ተስፋ አትቁረጥ። በእግዚአብሔር ድፍረት ይኑርህ።ምንም እንኳ የዲያቢሎስ ውጊያዎች ከባድ ቢሆኑም ተስፋ አትቁረጥ። ብዙ ጊዜ ብትወድቅ ፣ ትዕዛዛቱን ብትዘነጋና ምግባር ጎዶሎ ብትሆን ተስፋ አትቁረጥ። ለራስህ እንዲህ በል፦እነዚህ ሁሉ ተራ ውጊያዎች ናቸው። ቢሆንም ወደ እግዚአብሔር እጠጋለሁ።እግሮቼንም ብጎትት ወደ እግዚአብሔር የማደርገው ጉዞዬን አላቋርጥም። በጉዞዬ ላይ አንድ መቶ ጊዜ ብወድቅም እንኳን ተነስቼ ጉዞዬን እቀጥላለው። ተስፋ መቁረጥ ከዲያቢሎስ ነውና ምንጊዜም ቢሆን ተስፋ አልቆርጥም።