ኢየሱስ ክርስቶስ - እውነተኛ ብርሃናችን!
[ "ብርሃን ወደ ዓለም መጣ፥ ያድነን ቤዛም ይሆነን ዘንድ፥ ብርሃንንም ይገልጥልን ዘንድ ቃል ሥጋ ሆነ።'' (ቅዱስ ያሬድ)]
በቤተክርስቲያናችን ሥርዓት ከታህሳስ 14 - 20 ያለው ጊዜ "ብርሃን" ይባላል። ነቢያት ብርሃን ክርስቶስ እንዲገለጥላቸው መማጸናቸው፥ የተገለጠው መድኅን ብርሃን መሆኑ ይነገርበታል።
ኦሪት የጨለማ ዘመን ናትና አበው የሰው ልጆች ተስፋ መድኅን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን ሆኖ ይገለጥላቸው ዘንድ በብርቱ ይጮኹ ነበር። ክቡር ዳዊት 'ብርሃንህና ጽድቅህን ላክ፥ እነርሱም ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ' እያለ ተማጽኗል(መዝ 42(43):3)። ምሥጢራዊ ትርጓሜው 'ብርሃንና ጽድቅ የተባለ የባሕርይ ልጅህ ኢየሱስ ክርስቶስን ወደዚህ ዓለም ላክልን፥ እርሱም የእኛ ወገን ከምትሆን ከእመቤታችን ሥጋንና ነፍስን ነስቶ ተወልዶ እውነትና መንገድ ሕይወትም በመሆን ወደ መንግስተ ሰማያት መርቶ ያስገባኝ።' ማለት እንደሆነ አባቶቻችን ያስተምራሉ።
ነቢዩ ኢሳይያስም አስቀድሞ በመንፈስ ቅዱስ ኾኖ 'በጨለማ የተቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፥ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው።' እንዳለ ብርሃን ተገለጠ(ኢሳ 9:2)። ያም ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው(ዮሐ 8:12)። ይህ ብርሃን በሥጋ በመገለጡ በድንቁርና በቀቢጸ ተስፋ ለነበሩ መንፈሳዊ ዕውቀት፥ በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ ለነበሩ የከበረ ልጅነት፥ በኃጢአት በክህደት ለነበሩ ሃይማኖተ ክርስቶስ ተሰጥቷቸዋል። በእርሱ ያመንን ለእኛም 'ውሉደ ብርሃን - የብርሃን ልጆች' የመባልን ክብር አደለን(ኤፌ 5:9-10)።
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በውዳሴ ማርያም ድርሰቱ 'በዚህ ዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የምታበራ እውነተኛ ብርሃን ስለ ሰው ፍቅር ወደዚህ ዓለም የመጣው ፍጥረት ሁሉ በመምጣትህ ደስ አለው።'(ውዳ. ማር. ዘሰኑይ) እያለ ሲያመሰግነው ቅዱስ ያሬድ ደግሞ "ወደ ዓለም የመጣው ብርሃን ለጻድቃን የሚያበራ የቤተ ክርስቲያን ሙሽራ ነው። የጠፋውን ይፈልግ (ይረዳ) ዘንድ የተበተኑትን ይሰበስብ ዘንድ ወደእኛ መጣ።' እያለ ወደ ዓለም የመጣውን እውነተኛ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ያመሰግኑታል።
ክብርና ምስጋና አምልኮትና ውዳሴ ብርሃን ሆኖ ከጨለማ ላወጣን ለእርሱ ይሁን፥ አሜን!!!