በትግራይ ክልል ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች እስካሁን ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመለሱም ተባለ
በትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ የወደሙ እና ወደ ሥራ ያልተመለሱ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ስዩም ሀጎስ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ምዕራብ ትግራይ በሌሎች ኃይሎች ቁጥጥር ሥር በመሆኑ ትምህርት ለማስጀመር እንዳልተቻለ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ እንደ እቅድ ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ ከታሰበው 2 ነጥብ 45 ሚሊየን ተማሪዎች ውስጥ እስካሁን ወደ ትምህርት መመለስ የተቻለው 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ያክል ተማሪዎችን ብቻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከነዚህም ውስጥ ባለው ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡"በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ቢሞከርም፤ ባለው የምግብ አቅርቦት ችግር እና በሌሎችም ተደራራቢ ጫናዎች ምክንያት ታዳጊዎቹ ለልመና እና ለቀን ሥራ እየተዳረጉ በመሆኑ ጥረቱን አስቸጋሪ አድርጎታል" ብለዋል፡፡
"በመጠለያ ውስጥ ያለው የእርዳታ አቅርቦት የሚፈለገውን ያህል ባለመሆኑ ወላጆቻቸውም ሰርተው ልጆቻቸውን ማስተማር የሚችሉበት ሁኔታ ላይ ባለመሆናቸው፤ በተለይም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕፃናት ምግብ ለማግኘት ወደ ልመና ይሰማራሉ" ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ግጭት ብሎም ሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ አደጋ በተከሰተባቸው ክልሎች በርካታ ሕጻናት እና ወጣቶች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸው የሚገለጽ ሲሆን፤ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚህ ዓመት እንደ ሀገር ከ7 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።