በስነ ምግባር ጉደለት ከሚሰራበት ተቋም የተሰናበተው ግለሰብ የመስሪያ ቤቱን ስም በመጠቀም የተቋሙ ሰራተኛ መስሎ የማታለል ወንጀል ሲፈፅም በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን ፖሊስ ገለፀ።
***
ከዚህ ቀደም የፌዴራል ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሰራተኛ የነበረ እና በተለያየ የስነ ምግባር ጉደለት ከተቋሙ የተሰናበተ ታረቀኝ ክፍሌ የተባለ ተጠርጣሪ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኛ እንደሆነ በማስመሰል የተለያዩ ግለሰቦች ያሉበት የመንግስት የኪራይ ቤቶች ላይ እየተዘዋወረ የኪራይ ቤቶቹ ታፔላ ወደ ዲጂታል እየተቀየሩ ነው በማለት በተቋሙ ስም የተዘጋጁ ቅፆች የያዘ በማስመሰል እና ሀሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም ታፔላውን ወደ ዲጂታል ማስቀየር አለባችሁ በማለት ከሁለት የግል ተበዳዮች ከእያንዳንዳቸው 1ሺህ 7መቶ ብር የተቀበለ ሲሆን በግል ተበዳዮች ጥቆማ ሰጭነት በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
የማታለል ወንጀሉ የተፈፀመው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ጎጃም በረንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኙ የመንግስት ኪራይ ቤቶች ውስጥ ባሉ ነጋዴዎች ላይ ነው።
አንዳንድ የሥነ ምግባር ጉድለት ያለባቸው ግለሰቦች የግል ጥቅማቸውን በማሰብ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የተለያዩ ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ሊኖሩ እንደሚችሉ በመገንዘብ ለመሰል የወንጀል ድርጊት ህብረተሰቡ እንዳይዳረግ በማንኛውም ጉዳይ ለሚጠይቀውና ለሚጠየቀው አገልግሎት ህጋዊነቱን ከማረጋገጥ ባሻገር አስፈላጊውን መረጃና ማስረጃ መጠየቅ እንደሚያስፈልግ ፖሊስ አሳሰቧል ።
*