ከአንተ የሆነው መልካም ነው | ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገብረማርያም
ከአንተ የሆነው መልካም ነው/2/
ሁሉን በጊዜው ስትሰራው
ከአንተ የሆነው መልካም ነው
የኑኃሚን ርስት ሞአብ አይደለችም
ለምለሙን እንጀራ ስቡን ብታበቅልም
በሙላት ወጥታችሁ ባዶ አትመለሱ
የእስራኤልን ቅዱስ ቃልኪዳን አስታውሱ
ሩት አትለፊ የቡኤዝን እርሻ
ጌታ ሰፍሮልሻል የእንጀራሽን ድርሻ
ያለኝ ይበቃኛል ብለው ለሚያምኑት
እጅግ አትርፈዋል ሰላም በረከት
እስማኤል አይደለም የእግዚአብሔር ስጦታ
አብርሃም ሆይ ጽና ባለህበት ቦታ
ሰላም እና ፍቅር ይዞ የሚመጣው
ይስሐቅ ይወለዳል ቢዘገይም ጊዜው
ሰዶም ብታበቅል ለምለሙን ቄጤማ
ለእግዚአብሔር ልጆች መቼም አትስማማ
ድንጋይ እንኳን ቢመስል የአብርሃም ርስት
ጠግበናል ልጆቹ ማርና ወተት
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All
ከአንተ የሆነው መልካም ነው/2/
ሁሉን በጊዜው ስትሰራው
ከአንተ የሆነው መልካም ነው
አዝ
የኑኃሚን ርስት ሞአብ አይደለችም
ለምለሙን እንጀራ ስቡን ብታበቅልም
በሙላት ወጥታችሁ ባዶ አትመለሱ
የእስራኤልን ቅዱስ ቃልኪዳን አስታውሱ
አዝ
ሩት አትለፊ የቡኤዝን እርሻ
ጌታ ሰፍሮልሻል የእንጀራሽን ድርሻ
ያለኝ ይበቃኛል ብለው ለሚያምኑት
እጅግ አትርፈዋል ሰላም በረከት
አዝ
እስማኤል አይደለም የእግዚአብሔር ስጦታ
አብርሃም ሆይ ጽና ባለህበት ቦታ
ሰላም እና ፍቅር ይዞ የሚመጣው
ይስሐቅ ይወለዳል ቢዘገይም ጊዜው
አዝ
ሰዶም ብታበቅል ለምለሙን ቄጤማ
ለእግዚአብሔር ልጆች መቼም አትስማማ
ድንጋይ እንኳን ቢመስል የአብርሃም ርስት
ጠግበናል ልጆቹ ማርና ወተት
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All