" ' የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን ' በሚል የተሰጠው መግለጫ የሰራዊቱ እና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሃሳብ እና ውሳኔ እንዳልሆነ ለኢትዮጵያ መንግስት እናሳውቃለን " - የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው መግለጫ ተፈፃሚነት እንዳይኖረው (null and void እንዲሆን) ወስኗል።
" በሰራዊቱ የኮር አመራር የሚል አደረጃጀት እውቅና የለውም " ሲል የወሰነው ካቢነኔው " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል ጥር 14/2017 ዓ.ም የተሰጠውን መግለጫ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጎታል።
ካቢኔው ዛሬ ቅዳሜ ጥር 17/2017 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ ፤ "የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው መግለጫ ፦
- ለአንድ ቡድን የወገነ
- መንግስት የሚፈርስ
- ሰራዊት የሚበትን
- የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የሚያፈርስ እና መሰረታዊ ችግር ያለው በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲታረም እና ታች ወርዶ እንዳይተገበር ወስኗል።
" የተሰጠው መግለጫ ከሰራዊት ተልእኮ ያፈነገጠ ፣ ተቋማዊ አሰራር የጣሰ " ነው "ሲል የገለፀው ካቢኔው ፥ " ' አመራር ነኝ ' በሚል በዚህ ሁኔታ ተሰብስቦ ውሳኔ ለማሳለፍ የሚያስችል ስልጣን የለውም " ብሏል።
" ' የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን ' በሚል በተሰጠው መግለጫ መንግስታዊ ማስተካከያ እንዲደረግ አስመልክቶ የቀረበው አቋም የአንዱ ቡድን የስልጣን ጥማት ለማርካት ሲባል የፕሪቶሪያ ውል የሚያፈርስ ሃላፊነት የጎደለው ውሳኔ ነው " አደገኛ ነው ' ሲል ገልጾ በአስቸኳይ የሚታረምበት አቅጣጫ ማስቀመጡን አሳውቋል።
ካቢኔው ባወጣው የውሳኔ መግለጫ ለኢትዮጵያ መንግስት ባስተላለፈው መልእክት " ' የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን ' በሚል በተሰጠው መግለጫ የሰራዊቱ እና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሃሳብ እና ውሳኔ አይደለም በመሆኑም ወድቅ አድርጎታል ፤ ሰራዊቱ እና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አሁንም ለፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተገዢ በመሆን ጅምር ሰላሙ እንዲጎለብት የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ተከብሮ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የጀመረውን ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል " ብሏል።
" የትግራይ ህዝብና ጊዚያዊ አስተዳደሩ ፍላጎት ሰላም ነው " ሲል ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ መልእክት ያስተላለፈው ካቢኔው ፤ " የፕሪቶሪያ የሰላም ውል በአፈፃፀም ብዙ ችግሮች ቢኖሩትም በስምምነቱ አፈፃፀም የሚነሱ ችግሮች በሰላማዊ እና ፓለቲካዊ ትግል እንዲመለሱ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ የተሟላ ድጋፍ እንዲያደርግ " ሲል ጥሪ አስተላልፏል።