ማስተዋል ስጥልን | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ማስተዋል ስጥልን አእምሮን ስጥልን
አከበርንህ ብለው ለጣሉት ክብርህን /2/
አለቱን ፈልፍላ መቅደስ ለተከለች
ሥጋዉና ደሙን ለሕይወት የሰጠች
በአምስቱ አዕማድ የጸናችው ቆማ
የነፍስ እረፍት ነች ያለች አስቀድማ
ያላቸው ከሚመስል የአምልኮ መልክ
ኃይልህን ለካዱት ሀሰት በመስበክ
የሰራሃት ቅፅርህ በፅኑ መሠረት
ከመንጋው ተለዩ በኑፋቄ ትምህርት
ማርያም ማርያም ብትል በሠርክ በማለዳ
ስለሰጠችን ነው መድሃኒትን ወልዳ
ነገረ ቅዱሳን ቢሰበክ በአዋጅ
መች ጋረዱንና ገለጡልን እንጂ
ከሦስት ሺህ ዘመን ቀድማ ለታነጸች
አምላክ ወልደ አምላክ መሆኑን ላመነች
አይሆንም ኢየሱስ እንግዳ ዜናዋ
እርሱ ነው ያስገኛት እርሱ ነው ሰሪዋ
የሥጋን ነው እንጂ የነፍስን ሳያዩ
የጸጋው ግምጃ ቤት እርቀው ተለዩ
ሃይማኖት እያለኝ ምግባር ለጎደለኝ
ለእኔም ማስተዋሉን አእምሮን ስጠኝ
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All
ማስተዋል ስጥልን አእምሮን ስጥልን
አከበርንህ ብለው ለጣሉት ክብርህን /2/
አዝ
አለቱን ፈልፍላ መቅደስ ለተከለች
ሥጋዉና ደሙን ለሕይወት የሰጠች
በአምስቱ አዕማድ የጸናችው ቆማ
የነፍስ እረፍት ነች ያለች አስቀድማ
አዝ
ያላቸው ከሚመስል የአምልኮ መልክ
ኃይልህን ለካዱት ሀሰት በመስበክ
የሰራሃት ቅፅርህ በፅኑ መሠረት
ከመንጋው ተለዩ በኑፋቄ ትምህርት
አዝ
ማርያም ማርያም ብትል በሠርክ በማለዳ
ስለሰጠችን ነው መድሃኒትን ወልዳ
ነገረ ቅዱሳን ቢሰበክ በአዋጅ
መች ጋረዱንና ገለጡልን እንጂ
አዝ
ከሦስት ሺህ ዘመን ቀድማ ለታነጸች
አምላክ ወልደ አምላክ መሆኑን ላመነች
አይሆንም ኢየሱስ እንግዳ ዜናዋ
እርሱ ነው ያስገኛት እርሱ ነው ሰሪዋ
አዝ
የሥጋን ነው እንጂ የነፍስን ሳያዩ
የጸጋው ግምጃ ቤት እርቀው ተለዩ
ሃይማኖት እያለኝ ምግባር ለጎደለኝ
ለእኔም ማስተዋሉን አእምሮን ስጠኝ
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All