ኛ ደረጃ መሰናዶ ት/ቤት" እንዲሁም የአማራ ፋኖ በጎጃም የሜጫውን ወኪል "ኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ" በጀግናው ስም ሰይማለታለች !
#ታሪክ ጠባቂ ፣ ታሪክ ሰሪ ነን‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
26/06/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra