Репост из: Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
የ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን ከተለያዩ መሪዎች ጋር በቁልፍ ቀጠናዊ፣ አኅጉራዊ እና የልማት ቀዳሚ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረግንበት ውጤታማ ቀን ነበር። ከኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ቴዮዶር ኦቢያንግ ንጉዬ ማምባሶንጎ፣ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ብሎም የቦትስዋና ፕሬዝዳንት ዱማ ቦኮ ጋር ትብብሮቻችንን በምናጠናክርባቸው መንገዶች ላይ ቁርጠኝነታችንን አረጋግጠናል። ከሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ እና ከታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉህ ሀሰን ጋርም የአፍሪካን እድገት ለማፋጠን የጋራ ጥረቶቻችንን ለማጠናከር ተወያይተናል።
ከመንግሥታትም ባሻገር ከግሎባል ፈንድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፒተር ሳንድስ እና ከጂኤቪአይ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳኒያ ኒሽታር ጋር የጤናውን ዘርፍ በማጠናከር ሥራ ላይ ተወያይተናል። ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንዊሚ አዲሴና እና አይኤፍኤዲ ፕሬዝዳንት አልቫሮ ላሪዮ ጋርም የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ የሚያጎለብቱ ጉዳዮችን አንስተን ተነጋግረናል። ከንግዱ ዘርፍም ከአሊኮ ዳንጎቴ እና ቶኒ ኢሉሜሉ ጋርም የግሉ ዘርፍ የአፍሪካን እድገት በመምራት ረገድ ስላለው ሚና ውይይት አድርገናል።
በነዚህ ውይይቶች ላይ በመመሥረትም የጋራ ብልፅግናን ለማሳካት እንሠራለን።