የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አስመረቀ ።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ ዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል በላይ ስዩም ፣ ሃገር ታፍራና ተከብራ በነፃነት የምትቆመው የሃገርን ክብርና የነፃነትን ዋጋ የሚያውቅ ሃገር ወዳድ ሰራዊት ማፍራትና ማብቃት ስትችል ነው ብለዋል።
በመሆኑም ተቋማችን መከላከያ እንደተቋም በጠንካራ መሠረት ላይ ለመገንባት መጠነ ሰፊ የፕሮፌሽናል ሰራዊት ግንባታና ሪፎርም ስራዎችን እየሰራ ጎን ለጎንም ህዝብና መንግስት የሰጡትን ተልዕኮ በአኩሪ ተጋድሎ በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በተጨማሪም መከላከያ የውጭና የውስጥ ፅንፈኛ እና አሸባሪ ኃይሎችን በመዋጋት ህልማቸው እንዳይሳካ በማድረግ ሀገራችን እና ህዝባችንን በመታደግ ተግባር ላይ እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡
ተመራቂዎች በስልጠና ቆይታችሁ በመሰረታዊ ውትድርና ስልጠና ያገኛችሁትን የወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ እንዲሁም እውቀት፣ ችሎታና ክህሎት በመጠቀም በምትመደቡበት የሰራዊታችን ክፍሎች የተልዕኮ አፈፃፀም ብቃት በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ኃላፊነት እንደሚጠበቅባችሁ አውቃችሁ በታላቅ ሀገራዊ ስሜት መንቀሳቀስ እና ከነባሩ ሠራዊት ጋር በመሆን ልምድና ተሞክሮን ቀስማችሁ ለሠላም መሥራት አለባችሁ ሲሉ አሳስበዋል።