“በሪፎሙ በወንጀል መከላከልም ሆነ በወንጀል ምርመራ ብቁ ሆኖ ለመገኘት እንደተቋም ትላልቅ ሥራዎችን ስንሰራ ቆይተን አስደናቂ ውጤቶችን አስመዝግበናል።” ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግሥቴ ::
ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግሥቴ በሪፎርሙ በወንጀል መከላከልም ሆነ በወንጀል ምርመራ ብቁ ሆኖ ለመገኘት እንደተቋም ትላልቅ ሥራዎችን ስንሰራ ቆይተን አስደናቂ ውጤቶችን አስመዝግበናል ያሉት የፌደራል፣ የክልልና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ኃላፊዎች መደበኛ ጉበዔን በድምቀት በከፈቱበት ወቅት ነው።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግሥቴ በ19ኛው የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽነሮች ጉባኤ ሀገርን በጋራ ለማፅናት እና የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ሰነድ በተፈራረም ነው መሠረት በቀጣይ በቅንጅትና በመደጋገፍ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሰብአዊ መብት አያያዝን በማጠናከር ሀገራዊ ራዕይን ለማሳከት ሁሉም መረባረብ አለበት ብለዋል።
ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል አያይዘውም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሕገ-መንግሥቱንና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን እንዲሁም ሌሎች ሕጎችን በማክበርና በማስከበር ሕብረተሰቡን በወንጀል መከላከልና ምርመራ በማሳተፍ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት እየጠበቀ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በጉባኤው ማንኛውም የወንጀል ተጠርጣሪ የትኛውም ክልል ተደብቆ ማምለጥ በማይችልበት ሁኔታ ላይ በመወያየት እና በአፈፃፀሙ ላይ ስምምነት ላይ በመድረስ ሀገራችን በግብርና፤ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም እና በቴክኖሎጂ የጀመረችውን የኢኮኖሚ ሪፎርም ግቡን እንዲመታ የፀጥታ ዘርፉ አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ በወንጀል በመከላከልም ሆነ በወንጀል ምርመራ አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገብ ይኖርብናል ብለዋል።
ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ከጉባኤው ተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ ሰጥተው በማጠቃለያቸው የፖሊስ ስታንዳርድ ማስጠበቅ የክልል ፖሊስ ስልጣንን መጋፋት እንዳልሆነ አብራርተው፤ የተወሰደው ልምድና ተሞክሮ በቀጣይ ለሚሠሩ የምርመራ ሥራዎች መጠናከር ከፍተኛ አበርክቶ ስላለው ከዚህ በኋላ በምርመራ ሥራ ረገድ ጉራማይሌ አሠራር እንደማይኖር ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 720/2004 አንቀጽ 18 ንዑስ አንቀጽ 3 ሥር ከተዘረዘሩት የፌደራል፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደር ፖሊስ ግንኙነቶች አንዱ የወንጀል ምርመራ ሥራዎችን በቅንጅትና በመደጋገፍ የሚሠሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሥልጣንና ተግባር እንደተደነገገ በውይይቱ ተነስቷል።
በባለፉት ዓመታት በአንዳንድ አካባቢዎች ሲስተዋሉ የነበሩ ግጭቶችና የሽብር ወንጀሎች፣ ከባድና ውስብስብ የሙስና እና የኢኮኖሚ ወንጀሎች፣ የተደራጁና ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ምርመራ ላይ ባስመዘገብነው ውጤት የፌደራልና የክልል መንግሥታት የሥራ ኃላፊዎች፣ የፀጥታና የደኅንነት አካላት፣ ባለድርሻ እና አጋር አካላት እንዲሁም ከፖሊስ ጎን ተሰልፎ የዜግነት ኃላፊነቱን እየተወጣ ለሚገኘው ኅብረተሰብ ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግሥቴ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።