ከሁሉ በፊት የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን!
ዛሬ በለነገዋ የሴቶች የተሃድሶ እና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ 2ኛ ዙር ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ 380 ሰልጣኞችን አስመርቀን ወደ ስራ አሰማርተናል።
ከአስከፊ ህይወት ወጥታችሁ ስልጠናችሁን በብቃት በማጠናቀቅ ለምርቃት የበቃችሁ እንዲሁም ወደ ስራ ለመሰማራት የተዘጋጃችሁ ልጆቻችን እና እህቶቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!
ለነገዋ የሴቶች የተሃድሶ እና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ለማህበራዊ፣ ለኢኮኖሚያዊ እና ለስነ ልቦና ስብራት የተጋለጡ ሴቶችን ካሉበት የህይወት ውጣ ውረድ እንዲወጡ በማድረግ፣ የስነ ልቦና ድጋፍ እና የሙያ ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ በማሰማራት ላይ የሚገኝ ማዕከል ሲሆን በ2ኛው ዙርም በ17 የሞያ አይነቶች የብቃት ምዘና ያለፉ 380 ሰልጣኞችን አስመርቀን የስራ እድልም ተፈጥሮላቸዋል።
ለማዕከሉ ድጋፍ በማድረግ እና የስራ እድል በመፍጠር ላይ የምትገኙ ባለሀብቶች እንዲሁም ሰልጣኞቹ በማዕከሉ በነበራቸው ቆይታ እናትም አባትም ሆናችሁ ከስልጠና በላይ የሆነ እንክብካቤ እና ፍቅር በመስጠት ከልብ ያሰለጠናችሁ፣ የተንከባከባችሁ እና ወደ ስራ ያሰማራችሁ አመራሮች እና መምህራንን በሰልጣኞቹ እና በራሴ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ