ኦርቶዶክስ ተዋህዶ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана



Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ቅድስት ሶፍያ
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥር ሠላሳ በዚች ቀን
ቅድስት ሶፍያና እና የከበሩ ሶስቱ ደናግል ልጆቿ ጲስጢስ አላጲስና አጋጲስ ስለ ክርስቶስ ፍቅር በሰማዕትነት አረፉ
የተባረከች እናታቸው ሶፊያም ከአንፆኪያ ከከበሩ ወገኖች ውስጥ ናት የልጆቿም የስም ትርጉም ሃይማኖት ተስፋ ፍቅር ነዉ
የራሷ ስም ትርጓሜም ጥበብ ማለት ነው
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎታቸው ይማረን በርከታቸው ከኛጋር ትኑር ለዛላለሙ አሜን
መልካም በዓል

✝ኦርቶዶክስ ተዋህዶ✝

#መልካም_እለት

https://t.me/OrtoPicture
https://t.me/OrtoPicture
https://t.me/OrtoPicture


ምስባክ አመ ፴ ለጥር

👉👉@misbakze👈👈


ግጻዌ አመ ፴ ለጥር

👉👉@misbakze👈👈






ግጻዌ አመ ፳፱ ለጥር

👉👉@misbakze👈👈


ምስባክ ዘነግህ አመ ፳፰ ለጥር

👉👉@misbakze👈👈


ግጻዌ አመ ፳፰ ለጥር

👉👉@misbakze👈👈






ጥር 24

ኢትዮጲያዊው ጻድቅ አባታችን አቡነ ተክለ ሐይማኖት እግራቸው በጸሎት ብዛት የተሰበረበት ዕለት ነው
አባታችን በጸሎታቸው ሀገራችንን ከመከራ ይጠብቁልን

መልካም በዓል

✝ኦርቶዶክስ ተዋህዶ✝

#መልካም_እለት

https://t.me/OrtoPicture
https://t.me/OrtoPicture
https://t.me/OrtoPicture


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

††† ጥር 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1አቡነ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅድስት ማርያ ግብጻዊት
3.ታላቁ አባ ቢፋ
4.አባ አብሳዲ ቀሲስ
5.ቅዱሳን ጻድቃነ ሐውዚን

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእነዚህ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን




[ጥር ፳፩ የእመቤታችን ዕረፍትና የሊቃውንት ውዳሴ]
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት እንደገለጹልን የቅድስት ድንግል ማርያም መላ ዕድሜዋ 64 ሲኾን ይኸውም በእናት ባባቷ ቤት 3 ዓመት፤ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት፤ ጌታን ፀንሳ በቤተ ዮሴፍ 9 ወር ከ5 ቀን፤ ከልጇ ጋር 33 ዓመት ከ3 ወር፤ በቤተ ዮሐንስ 15 ዓመት ከቆየች በኋላ፤ ልጇ ክርስቶስ ለእናቱ ተገልጾ ከኀላፊው ዓለም ወደ ማያልፈው ሰማያዊዉ ዓለም ሊወስዳት እንደኾነ ነገራት።

💥 ርሷም ይኽነን ለሐዋርያት ነገረቻቸው፤ እነርሱም “አይቴ ተሐውሪ እግዝእትነ” (እመቤታችን ወዴት ትኼጃለሽ) ብለው ሲጠይቋት “ኀበ ጸውአኒ ወልድየ” (ልጄ ወደጠራኝ) በማለት ወደዚያኛው ዓለም የመኼጃዋ ጊዜ እንደደረሰ ነገረቻቸው፤ ይኽነን ሰምተው “ወበከዩ ኲሎሙ ሐዋርያት” ይላል ሐዋርያት በእጅጉ ዐዘኑ አለቀሱ፤ ያን ጊዜ የአምላክ እናት ፊት ተሰብስበው ከእጆቿ በረከትን አገኙ፡፡

💥 ያን ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ተገልጸው ሐዋርያትን ማዕጠንታቸውን ይዘው ደስ አሰኝተው እንዲሸኝዋት እንጂ እንዳያዝኑ እንዳያለቅሱ በመንገር አረጋጓቸው፤ ጌታም ተገልጾ "ዛሬ ለዘጠኝ ወራት በምድር ላይ መኖሪያዬ ኾና የቆየችውን ድንግል እናቴን የምቀበልበት እና ከእኔ ጋር ወደ ሰማያት ሰማያዊ ቦታዎች ይዤያት በመውሰድ ለመልካሙ አባቴ በስጦታ የማስረክባት ቀን ነው፣ ዳዊትም እንኳን “በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ፤ ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ” (መዝ ፵፬፥፲፬) እንዳለ በማለት ተናገረ።

💥 ከዚያም ጌታ እናቱን "የኔ ውድ እናት ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ፤ በመጠቅለያ ጨርቆች እንደጠቀለልሽኝ ኹሉ የእኔ ድንግል እናት ማርያም ሆይ በወለድሽኝ ዕለት በከብቶች በረት ከላም እና አህያ ጋር በአንድ ላይ ከብበውኝ እንዳኖርሽኝ ኹሉ (ኢሳ ፩፥፫፤ ሉቃ ፪፥፯)፤ እኔ ደግሞ ዛሬ ከእኔ ጋር ከሰማያት ባመጣዋቸው በሰማይ መጐናጸፊያ ሰውነትሽን እጠቀልለዋለኊ፤ ከዚያም ከሕይወት ዛፍ ሥር አስቀምጠዋለኊ፣ ኪሩቤልም በነበልባላማ ሰይፋቸው እንዲጠብቁት አደርጋለኊ (ዘፍ ፫፥፳፬)፡፡

💥 የተባረከችውን ነፍስሽን የሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም መንበር በተሸፈነችበት መሸፈኛዎች እንድትሸፈን አደርጋለኊ፡፡ እኔን በሚያሳድድበት ጊዜ ሥርዓት አልባውን ሄሮድስ በመፍራት ወደ ግብጽ ምድር እንደተሰደድሽው ኹሉ (ማቴ ፪፥፲፫-፲፰)፤ መላእክቶቼ ኹልጊዜም በክንፎቻቸው እያጠሉብሽ እና መልካም ዝማሬያቸውን እንዲዘምሩልሽ አደርጋለኊ አላት፡፡

💥 ይኽን ከልጇ በሰማች ጊዜ ጥር 21 እሑድ ዕለት በልጇ ፈቃድ በመዐዛ ገነት፣ በመዝሙረ ዳዊት፣ በይባቤ መላእክት የእመቤታችን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየ።

♥❖♥ ቅዱስ ያሬድም በመጽሐፈ ድጓው ላይ፡-
“ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና (ለማርያም)
ወረደ ወልድ እምዲበ ልዕልና
ጠሊሳነ ንግሥ ሶቤሃ ከደና”

(በማርያም ዕረፍት ጊዜ ወልድ ከልዕልና ወረደ፤ የንግሥና (የክብር) መጐናጸፊያን በዚያን ጊዜ ሸፈናት) በማለት የዕረፍቷን ነገር አስተምሯል፡፡

♥❖♥ የመልክአ ማርያምም ጸሐፊ በአድናቆት፦
“ሰላም ለፀአተ ነፍስኪ እንበለ ጻዕር ወጻማ
ለነቢር ዘልፈ በየማነ ወልድኪ ፌማ”

(ከሃሊ (ማእምር፣ ጠቢብ) በሚኾን ልጅሽ ቀኝ ዘወትር ለመቀመጥ ያለ ድካምና ያለ ጣር ለኾነ የነፍስሽ መለየት ሰላምታ ይገባል) ብሏታል፨

💥 ጌታም እንደ በረዶ ጸዐዳ የኾነውን የድንግል ማርያምን ነፍስ በዕቅፉ ውስጥ እንደያዘ ለነፍሷ ሰላምታውን ሰጥቶ ባማረው ሸማ ጠቅልሏት ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል በብርሃናማ ክንፎቹ እንዲሸከማት ሰጠው፤ የከበረ ሥጋዋም የጠራና መዐዛው ድንቅ ነበር።

♥❖♥ የመልክአ ማርያም ደራሲው ሊቁ፦
“ሰላም እብል በድነ ሥጋኪ ጽሩየ
ዘተመሰለ ባሕርየ"

(ዕንቊን ለተመሰለ የጠራ የሥጋሽ በድን ሰላም እላለኊ) በማለት ያመሰግናል።

💥 ከዚያም ቅዱሳን ሐዋርያት በዚያ አስደናቂ መጎናጸፊያ በክቡራን ሽቱዎች የከበረ ሥጋዋን አጅ እየነሡ ገንዘዋታል።

💥 ሊቁም በመልክአ ማርያም ላይ፦
“ሰላም ለግንዘተ ሥጋኪ በእደ ሐዋርያት አርጋብ
በአፈወ ዕፍረት ቅድው ዘሐሳበ ሤጡ ዕጹብ"

(የዋጋው ስሌት እጅግ ውድ በኾነ ያማረ ሽቱ ርግቦች በተባሉ በሐዋርያት እጅ ለተደረገ የሥጋሽ አገናነዝ ሰላምታ ይገባል) በማለት ያመሰግናል።

♥❖♥ ከኢትዮጵያ ሊቃውንት መኻከል ስለዚኽ በቅዱሳን ሐዋርያት ስለተደረገው የከበረ የሥጋዋ ግንዘት ቅዱስ ያሬድ አምልቶ አስፍቶ የጻፈ ሲኾን፤ በነሐሴ ፲፭ በአጫብሩ ድጓ ውስጥ በአስደናቂ መልኩ እንዲኽ ተጽፈዋል፡-

♥ “ሐዋርያት አመድበሉ
ሥጋ ድንግል ጠብለሉ
በሰንዱነ ብርሃን ዘላዕሉ
ልብሳ ተካፈሉ”

(ሐዋርያት ተሰበሰቡ፤ ከላይ በመጣ በፍታ (መጐናጸፊያ) የድንግል ሥጋን ጠቀለሉ፤ ልብሷንም ተካፈሉ)፨

♥ “በደመና ተጋቢኦሙ ሐዋርያት ለድንግል ንጽሕት
ገነዝዋ በክብር ወበስብሐት
ለቀበላሃ ወረዱ ኀይላት
ወቀበርዋ ውስተ ገነት”

(ሐዋርያት በደመና ተሰብስበው ንጽሕት ድንግልን በክብር በምስጋና ገነዟት፤ ለአቀባበሏ ኀይላት ወረዱ፤ በገነት ውስጥም ቀበሯት)፨

♥ “ተጋቢኦሙ ሐዋርያት እምኲለሄ
በደመናት ዘምሉእ ሡራኄ
ገነዙ በክብር ወበስባሔ
ሥጋ ድንግል ዘይምዕዝ እምርሔ”

(ብርሃንን የተመላ በኾነ በደመናት ሐዋርያት ከአራቱ ማእዝን ተሰብስበው ልብን ከሚመስጥ ሽቱ ይልቅ የሚሸትት የድንግልን ሥጋ በክብርና በምስጋና ገነዙ)፨

♥ “ተጋቢኦሙ በደመና ሰማይ
ሐዋርያት ሥርግዋን በዕበይ
ገነዝዋ ለድንግል በብዙኅ ግናይ
ዳዊት ዘመራ በመሓልይ”

(በገናንነት የተጌጡ ሐዋርያት በሰማይ ደመና ተሰብስበው ድንግልን በብዙ ምስጋና ገነዟት፤ ዳዊትም በምስጋና አመሰገናት)፨

♥ “ተጋቢኦሙ አርድዕተ ወልዳ
በደመና ብርሃን ጸዐዳ
ገነዝዋ በስብሐት ለጽርሕ ሳይዳ”

(ጸዐዳ በኾነ በብርሃን ደመና የልጇ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበው፤ ውቢቱ አዳራሽን በምስጋና ገነዟት)፨

♥“ተጋብኡ በቅጽበት ለግንዘተ እሙ ቅድስት
ብፁዓን ሐዋርያት
ቦኡ ኀቤሃ በሰላም አምኁ ኪያሃ
በስብሐት ገነዙ ሥጋሃ”

(ንኡዳን ክቡራን ሐዋርያት ቅድስት የምትኾን የጌታ እናቱን ለመገነዝ በቅጽበት ተሰበሰቡ፤ ወደ ርሷ ገብተው በሰላምታ ርሷን እጅ ነሧት፤ ሥጋዋንም በምስጋና ገነዙ) በማለት ሊቁ ማሕሌታይ በሐዋርያት እጅ የተደረገ የሥጋዋን ግንዘት አምልቶ አስፍቶ ጽፏል፡፡

♥ ከዚያም ወዲያውኑ የድንግልን የከበረ አካል ወደ ላይ በማንሣት ቅዱስ ጴጥሮስ ራሷን፣ ቅዱስ ዮሐንስ እግሮቿን ተሸክመው የተቀሩት ሐዋርያት በእጆቻቸው የዕጣን ማዕጠንት ይዘው በታላቅ ግርማ በአምላክ እናት ሥጋ ፊት ምስጋናን እያሰሙ ዝማሬን እየዘመሩ ሥጋዋን እጅ እየነሡ ጌቴሴማኒ ሊቀብሯት ሲኼዱ አይሁድ አይተው “ንዑ ናውዒ ሥጋሃ ለማርያም ምስለ ዓራታ” በማለት በምቀኝነት ተነሡባቸው፤ ታውፋንያ የሚባል ከአይሁድ ወገን በድፍረት የአልጋዋን አጎበር ሊነካ ሲሞክር ቅዱስ ገብርኤል በሰይፈ እሳት ቀጣው፡፡

♥ ያን ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ በዕለተ ዐርብ ከአምላኩ በስጦታ የተሰጠችውን የአምላክ እናትን ሥጋዋን በድፍረት ሊነኩ መምጣታቸውን አይቶ “ዐደራዬን አላፈርስም፤ ከርሷ ጋር እሞታለኊ" በማለት ይኽነን ተናግሮ በላይዋ ላይ ወደቀ፡፡

♥ ከዚያም “ወወረዱ ሚካኤል ወገብርኤል እምሰማይ በዐቢይ ግርማ” ይላል ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በታላቅ ግርማ ወርደው የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥጋዋንና ቅዱስ ዮሐንስን በደመና ነጥቀው በገነት በሕይወት ዛፍ ሥር አኖሯት፡፡


ቅዳሜ ይጾማል ወይ ?

ጥምቀት እሑድ ቀን በሚውልበት ጊዜ የራሱ አዋጅ አለው ። የጥምቀት በዓል ደግሞ የዋለው እሑድ ነው ። በዚህም መሰረት አዋጁ ቅዳሜን እንድንጾም ያዝዘናል ። ስንጾምም ጥሉላት ምግቦችን ከመብላት ነው ።ስለዚህም ቅዳሜ ከቅዳሴ በሗላ ጥሉላት ያልሆኑትን ምግቦችን መብላት እንችላለን ። ነገር ግን ቀድሞ ያለውን አርብ እስከ 12 ሰአት እንጾማለን ።


https://t.me/geeZzlekulu


#በዓለ_ጥምቀት_ቅዳሜ_እሑድ_ቢውል
ጾመ ጋድ_ይጾማል
ብዙዎቻችን ስለ ጾመ ጋድ ስናስብ በዓለ ልደትና በዓል ጥምቀት ረቡዕ እና አርብ ከዋሉ ብቻ የሚጾም አድርገን እንወስዳለን። ጾመ ጋድ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንዱ ነው። በልደትና በጥምቀት ዋዜማ ላይ ይጾማል። ጋድ ማለት ለውጥ ማለት ነው። በዓላቱ ረቡዕና አርብ ቢውሉ የዚያ ለውጥ ማክሰኞና ሐሙስን ጾመን በዕለቱ ጥሉላትን እንመገባለንና እንዲህ ተብሏል አንድም ገሀድ ይባላል መገለጫ ማለት ነው በልደቱ አምላክ ሰው ሆኖ በጥምቀቱ ደግሞ ብርሃነ መለኮቱን ገልጦ አይተነዋልና
ወደ መነሻ ሀሳባችን ስንመለስ በቤተ ክርስቲያናችን የሕግና የሥርዓት መጽሐፍ በሆነው ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ላይ ስለ አጽዋማት በሚናገርበት ሐተታው ጾመ ጋድ ከረቡዕና ከአርብ ውጭ ባሉት ቀናት ቢውሉ ዋዜማው እንደሚጾም « ሥርዓት አንድ ጊዜ ከተሠራ አይፈርስምና አንድም አንድ ጊዜ ሲጾም አንድ ጊዜ ሲቀር እንዳይረሳ » በማለት በዓመት በዓመት ጾመ ጋድ እንዳለ ይነግረናል

የሰንበታቱን (የቅዳሜና የእሑድን) ለየት የሚያደርገው ደግሞ ለምሳሌ ልክ ዘንድሮው በዓለ ጥምቀት እሑድ ቢውል ቅዳሜ ሰንበት ስለሆነ ሰዓት እንደሌሎች የአጽዋማት ዕለታት እህል ሳንቀምስ ባንውልም ከጥሉላት ምግቦች ግን ተከልክለን መቆየት እንዳለብን ይደነግጋል። ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንም በዚሁ ላይ ሲጨምሩ በዓለ ጥምቀት ቅዳሜ ወይም እሑድ እንዲሁም ሰኞ ቢውል ቀድሞ ባለው ዕለተ አርብ የጾማችንን ሰዓት ከፍ አድርገን በመቆየት የጾመ ጋድን ጾም ደርበን እንድንጾም ያስተምራሉ።

ጥር - 9-2017 ዓ,ም
◈⊰───── © እሱዬ ይማም

✝ኦርቶዶክስ ተዋህዶ✝

#መልካም_እለት

https://t.me/OrtoPicture
https://t.me/OrtoPicture
https://t.me/OrtoPicture





Показано 18 последних публикаций.