Репост из: Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ ስላደረጉልን የደመቀ አቀባበል አመሰግናለሁ:: ውይይታችን እንደ ሰላም እና ፀጥታ፣ ኢኮኖሚ፣ ዲፕሎማሲ እና በጋራ ልንገነባቸው ስለምንችላቸው የመሠረተ ልማት ሥራዎች ያሉ ቁልፍ ጉዳዮችን የተመለከተ ነበር።
የአፍሪካ ቀንድ በሀብት የበለፀገ ነው። ለም ምድር፣ የተፈጥሮ ውሃ እና የሰው ኃይል ሀብቶች አሉት። ይሁንና ራሳችንን ለመመገብ ስንቸገር ይስተዋላል። ቀጠናዊ ትስስር የጋራ ህልማችንን እውን ለማድረግ እጅግ ጠቃሚ ነው።
ለጋራ እድገታችን ልንጠቀምበት የምንችል ትልቅ አቅም አለን። በተናጠል ማደግ አንችልም። በጋራ ስንቆም ጠንካራ ነገ እና ብሩህ ተስፋ ይኖረናል። ቀጠናዊ ትብብር ቁልፍ ነው። ይኽን እውን ለማድረግ ከሶማሊያ ጋር ለመስራት ዝግጁ ነን።