ኦ እንዳንተ ያለ ወዳጅ ✞
ኦ እንዳንተ ያለ ወዳጅ አላገኘሁም እኔ
ኦ ውለታህን ሳስበው በእንባ ይመላል አይኔ
ከእናቴም ልጆች በላይ አንተ ውድ ነህ ለእኔ
ወዳጅና ዘመዴ ጌታ የክፉ ቀኔ
ምን አለኝና ልስጥህ የሚነገር የሚወራ
እኔስ ተሸንፊያለሁ በእንባ ስምህን ልጥራ
አዝ_
ተሰድጄ ብወጣ ወጥተሃል ከእኔ ጋራ
ትላንትናን አለፍኩት ጠላቴን እያራራ
ደግሞ የነገውን ቀን አንተ ታውቃለህ ጌታ
ወጥመዴን ስበርና አፌን ሙላው በእልልታ
አዝ_
በእስረኞች መሀል ሁኜ ሰንሰለት ለብሻለሁ
አለም እውነት የላትም ፍትህ ካንተ እሻለሁ
መቼ ታጽናናኛለህ ወዳጅና ዘመዴ
አውጣኝ አውጣኝ ለሚልህ አንተ አታጣም ዘዴ
አዝ_
መመላለስ አይደክምህ እኔን ማስታመም አንተ
ደክመህ አልፈልህልኛል እጆቼን አበርትተ
ሁሌ በሬ ላይ ቁም ደጃፌን የምትመታ
ግባ የክብር ንጉስ ብያለሁ ማራናታ/5×/
👉ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
ኦ እንዳንተ ያለ ወዳጅ አላገኘሁም እኔ
ኦ ውለታህን ሳስበው በእንባ ይመላል አይኔ
ከእናቴም ልጆች በላይ አንተ ውድ ነህ ለእኔ
ወዳጅና ዘመዴ ጌታ የክፉ ቀኔ
ምን አለኝና ልስጥህ የሚነገር የሚወራ
እኔስ ተሸንፊያለሁ በእንባ ስምህን ልጥራ
አዝ_
ተሰድጄ ብወጣ ወጥተሃል ከእኔ ጋራ
ትላንትናን አለፍኩት ጠላቴን እያራራ
ደግሞ የነገውን ቀን አንተ ታውቃለህ ጌታ
ወጥመዴን ስበርና አፌን ሙላው በእልልታ
አዝ_
በእስረኞች መሀል ሁኜ ሰንሰለት ለብሻለሁ
አለም እውነት የላትም ፍትህ ካንተ እሻለሁ
መቼ ታጽናናኛለህ ወዳጅና ዘመዴ
አውጣኝ አውጣኝ ለሚልህ አንተ አታጣም ዘዴ
አዝ_
መመላለስ አይደክምህ እኔን ማስታመም አንተ
ደክመህ አልፈልህልኛል እጆቼን አበርትተ
ሁሌ በሬ ላይ ቁም ደጃፌን የምትመታ
ግባ የክብር ንጉስ ብያለሁ ማራናታ/5×/
👉ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን