Репост из: ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
ጳጳስ የሚወገዘው ምን ሲያደርግ ነው?
ጳጳስ አይከሰስ፣ አይወቀስ፣ አይወገዝ የኾነባት ቤተክርስቲያን ነው ያለችን። ሊቃውንቱ የዚኽ ሁሉ ሚዛን አስጠባቂ ነበሩ። ይሁን እንጂ የኑሮ እጣ ፈንታቸው በጳጳስ እጅ ኾነና በዝምታና በኀዘን ይተባበሯቸዋል። ትክክል አይደለም የሚል የለም።
ልጅ ወልደው አያት ሲኾኑ ጥፋታቸው በደብዳቤ ለዓለም ተገልጦ ሳለ የሚጠይቃቸው የለም። የገንዘብ ዘረፋ ዐይን አፍጥጦ ወጥቶ ሳለ ጠያቂ ያለባቸውም።
ረዥም ዓመት ባለኾነ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ :- “የጻፉት መጽሐፍ እንደ ካቶሊክ ኹለት ባሕርይ የሚል ነው” ብለው ብፁዕ አቡነ ገብርኤልን (የቀድሞው) “አባ ኢያሱ” ብለው ሲኖዶስ አውግዟቸው ነበር። ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስም ጋር ይከራከሩ ይጋጩ ስለ ነበር በኋላም ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋርም ተጣልተው ስለነበር ነገር ሠርተው አወገዟቸው።
ብፁዕነታቸው ይኽንን ክስተት ሲገልጹ :- “አቡነ ጎርጎርዮስ ግሪክም ሀገር ኾነዉ ስምተዉ ነበርና በተገናኘን ጊዜ በጣም ተከራከርን፡፡ የክርክራችን ማዕከልም ሞኖፌስት (Monophysis) የሚለዉ የግሪክ ቃል ትርጉሙ እና ሃይማኖታዊ ዳራዉ ነበር፡፡ ሞኖፌስት የእኛን ሃይማኖት ይገልጣል አይገልጥም በሚል እጅግ ተከራከርን፡፡ ይህም ክርክራችን ሰፍቶ እሰከ መጣላት አድርሶን ነበር፡፡ ….
ከዚያም በተለያዩ ጊዜያት ተገናኝተን እንወያይ ነበር:: በቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ በዶክትሪን፣ በአገላላጽ እንከራከር ነበር፡፡
በወቅቱ ከብፁዕ ወቅዱስ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋራ በአጋጣሚ ተጣልቼ ስለነበር በጻፍኩት መጽሐፍ ምክንያት ተከሰስኩኝ፡፡ “ይህቺ መጽሐፍ ውስጧ ኹለት ባሕርይ ነች፤ ስለዚህ አቡነ ገብርኤል ኹለት ባሕርይ የሚሉ ካቶሊክ ናቸው” በማለት፡፡
ከቤተ ክህነት ግቢ አስወጥተውኝ ስለነበረ ለጊዜው እቴጌ ጣይቱ ሆቴል ሳለሁ ግንቦት ወርእኔ በሌለሁበት መጽሐፏ ተኮነነች፡፡ “ይሄ ኦርቶዶክሳዊ አይደለም፤ ይሄ የቤተ ክርስቲያን አባባል አይደለም ይሄም የሁለት ባሕርይ ነው” እያሉ እያስጠኑ አሳመኗቸው፡፡ “እንዲህ ከኾነ መልስ ይስጥበት፤ አንድ ሰው ሲሳሳት ይጠራል፣ ይጠየቃል እምቢ ካለ ይወገዛል” ተባለና ወደእኔ አንዳንድ አባቶች መጥተው “ተዘጋጅተው ይምጡ” አሉኝ፡፡ ተዘጋጅቼ ስጠብቅ የእኔን መምጣት አከሸፉት፡፡ ብጥብጥ ይፈጠራል፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ናቸውና ሰዎች ይከተሏቸዋል በማለት ቅዱስነታቸውን አሳሳቷቸው፡፡ በሌለሁበት ውግዘት ተፈጸመብኝ፡፡
የ“እኛን አክሊል (ቆብ) እንዳያደርግ፣ ከምእመናን ጋራ እንዳይገናኝ ሳይጠየቅ ሳይናገር እንዳይባርክ፣ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገኝ˝ ብለው ውግዘት አስተላለፉ፡፡ ውሳኔያቸው ደረሰኝ፡፡ ተናደድኩ “ይህ ከኾነ ዘንድ እናንተ (Monophsis) ሞኖፌስቶች ናችሁ ከእናንተ ከአውጣኪያን ጋራ ግንኙነት የለኝም፧ ብዬ አወገዝኩኝ፡፡ የእልህ ውግዘት እብደት ማለት ነው፤ አወገዙኝ አወገዝኳቸው፡፡” በማለት በወቅቱ የነበረውን ክስተት ገልጸውታል። (የማውቀውን እናገራለሁ ገጽ 63-64)
የጠቡ ዋና ጉዳይ ቃል (Terminology) ነው እንጂ የይዘት አልነበረም።
በስተ መጨረሻ ግን በብዙ ውይይትና ንግግር በኋላ መንግሥቱ ኃይለ ማርያምም ጣልቃ ገብተው ጉዳዩ በውይይት ታየ፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤልም ይቅርታ ደብዳቤ አስገብተው ውግዘቱ ተነሣ አለቀ። (ዝኒ ከማሁ ገጽ 65)
ዛሬ በነገረ መለኮት ዙሪያ ቁጭ ብለው የሚወያይ ጳጳስ የለም። ተሰብስቦ ቁርጥ የሚበላ የሚያድም፣ በጎጥ ዩሚቧደን ብቻ ነው። ይኽንን የምለው ለማቃለል እንዳልሆነ ልቤን ያውቃል። ችግሩን በትክክል አይተን ለተጋድሎ እንድንዘጋጅ ነው። ቤተ ክርስቲያንን ከጳጳሳት ነጻ ለማውጣት እንጂ።
በቀኖና ቤተ ክርስቲያን በመማለጃ በጉልበት በተንኮል የተሾመ መማለጃ ተቀብሎ የሾመው ይሻር ይላል። "ኤጲስቆጶስነትን ፡ በማማለጃ ፡ በጉልበት ፡ በተንኰል ፡ ስለ ፡ ተሾመው ፡ ወይም ፡ማማለጃ ፡ ተቀብሎ ፡ ስለሾመው ፡ ነው።” ፍት. ነገ.5:173
“ከዓለማዊ ሥራ አንዳቸውን የሚሠራ ኤጲስ ቆጶስ ቢኖር ይሻር” ፍት.ነገ.5:198
የሃይማኖት ሕጸጽ የሚገኝበት ጳጳስ ቤተክርስቲያን ታወግዘዋለች። ለምእመኑ አርዓያ የማይሆን ጳጳስ ይሻራል።
በቀኖና ቢመዘን የሚተርፍ ጳጳስ የለም።
ዛሬ አይነኬ ሆነው ፓለቲከኞች የማይኾኑትን እየኾኑ። አመጻቸውንና ግፋቸውን በቀሚስና በቆብ ሸፍነው መጽሐፍ ቅዱስን የወንጀላቸው መሸፈኛ አድርገው ይኖራሉ።
አባ ሳህለ ማርያም “አቡነ” ገብርኤል የሚጠይቃቸው ሲኖዶስ የለም፣ “አባ ወልደ ትንሣኤን “ አቡነ” በርናባስን የሚጠይቅ የለም። አቡነ ሳዊሮስንና አቡነ ኤዎስጣቴዎስን፣ አቡነ ዜና ማርቆስንማ ቀና ብሎ የሚያይ የለም። ክቡራን ጠራርጎ ከማስወጣት ውጭ ምርጫ የለም። ቤተክርስቲያንን ለሉቃውንቱ ማስረከብ ላይ መሥራት ብቻ ነው።
ንዋይ ካሳሁን(ከፍኖተ አበው ገጽ)