በሶማሊያ የሴክተር አራት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ያሰለጠናቸውን የመሀንዲስ ሙያተኞች አስመረቀ።
ስልጠናው በአካባቢው በድጋፍ ሰጪነት ተሰማርተው ለሚገኙ የምስራቅ ዕዝ የአንድ ኮር አባላት ከUNMAS ጋር በመተባበር በንድፈ-ሀሳብ እና በተግባር የተሰጠ ነው።
ለሙያተኞቹ ሰርተ-ፊኬት የሰጡት የሴክተሩ ምክትል አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ሹመት ጠለለው ሙያተኞቹ ከስልጠናው ባገኙት እውቀት የተሰጣቸውን ተልእኮ በብቃት ሊወጡ እንደሚገባ ገልፀዋል።
በየጊዜው ቴክኖሎጂዎች እየተሻሻሉ በመጡ ቁጥር ብዙ አማራጮች ይኖራሉ ያሉት ጄኔራል መኮንኑ ከግዳጅ ቀጠናው ጋር ተያይዞ አልሻባብ በዋናነት የሚጠቀምባቸውን ፈንጆች በመለየት እና ፍተሻዎችን በማድረግ ጉዳት ሳያደርሱ ማስወገድ ቀዳሚው ተግባር እንደሆነ ተናግረዋል።
ሙያተኞችም ይህንኑ በመገንዘብ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት ቅድመ ፍተሻ እና ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው አስረድተዋል። ስልጠናው በቀጣይነት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን እና በየጊዜው ሙያተኞችን በማፍራት ግዳጅን በስኬታማነት ለማከናወን ይሰራል ብለዋል።
የUNMAS አሰልጣኞች በበኩላቸው ሙያተኞች በስልጠናው ስለነበራቸው ጥሩ ስነ-ምግባር እና የመረዳት ብቃት አድናቆታቸውን ገልፀዋል።
መሰረታዊ ወታደር ወረታው ወንዴ እና መሰረታዊ ወታደር ምንተስኖት በቀለ ከስልጠናው ያገኙት እውቀት አልሻባብ የፍተሻ ቦታዎች ላይ ምን አይነት ፈንጆችን ነጣጥሎ ይዞ ሊገባ እንደሚችል እና ይዞ የገባቸውንም እንዴት ቀጣጥሎ በአካባቢው ላይ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል መንገዶቹን በማወቅ ቀደምተኝነትን ማትረፍ የሚቻልበትን መንገድ በስልጠና አውቀናል ብለዋል።