#ቀን_ሲጥል
ድርቅ ብዬ ቀረው አንዲት መልከመልካም ሴት ከፊቴ ቆማለች ሌላ ማንም የሰው ዘር አይታየኝም አቢጊያ ወደ እኔ መጥታ ስላም ነው። ናኦድ አለችኝ ደንዝዤ ቀረው እጄ ይንቀጠቀጥ ጀመር አቢጊያ ህመሙ መስሏት ደነገጠች ወደ ሰመሀል ዞራ ሰሙ እየተንቀጠቀጠ እኮ ነው እያመመው ነው መሰለኝ አለቻት ሰመሃል ፈጠን ብላ ወደ እኔ መጥታ ምነው ናኦድ ደህና አይደለህም እንዴ አለችኝ ቲንሽ ሰመሃልን ሳይ ተረጋጋው ደ..ደና ነኝ አልኩዋት እራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ ቁና ቁና እየተነፈስኩ ስላም ነው አልኩዋት አቢጊያ ፈገግ እያለች ደህና ነኝ እንዴት ነህ አንተ እየተሸለህ ነው አለችኝ።
እኔ ማመን አልቻልኩም በ ህልሜ በ ህልሜ ነው በውኔ? ምንም ይሁን ምን ከእዚ ህልም መንቃት አልፈለኩም ደህና ነኝ አልኩዋት ዝም አለች እሱዋም ዝም አለች ዝምታው ሲበዛ ኪያር ወንበር
ወደእሱዋ አስጠጋላት ተቀመጭ አላት እሱዋም ወንበሩን ስባ ከአጠገቤ ተቀመጠች ኪያር ከሁዋላዋ ሆኖ ፈገግ እያለ ጠቀሰኝና ሰሙ ነይ ዶክተሩዋን እናናግራት እና እንምጣ ብሎዋት ይዙዋት ሄደ።
ክፍሉ ውስጥ እኔ እና አቢጊያ ብቻ ቀረን ልቤ በጣም ይመታል አይደለም አጠገቤ ሆና ከርቀት ሳያት የምበረግገው አሁን በቅርበት ሆና እያየችኝ ነው ህመሙ ሆኖብኝ ነው እንጂ ጥያት ብሮጥ ምነኛ ደስ ባለኝ ዝም ብዬ በ ሃሳብ መብሰልሰል ቀጠልኩ ዝምታውን ለመስበር ይመስል ወደእኔ ቀና ብላ እያየች ሰመሃል ጥሩ የክላሴ ልጅ ናት ትናት ማታ አግኝታኝ ሁሉንም ነገር ስትነግረኝ ምን… በድነጋጤ አውርታ ሳትጨረስ ነገረችሽ ብዬ ጮክ ብዬ ጠየኩዋት ልቤ ከአፌ ልትወጣ ቲነሽ ቀራት አቢጊያ ደንገጥ እያለች አውው…በጣም ያሳዝናል ህግ ባለበት ሃገር እንደዚ ሲደረግ ያሳዝናል አግባብ አይደለም ምን አይነት ሰውስ ቢሆን ነው እነደዚ አይነት ጨካኝ የሚሆነው ዘመኑ ከፍቱዋል አለችኝ። እፎይ…ይ ተመስገን አልነገረቻተም አልኩ በልቤ ዝም ስል ምነው ዝም አልክ አለችኝ አ..አይ ዝም አላልኩም ቲንሽ ሰው ማናገር ስለሚከብደኝ ነው አልኩዋት እየሳቀች ታፍራለህ እንዴ ስትለኝ ተሽኮረመምኩ ይበለጥ ሳቀች ስትስቅ ደስ ትላለች ጥርሶቹዋ የተፈለቀቀ ጥጥ ነው።
የሚመስሉት ፈጣሪ ጥርሶቹዋን ተጠንቅቆ የደረደራቸው ማራኪ ተፈጥሮ ናቸው በእዚ ቅርበት አይቻት ስለማላውቅ ፍቅሯ በውስጤ ሲጨምር እሱዋነቷ ውበቷ እኔነቴን ሙሉ ለሙሉ ሲቆጣጠረኝ ተሰማኝ ሽቶዋ ደስ የሚል መአዛ አለው በግድ አፍንጫዬን ከፍቶ ልግባ ይላል በቃ ሞኝ ሆንኩ እራሴን መቆጣጠር አቃተኝ በደስታ ይሁን በሃዘን ስሜት አላውቅም ማልቀስ ጀመርኩ ውስጤ ባይፈለገውም መቆጣጠር አልቻልኩም ምነው አለችኝ ድንገት ያለፉትን ሁለት አመታት እንዴት እንዴት ሆኝ እንዳሳለፍኩዋቸው አይኔ ላይ ውል አለ ይበልጥ ተከፋው ኤቢ ከእዚ በላይ አፍኜው መቆየት አልችልም ይበቃኛል ልፈነዳ ነው እኔ ባነቺ ምክንያት ብዙ ተሰቃየው እኔ ካየውሽ ቀን ጀምሮ በጣም ነው የወደድኩሽ አምና መስከረም 24 ቀን እናተ ፍሬሽ ሆናችው ወደ ግቢ ስትመጡ ሻንጣሽን እየጎተትሽ ስትገቢ እኔ ደሞ ስወጣ ነበር ያየውሽ እኔ በቃ አልችለም ከእዚ በላይ በፍቅር መቀጣት አልችልም አልችልም አልችልም ባንቺ ምክንያት ትምህርቴን ተውኩ ጎብዝ ተማሪ ነበርኩ ያውም የባቻችን ሰቃይ አሁን ግን ጀዝባ ነኝ ሞሮ…ጉዋደኞቼ ሸሹኝ ሁሉም እራቁኝ አንቺን እንደምውድሽ ግቢው በሙሉ ያውቃል
አንቺ ግን አይደለም እንደምውድሽ ቀርቶ ምን አይነት ስው እንደሆንኩ እራሱ አታውቂም…በቃ በቃ በቃ ብላ ተቆጣች እኔም መነፋረቄን ለጊዜም ቢሆን
ገታውት ደነገጥኩ እኔ ሙትልኝ ውደደኝ ጀዝባ ሁንልኝ ብዬሃለው እንዴ ምን አይነት ወሬ ነው የምታወራው በእራሰህ ስንፍና እኔን ጥፋተኛ ታረጋኛለህ እንዴ እኔ እና አንተ እኮ አንመጣጠንም ለመሆኑ እራስህን አይተውሃል አለችኝ ቅፍፍ እያልኩዋት ፍቅር ምናምን የሚባለው እንቶ ፈንቶ አይገባኝም እሺ ሃ..ሃ ሃ.ሃ…ሃ ይውጣልህ ብላኝ የምጸት ሳቅ እየሳቀች ከተቀመጠችበት እየተገላመጠች ተነሳች።
እያመመኝ እየንተጠራራው እጇን ያዝኳት አቢጊያ እባክሽ አትሂጂ ስላት
እጀዋን መንጭቃ ሄደች ልከተላት ከአልጋው ላይ እየንተጠራራው ስነሳ ከአልጋው ላይ ወደኩ ይበልጥ አመመኝ ወደኋላ ዞር ብላ አየችኝና ወጣች አቢጊያ እንደዚ አይነት መልስ ትሰጠኛለች ብዬ ነበር እሺ ልትል እንደማትችል ገምቼ ነበር ግን እንደዚ ውጪ ከሰመሃል ጋር ተገጣጠሙ መሰለኝ ወዴት ነው ስትላት ሰማሁኝ አቢጊያ በጣም እየበሸቀች ለእዚ ነው የጠራሽኝ ዘመዴ ነው ምናምን ብለሽ ከዚ ጀዝባ ጋር ልታጣብሺኝ ነበር ያመጣሽኝ በጣም ነው የማዝነው ብላ ስትሄድ የጫማዋ ዳና ተሰማኝ ኪያር ወደ ክፍሉ ሲገባ መሬት ላይ ወድቄ ደም እንባ እያለቀስኩ ነበር ደንግጦ ናዲ…ምነው ብሎ ቀና አደረገኝ ሰመሃልም ስትገባ አየችኝ ጩኀቷን አቀለጠችው ወለሉ በደም እየራሰ ነበር
ይቀጥላል...
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot