Репост из: Health info & vaccancy news (HIVN)
ኖሮቫይረስ ተከሰተ
የፈረንጆቹ 2025 ከገባ ወዲህ፣ ኖሮቫይረስ፣ ወይንም 'ስቶማክ ፍሉ' በመባል የሚታወቀው፣ በመላው ዩናይትድ ስቴትስ እየተስፋፋ መሆኑን ሲዲሲ አስታውቋል። እንደ ሲዲሲ መግለጫ ትውከት እና ተቅማጥ የሚያስከትለው ይህ ተላላፊ ቫይረስ በብዙ ሰዎች ላይ በመከሰት በዚህ አመት ሪከርድ ይዟል።
የኖሮቫረስ ምልክቶች ማስታወክ፣ ተቅማጥ፣ የሆድ ቁርጠት፣ ማቅለሽለሽ የሚያስከትል ሲሆን አንዳንዴም ዝቅተኛ ደረጃ ትኩሳት ወይም ብርድ ብርድ ማለት፣ ራስ ምታት እና የጡንቻ ህመምን ሊያካትት እንደሚችል የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ:: ለቫይረሱ ከተጋለጡ ደግሞ ምልክቶቹ በሰውነት ላይ ከ 12 እስከ 48 ሰዓታት ሊታዩ ይችላሉ::
መከላከያው እጅን መታጠብ፣ የምግብ ንፅህናን መጠበቅ ፣ የምግብ ማዘጋጃና ሰዎች በጋራ ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ አካባቢዎችን በበረኪና ነክ ነገሮች ማፅዳትና በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ራስን ማራቅ መሆኑን ሲዲሲ ይመክራል::
ጥንቃቄ አይለየን!