" በአደጋው የሦስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድማል " - ማይጨው ችፑድ ፋብሪካ
ዛሬ ሰኞ መጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ/ም ጠዋት በትግራይ ደቡባዊ ዞን ማይጨው ከተማ በሚገኘው ችፑድ ፋብሪካ ባጋጠመ የእሳት አደጋ የሦስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።
የፋብሪካው የህዝብ ግንኙነት ክፍል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ በሰጠው ቃል የእሳት ቃጠሎ አደጋው የተነሳው በፋብሪካው የምርት ክፍል መሆኑን ጠቁሟል።
" የአደጋው መነሻ ምክንያት ገና አልታወቀም " ሲልም ገልጿል።
ይህን መረጃ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ የሦስት ሰዎች ህይወት አልፏል። አንድ ሰው ደግሞ በሞት አፋፍ ላይ ይገኛል ተብሏል።
ሌሎች አካላዊ ጉዳት የደረሰባቸውም ወደ ጤና ማእከላት ተወስደዋል።
የተነሳው ቃጠሎ በፋብሪካው ማሽነሪዎችና ህንፃ ላይ በሚሊዮን ብሮች የሚገመት ወድመት መድረሱ ነው የተገለፀው።
ዛሬ ረፋድ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎው በሰው ሃይልና በማሽነሪ ተደግፎ በቁጥጥር ስር ውሏል።