#ቀን_ሲጥል
ሰምሃል ለእኔ ብላ ኤቤጊያን አንድ ወር ሙሉ ማኩረፏ አስገረመኝ ተገረምኩባት ስብእናዋ ያስደንቃል አንድ ወር እንኲን በቅጡ ለማታውቀው ሰው ብላ ለአመታት የምታውቃትን ጓደኛዋን አኮረፈች ይገርማል። ብዙ ከጨቀጨቅኳት በኃላ እንዲታረቁ አስማማኃት ሲቀጥል እኔ ኤቤጊያን አልተቀየምኳትም የተናገረችው ነገር ደባሪ ሊሆን ይችላል ግን አሁንም ድረስ ወዳታለው የዛኔ የኔም ጥፋት ነበረበት መታመሜን ልትጠይቅ የመጣችን ሴት ዘልዬ አፈቅርሻለው ምናምን ማለት አልነበረብኝም እንደውም ጥፋተኛው እኔ ነኝ አልኳት።
እያወራን እያለ አባዬ ከቤተክርስቲያን ተመልሶ ነጠላውን አጣፍቶ ወደቤት ገባ አራቱም ደንገጥ ብለው አባዬን ሰላም ሊሉት ከመቀመጫቸው ብድግ አሉ እኔ ደሞ ሁኔታቸውን አይቼ ፈገግ አልኩ እነሰሙ በደምብ ስለማያውቁት ነው ከሁሉም ያሳቀኝ የኪያር ነበር ቤቴ ሁሌ ሲመጣ ኖሮ ዛሬ እንዳዲስ መደንገት ሃ..ሃ..ሃ... አይ ኪያር።
አባዬ ገና ሰምሃልም ሲያያት ነበር ደስ ያለው እንዴ መጣችው እንዴ ጠፍታችው ቆያችው ምነው አላቸው ወደ ሰምሃል እያየ እሷም አፈር እያለች አይ የፈተና ሰሞን ስለነበረ ትንሽ ተጨናንቀን ስለነበር ነው ጋሼ አለችው። አይ ደግ ይሁን በቃ በደምብ ተጫወቱ እንደቤታችው ቁጠሩትቁጠሩት ብሏቸው ወደላይ ሄደ ቤተሰቦቼ ሰምሃልን በጣም ነው የሚወዷት ስለሷ ብዙም ባያውቁም እኔ ያደረገችልኝን ሁሉ ነግሪያቸው በጣም ወደዋታል በተለይ አባዬ። እኛም ጨዋታችንን ቀጠልን በመሃል እያወራን ዛሬ ከናንተ ጋር ወደ ግቢ ለምመጣት አስቢያለው አልኳቸው ደስ አላቸው ግን ችግሩ አባዬ እሚፈቅድልኝ አይመስለኝም እሱን ለማሳመን የተቻለኝን አደርጋለው እናንተም ታግዙኛላችው እሺ አልኳቸው ተስማሙ ግን ኪያር ቅር ያለው ይመስላል ምክንያቱም ለምን ለማን ብዬ ናዝሬት እንደምመለስ ያውቃል ድጋሚ ኤቤጊያን ለማግኘት እንደሆነ ያውቃል እየደበረው እሺ አለኝ።
ሁላችንም ምሳ ከበላ በኃላ ሁሉም ባሉበት ስፈራ ስቸር አባቴን ግቢ ደርሼ መምጣት እንደምፈልግ ነገርኩት ወዲያውኑ የቲቪውን ሪሞት ከጠረጵዛው ላይ አንስቶ ድምፁን እየቀነሰ ኮስተር ብሎ ምን? አለኝ ድምፁ ይበልጥ አስፈራኝ። አይ አባዬ አሁን ተሽሎኝ የለ ደህና ነኝ እኮ ግቢ ዛሬ ደርሼ መምጣት ፈል.... አባዬ እስክጨርስ አልጠበቀኝም ቆጣ ብሎ አይቻልም! ብሎ ቀጭን ትእዛዝ አስተላለፈ። ኪያር ጋሽ ምሽጉ እኛ ስላለን እኮ ችግር የለውም እንጠብቀዋለን ምንም አይሆንም አለ አባዬ ግን በሃሳቡ ፀና አይሆንም የሆነ ነገር ቢሆን ፀፀቱን አልችለውም ብቸኛ ወንድ ልጄ ነው አለው።
ዝምታ ሰፈነ ሁሉም ከተረጋጋ በኃላ ሰምሃል ወደ አባቴ እያየች ጋሼ እኔም በእርሶ ሃሳብ እስማማለው ናኦድ ህመም ላይ ነው ነገር ግን ደግሞ ብዙ አመት የለፋበት ትምህርት አለ ያንን ትምህርት እንዲው እንደቀልድ መተው ለእርሶም ለናኦድም የህሊና እረፍት አይሰጥም ናኦድ በጣም ጎበዝ ተማሪ እንደሆነ አውቃለው በዚ አመት ዊዝድሮው ፎርም ካልሞላ ቀጣይ አመት መመለስ አይችልም ይባረረል ዩኒቨርስቲው የሚያውቀው አሁንም በትምህርት ላይ እንደሆነ እንጂ በህመም ምክንያት አቋርጦ እንደሄደ አያውቅም ስለዚህ ድጋሚ ተመልሶ ያለውን ሁኔታ ገልፃ ዊዝድሮው ሞልቶ መመለስ አለበት እኔም ባይሄድ ደስ ይለኝ ነበር ግን ፋይናል ፈተና ሳይጀመር ዊዝድሮው መሙላት አለበት አለችው። አባዬ በትምህርት ምንም አይነት ድርድር ስለማያውቅ ሊቃወምበት የሚችለው ምክንያት አልነበረውም።
ይቀጥላል.....
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot