ከ100 በላይ የንግድ ማህበረሰብ አባላትን ያሳተፈው የኢትዮጵያ እና የሳዑዲ አረቢያ የንግድ ምክር ቤት የቢዝነስ ፎረም ተካሄደ
የኢትዮ-ሳዑዲ የጋራ ንግድ ም/ቤት የመጀመሪያ ስብሰባ እና የቢዝነስ ፎረም በሳዑዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ ተካሄዷል።
ስብሰባው በኢትዮጵያ ወገን በኢፌዴሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አብዱልሃኪም ሙሉ ዶ/ር የተመራ ሲሆን የሳዑዲ አረቢያን ልኡካን የሳኡዲ አረቢያ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሃሰን ቢን ሙጂብ አልሁዋዚ መርተውታል።
በፎረሙ ላይ ከ100 በላይ የሁለቱ አገሮች የንግድ ማህበረሰብ አባላትን የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፥ በሁሉቱም አገሮች ለንግዱ ማህበረሰብ ያሉ መልካም እድሎችን በተመለከተ ገለጻዎች ተደርገዋል፥ በንግዱ ማህበረሰብ አባላት መካከልም የቢዝነስ ውይይቶች ተካሂደዋል።
በቢዝነስ ፎረሙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አብዱልሃኪም ሙሉ ዶ/ር እኤአ በጁን 2024 በአዲስ አበባ የተቋቋመው የጋራ ንግድ ም/ቤት የሁለቱን አገራት ታሪካዊ እና ጂኦግራፊያዊ ቅርበትን እንደ እድል በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን ጠቅሰው በኢትዮጵያ ሰፊ የንግድና የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዳሉ በመግለፅ የሳዑዲ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በተመሳሳይ በሳኡዲ አረቢያ የኢፌዴሪ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሙክታር ከድር ዶ/ር የጋራ ንግድ ምክር ቤቱ ስራ መጀመርና የቢዝነስ ፎረሙ መካሄድ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትስስር እንደሚያጠብቅ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
አምባሳደር ሙክታር ጨምረውም በቀጣይ በግንቦት ወር 2017 በአዲስ አበባ በሚካሄደው ኢትዮጵያ ታምርትና ኢንቨስት እን ኢትዮጵያ መድረኮች የሳኡዲ አረቢያ ባለሀብቶች በስፋት እንዲሳተፉ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከኤንባሲው ያገኘነው መረጃ ያመልክታል።