ተስፋ ቆርጠን ነበር | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ተስፋ ቆርጠን ነበር ኤማሁስ የሄድነው
በግፍ ስለሞተ ይቤዠናል ያልነው
ሥልሳዉን ምእራፍ በሀዘን ተራመድን
የሚያቃጥል ፍቅሩን ሞቱን እያሰብን
በመንገዳችን ላይ አንድ እንግዳ መጥቶ
ጠየቀን በብርቱ መሀላችን ገብቶ
ዓለም የሰማዉን ባያውቀው ደነቀን
እውነቱን ገለጥነው በእምነት ተናገርን
በስራና በቃል ብርቱ ነብይ ነበር
በአይሁድ ተገድሎ አደረ መቃብር
ይህ ሁሉ ከሆነ ሦስተኛ ቀን ሆነው
በምኩራባችን ላይ መምህሩን ካጣነው
ዛሬ በማለዳ አዲስ ነገር ሰማን
በመቃብር የለም ተነስቷል ጌታችን
ሴቶች አስገረሙን ሥጋው የለም ሲሉ
መላእክቱም ታዩ ህያው ነው እያሉ
መጻህፍትን ገልጾ በሚነግረን ነገር
ልባችን በሚስጢር ይቀልጥብን ነበር
አይናችን ተይዞ እኛ መች አወቅነው
ቀኑ መሽቷልና በቤት እደር አልነው
እንጀራውን ቆርሶ በእጃችን ሲሰጠን
ባይናችን ላይ ያለው አዚሙ ለቀቀን
እንዳላዋቂ ሰው ከኛ ጋራ ያለው
የትንሳኤው ጌታ ለካስ እየሱስ ነው/3/
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All
ተስፋ ቆርጠን ነበር ኤማሁስ የሄድነው
በግፍ ስለሞተ ይቤዠናል ያልነው
ሥልሳዉን ምእራፍ በሀዘን ተራመድን
የሚያቃጥል ፍቅሩን ሞቱን እያሰብን
አዝ
በመንገዳችን ላይ አንድ እንግዳ መጥቶ
ጠየቀን በብርቱ መሀላችን ገብቶ
ዓለም የሰማዉን ባያውቀው ደነቀን
እውነቱን ገለጥነው በእምነት ተናገርን
አዝ
በስራና በቃል ብርቱ ነብይ ነበር
በአይሁድ ተገድሎ አደረ መቃብር
ይህ ሁሉ ከሆነ ሦስተኛ ቀን ሆነው
በምኩራባችን ላይ መምህሩን ካጣነው
አዝ
ዛሬ በማለዳ አዲስ ነገር ሰማን
በመቃብር የለም ተነስቷል ጌታችን
ሴቶች አስገረሙን ሥጋው የለም ሲሉ
መላእክቱም ታዩ ህያው ነው እያሉ
አዝ
መጻህፍትን ገልጾ በሚነግረን ነገር
ልባችን በሚስጢር ይቀልጥብን ነበር
አይናችን ተይዞ እኛ መች አወቅነው
ቀኑ መሽቷልና በቤት እደር አልነው
አዝ
እንጀራውን ቆርሶ በእጃችን ሲሰጠን
ባይናችን ላይ ያለው አዚሙ ለቀቀን
እንዳላዋቂ ሰው ከኛ ጋራ ያለው
የትንሳኤው ጌታ ለካስ እየሱስ ነው/3/
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All