እንግዲህ ምን ልበል | ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
እንግዲህ ምን ልበል
እንግዲህ ምን ላውራ
እጄን በአፌ አስጫነኝ
የአማኑኤል ስራ
በሞት ጥላ ምድር ያሳለፈኝ መርቶ
ደግሞም ዛሬ አነሣኝ በልጁ ሞት ጠርቶ
ክብሬን ለማይረባ ነገር አልለውጥም
ከአመድ ስላነሳኝ ክብሩ ለዘለዓለም
የሺሖርን ውኃ ለምን እጠጣለሁ
ፊቴን የማዞረው ምን አግኝቼበት ነው
ሁልጊዜ እየራራ ሳይዘነጋኝ ላፍታ
እኔ የዓይኑ ስስት እርሱ የኔ ርካታ
ስለምን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ ብለህ
እኔ አልተነቀልኩም ስለፍጹም ፍቅርህ
ቢቀላ እንዳለላ ነጣ እንደባዘቶ
የተከፋው ልቤ ሄደ ተደስቶ
ከወዜ ላይ ቀለብ ምናልባት ቢሰፍሩ
ወራቶቼ እንባን መከራን ቢያዘሩ
ልቤን ያስነከሰው ያ ቀን አለፈና
የበፍታዬን ኤፋድ ለበስኩ እንደገና
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All
እንግዲህ ምን ልበል
እንግዲህ ምን ላውራ
እጄን በአፌ አስጫነኝ
የአማኑኤል ስራ
አዝ
በሞት ጥላ ምድር ያሳለፈኝ መርቶ
ደግሞም ዛሬ አነሣኝ በልጁ ሞት ጠርቶ
ክብሬን ለማይረባ ነገር አልለውጥም
ከአመድ ስላነሳኝ ክብሩ ለዘለዓለም
አዝ
የሺሖርን ውኃ ለምን እጠጣለሁ
ፊቴን የማዞረው ምን አግኝቼበት ነው
ሁልጊዜ እየራራ ሳይዘነጋኝ ላፍታ
እኔ የዓይኑ ስስት እርሱ የኔ ርካታ
አዝ
ስለምን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ ብለህ
እኔ አልተነቀልኩም ስለፍጹም ፍቅርህ
ቢቀላ እንዳለላ ነጣ እንደባዘቶ
የተከፋው ልቤ ሄደ ተደስቶ
አዝ
ከወዜ ላይ ቀለብ ምናልባት ቢሰፍሩ
ወራቶቼ እንባን መከራን ቢያዘሩ
ልቤን ያስነከሰው ያ ቀን አለፈና
የበፍታዬን ኤፋድ ለበስኩ እንደገና
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All