“ኢትዮጰያን በ2026 የአለም የንግድ ድርጅት ሙሉ አባል ለማድረግ እየሰራን ነው” -የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር
ኢትዮጵያ 5ኛውን የአለም የንግድ ድርጅት የስራ ቡድን ስብሰባ በበቂ ዝግጅት ተሳትፋ በስኬት ማጠናቀቋን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ትላንት መጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
በመግለጫቸውም በቅርቡ ጄነቭ በተካሄደው 5ኛው የሀገራችን የአለም ንግድ ድርጅት የስራ ቡድን ስብሰባ በስኬት መጠናቀቁንና በቀጣይ በሚካሄደው 6ኛው የአለም ንግድ ድርጅት የስራ ቡድን ስብሰባ ኢትዮጵያን ሙሉ አባል ሆና ድርጅቱን መቀላቀል የሚያስችላትን ስራ መሰራቱን አስታውቀዋል፡፡
በካሜሩን በ2026 በሚካሄደው 14ኛው የአለም ንግድ ሚኒስትሮች ስብሰባ ኢትዮጵያ የአለም የንግድ ድርጅት አባል መሆኗን የሚያበስር ዜና የምንሰማበት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በ5ኛው የሀገራችን የአለም ንግድ ድርጅት የስራ ቡድን ስብሰባ በተለያዩ የድርድር ነጥቦች ዙሪያ ከ110 በላይ ጥያቄዎች ከተለያዩ ሀገራት ቀርበው ምላሽ የተሰጣቸው መሆኑንና የልኡካን ቡድናቸው በበቂ ዝግጅት ውጤታማ ድርድር ያካሄደ መሆኑን ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡
ሚኒስትሩ በትላንትናው እለት መግለጫቸው ኢትዮጵያ ከ17 ሀገራት መካከል ከ12ት ሃገራት ጋር የሁለትዮሽ ድርድር የተካሄደ መሆኑን አንስተው በተለይም ከአሜሪካና ከአውሮፓ ህብረት ጋር ውጤታ ድርድር መደረጉን ጠቁመዋል፡፡
የአለም ባንክ እና 19 ሀገራት ኢትዮጵያ ድርጅቱን እንድትቀላቀል ጠንካራ ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቁመው "ከተለመደው እና ከሚጠበቀው በላይ ድጋፍ" አግኝተናል ብለዋል።ከአለም የንግድ ድርጅት ጋር የሚካሄደው ቀጣዩ ድርድር በተያዘው አመት 2017 በሐምሌ ወረ መሆኑን አስታውቀዋል።