የእግር ኳስ ሁለት ገፅታ
ዳርዊን ኑኔዝ በቀደሙ የቪላ ጨዋታ ኳስ ከሳተ በኋላ በርካታ ዘለፋዎችና ማንጓጠጦች ደርሰውበታል.....ግን ዳርዊን ከሳምንታት በፊት ሊቨርፑል ተቸግሮ የሚያደርገውን ባላወቀበት ሰዓት ተቀይሮ ገብቶ ባለቀ ሰዓት ብሬንትፎርድ ላይ 2 ግቦችን አስቆጥሮ ውድ 3 ነጥብን ለቡድኑ አስገኝቶ ነበር።
ነገሩ የዳርዊን ብቻ አይደለም....ያለ ፔፕ ጋርዲዮላ ምንም የሆነው ማንችስተር ሲቲ እየተፈተነ ባለበት ወቅት በሜዳው ነጥብ ሲጥል ደጋፊዎች ሲጮኹበት ነበር....እሱም ትክክል ናቸው ደጋፊ ዛሬ ምን ሰራህ እንጂ ትናንት ስለሰራከው አያገባውም ብሎ ነበር።
ሉክማን በአታላንታ እያጋጠመው ያለው ኦሲሜህን በናፖሊ ቤት ያጋጠመውን ብዙ ተመልክተናል፤ታዝበናል።
በፕሪሚየር ሊጉ ብቸኛውን ያልተሸነፈ ቡድን የገነቡት አርሰን ቬንገር እንኳን በደጋፊዎቻቸው አንፈልግህም 'Wenger out' ተብለዋል።
በጣም ብዙ ብዙ መጥቀስ ይቻላል.....
የእግር ኳስ አንዱ ገፅታ ይህ ነው....ትናንት ያደረከው እና ያሳካከው ነገር በትንሽ እድፍ ይጠለሻል።
SHARE |
@Premier_League_Sport