ኖላዊ ሆይ ! ባይጠብቁ አያስክዱ !?!?
➠ እመቤታችን ቤዛ አትባልም እንዲሉ ያስገደደዎት ምንድን ነው ? አውቀው ነው ? ወይስ ሳያውቁ ነው ?
ለማደናገር ነው ? ለማስካድ ነው ? ለማሰናከል ነው ?
➠ እመቤታችን ቤዛ እንዳይደለች ያነበቡት መጽሐፍ አለ?
ወይስ የጠየቁት መምህር አለ ? ነው የተገለጠልዎት መገለጥ አለ ? ወይስ ያዩት ራዕይ አለ? ነው የነገረዎት መልአክ አለ ? ይህንንስ ተናግረው የሚመልሱት መናፍቅ በትምህርትዎት የሚያጸኑት ምዕመን አለ ? ነው የሚያስጨብጡት መሠረታዊ ዕውቀት አለ ከሌለ ይህን እንዲናገሩና እንዲያስተምሩ ምን አስገደደዎት ?
➠ በእርግጥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ጵጵስና ? ካገኙ የማያጧት ከገቡ የማይወጡባት ከወረሷት የማትነጠቅ መንግሥተ ሰማያት
ከሆነ ውሎ አድሯል ። አንድ ሰው የጵጵስና ቆብ ከጫነ በኋላ የፈለገውን የሚናገርበት ያሰበውን የሚተነፍስበት ዓውደምህረት ይፈጥራል ከዚያ በኋላ ለተናገረው ስሑት ነገር ቀኖና ሳይገባ ወይ ተድበስብሶ ይታለፋል ያለዚያም በይቅርታ ይተዋል ግን ለምን ይሆን ?
➠ ቤዛ ማለት ምንድን ማለት ነው ?
ይህ ኃሳብ በእርግጥ የጳሱ ሳይሆን የፕሮቴስታንት ኃሳብ ነው ፕሮቴስታንት ቤዛ መድኃኒት መባል ለጌታ ብቻ እንጅ ለሌላ አይገባም ቤዛነትን ለሌላ አካል መስጠት የጌታን አዳኝነት መካድና ሌሎቹን ከጌታ ጋራ ማስተካከል ነው ይላሉ ስለዚህ ብፁዕነትዎ እንዲህ እንዲሉ ከጀርባዎት ማን ነው ያለ ?
⏩ ቤዛነት በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ምንድን ማለት
ነው ? ቤዛ ማለት ሁለት ትርጕሞችን የያዘ ነው
፩ , ተቤዘወ አዳነ ካለው የወጣ የግዕዝ ግሳዊ ቃል ሲሆን ትርጕሙ መድኃኒት አዳኝ ማለት ነው ።
ዮም ተወልደ ቤዛ ኵሉ ዓለም ፦ ዛሬ የዓለም ሁሉ መድኃኒት ተወለደ እን ቅ ያሬ
፪, ስለ፣ ፈንታ ማለት ነው ዐይን ቤዛ ዐይን ወስን ቤዛ ስን ስለዐይ ፈንታ ዐይን ይጥፋ ስለ ጥርስ ፈንታ ጥርስ ይርገፍ እን ዘጸ ማቴ ፭ ÷ ስለዚህ እመቤታችንን ቤዛ ሲላት ምን ማለት ነው ኅፀፅስ አለው ወይ ?
⏩ ስለእመቤታችን ቤዛነት ከመናገሬ በፊት ትንሽ ነገር ልናገር እወዳለሁ ለአንድ ግስ ሦሰት ነገሮች አሉት
፩, ንባብ
፪, ትርጕም
፫, ምሥጢር ፦ እነዚህን ጠንቅቆ አለመረዳት ፍጹም ወደሆነ የስህተት ጕድጓድ መውደቅ ነው ።
ማንኛውም ነገር በንባብ ይገናኛል በትርጕምም ይገናኛል በምሥጢር ግን ይለያያል ።
⏩ ይህም ማለት እግዚአብሔር ቅዱስ ይባላል መላዕክት ቅዱሳን ይባላሉ ሰዎችም ቅዱሳን ይባላሉ ፍጥረታትም ቅዱሳን ይባላሉ ።
ቅዱስ ማለት ልዩ ንጹህ ክቡር ማለት ነው ስለዚህ እግዚአብሔርን ቅዱስ ስንለው የባህርዩ ነው መላእክትን ቅዱሳን ስንላቸው የጸጋ ነው አንድ ጊዜ ተሰጥቷቸዋል እያደጉ ይሄዳሉ እንጂ መመለስ መውደቅ የሌለበት ነው (ከዲያብሎስ ውጭ) ሰዎችን ቅዱሳን ስንላቸው በተፈጥሮ ይሰጣየዋል በልጅነት ይታደላየዋል ኋላ በኃጢአት ነሳቸዋል በምግባር በትሩፋት በንስሃ ይመለስላቸዋል ፍጥረታትን ቅዱሳን ስንላቸው የተፈጥሮ ነው ማለት እግዚአብሔር ሲፈጥር አንድ ጊዜ ንፁህ አድርጎ ፈጥሯቸዋልና ፤
ስለዚህ ቅዱስ ባለው ንባብ ይገናኛሉ ልዩ ባለው ትርጕምም ይገናኛሉ በምሥጢር ይለያሉ ማለት የእግዚአብሔር ቅድስና ከመላዕክት የመላዕክት ቅድስና ከሰዎች የሰዎች ቅድስና ከሥነፍጥረት ቅድስና ፈጽሞ የተለየ ነው
⏩ እግዚአብሔር ረቂቅ ነው መላዕክትም ረቂቃን ናቸው
ነፋስም ረቂቅ ነው ውሃ በእጅ የማይጨበጥ በዓይን የማይታይ በእቃ የሚያዝ ረቃቅ ነው እሳት በዓይን የሚታይ በእጅ የማይጨበጥ ረቂቅ ነው ሰይጣን ረቂቅ ነው እሊህ ሁሉ ግን ንባብ ትርጕም ቢያገናኛቸው የርቀት ምሥጢር ይለያየዋልና የአንዱ ርቀት ከአንዱ ርቀት ፈጽሞ የተለነ ነው
🕎 መጽሐፍ እመቤታችንን ቤዛ ሲላት ከጌታ ቤዛነት ጋራ
ንባብና ትርጕም አገናኛት እንጅ ምሥጢር አያጋናኛትም
የእርሷ ቤዛነት ( ፈንታነት ) ስለሔዋን ነው ይህ ማለት ሔዋን ትዕዛዘ እግዚአብሔርን እንቢ በማለት ሞትን አመጣች ቤዛ ሔዋን እመቤታችን እንደቃለህ ይሁንለኝ ብላ ትዕዛዘ እግዚአብሔርን በመቀበል ሕይወትን አመጣች ።
🕎 ሔዋን ባለመታመን በጥርጥር በዓለም ላይ የሞት አዋጅን አሳወጀች ቤዛ ሔዋን እመቤታችን በፍጹም እምነት በፍጹም አለመጠራጠር በዓለም ላይ የሕይወት አዋጅን አሳወጀች ሔዋን ቃለ ሰይጣንን ሰምታ ሰምታ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን አመጣችብን ቤዛ ሔዋን እመቤታችን ቃለ መልአክን ሰምታ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስን አመጣችልን ቤዛነት ማለት ይህ አይደለምን ?
🕎 ሔዋን ምክንያተ ሞት መሠረተ ሞት ቃኤልን ወለደች
ቤዛ ሔዋን እመቤታችን ምክንያተ ሕይወት መሠረተ ሕይወት ክርስቶስን ወለደች ።
ነገር ግን ሔዋንን ዲያብሎስ አሳታት የሞት ምንያት የሚሆን ቃኤልን ወለደች ማርያም ግን መልአክ በአበሠራት ጊዜ ሁሉን ወደዘለዓለም ሕይወት የሚመራ አካላዊ ቃልን በሥጋ ወለደች ሃይ አበ ፷፯ ÷ ፬
🕎 ገነት በሔዋን ምክንያት እነደተዘጋች በቤዛ ሔዋን በእመቤታችን ምክንያት ተከፍታለች ሔዋን ለዓለም ድቀት ምክንያት ከሆነች ቤዛ ሔዋን እሠቤታችን ለዓለም መነሳት ምክንያት ሆነች ቢባል ምንድን ነው ጥፋቱ ?
🕎 ክርስቶስ ግን ቤዛ ሲባል በመጥወተ ርዕስ (ራሱን ሠሥዋዕት አድርጎ) በመስጠት ሥጋውን በመቁረስ ደሙን በማፍሰስባህርያዊ መሥዋዕት በማቅረብ ነው ።
እርሱ የመሥዋዕት በግ ነው እርሱም መሥዋዕት አቅራቢ ሊቀ ካህናት ነው እርሱ ከባህርይ አባቱ ከአብ ከባህርይ ሕይወቱ ከመንፈስቅዱስ ጋራ መሥዋዕት ተቀባይ ነው
ሃይ አበ ፴፮ ÷ ፳፮
ስለዚህ ብፁዕነትዎ ቤተክርስቲያን እመቤታችንን ቤዛ ስትል የጌታን ቤዛነት ሰጥታ እመቤታችን ሥጋዋን ቆርሳ ደሟን አፍስሳ ቤዛ ሆነችን እያለች አደለም ።
ስንዱዋ እመቤት ቤተክርስቲያን ይህንን ያህል ዘመን እመቤታችንን ቤዛ ስትል በረቀቀ ዐይን ተመልክታ አየረ አየራትን ወጥታ እመቀ እመቃትን ወርዳ እንጅ በገዘፈ ዐይን እንዳይመስልዎት ?!?!
ስለዚህ ይህ ኃሳብ ለዘመናት ሲነገር የኖረ የፕሮቴስታንት ኃሳብ እንጅ የእርስዎት ኃሳብ አደለም ።
ወይ ተገልጠው ይምጡ ወይ አጥፍቻለሁ ብለው ቀኖና ገብተው ይመለሱ በጀርባዎት የሌላ ኃሳብ ተሸክመው አያወናብዱን !?!?
( ኖላዊ ሆይ! ባይጠብቁ አያስክዱ!?!?)