#ቀን_ሲጥል
ሰምሃል ሊዲያና ራኬብ እየተሳሳቁ ልክ ወደ ዶርም ሲገቡ ኤቤጊያ ወደውጪ ለመውጣት እየተኳኳለች ነበር ሰምሃል ሳቋን በአንዴ አቆመችና ቦርሳዋን አልጋዋ ላይ አስቀመጠችና ወደ ሎከሯ ሄደች ራኬብና ሊድያ ደክሟቸው ስለነበር ሃደው አልጋቸው ላይ ተዘረገፉ ኤቤጊያ መኳኳሏን አቁማ ወደ ሰምሃል እየተጠጋች አረ... ሰሙዬ አሁንም እንዳኮረፍሽኝ ነው ወር ሞላኝ እኮ ካኮረፍሽኝ ያጨዋታሽና ሳቅሽ ናፈቀኝ እባክሽ ይቅር በይኝ በቃ አለቻት ሰምሃል ምንም መልስ ሳትሰጣት አድርጋቸው የነበሩትን ጉትቻ የጆሮ ጌጦች እያወለቀች ሎከሯ ውስጥ ስርአት ባለው መልኩ ታስቀምጣለች።
ኤቤጊያ የሰምሃል ዝምታ ሲበዛባት ጮክ እያለች እሺ ቆይ ምን እንድልሽ ነው ምትፈልጊው ከዚ በላይ መቶ ግዜ እኮነው ይቅርታ ያልኩሽ የምር ሰሙዬ ሁለተኛ አይለመደኝም የእውነት አንቺ የፈለግሺውን ነገር ቅጪኝ እና ልገላገል እኔ ዝምታሽ ሊበላኝ ነው አለቻት ሰምሃል እንደመበሳጨት እያለች የሎከሩን በር አጋጭታ ዘግታው ወደኤቤጊያ ዞረች እኔ አንቺን የመቅጣት ፍላጎት የለኝም የዛን ቀን ርክክለኛ ማንነትሽን ነው ያሳየሽኝ በጣም ነው ያዘንኩብሽ እንደዛ አይመት የቀሸመ ስብእና ይኖርሻል ብዬ አላስብም ነበር እኔ ባንቺ አዘንኩብሽ እንጂ አልተቀከምኩሽም ያስቀየምሽው እኔን ሳይሆን ናኦድን ነው አሁን ውጪ ሊያገኝሽ እየጠበቀሽ ነው ጥሪልኝ ብሎኛል ሄደሽ አናግሪው የእውነት ያደረግሽው ነገር ከፀፀተሽ ይቅርታ በይው ይቅርታ ሳትጠይቂው ብትመለሽ እኔን አያድርገኝ ብላ ጮኀችባት።
ሊዲያ እና ራኬብ የሁለቱን ጭቅጭቅ ድምፃቸውን አጥፍተው ከመስማት ውጪ ምንም ትንፍሽ አይሉም። ኤቤጊያ እያቅማማች እህህህ አሁን እኮ ከራስታው ጋር ልንወጣ ተቀጣጥረናል እንዴት ብዬ ነው ሞሮ ጋር እምሄደው አለቻት ተሳስታ ሞሮ እንዳለችው ስራውቅ በጣም ደነገጠች ሰምሃል ይበልጥ ፊቷ ሲቀላ ታወቃት እዛው በቆመችበት ደነፋች የምርሽን ነው!!! አንቺ እሚያስጨንቅሽ ከእንድ ሰው ጋር ስለመውጣት ነው ያስቀየምሽው ሰው ያስለቀስሺው ሰው አይታይሽም አለቻት ኤቤጊያ በአፍረት አንገቷን አቀረቀረች መልሽልኛ ብላ ጮኀችባት መሄድ ትችያለሽ አልከለክልሽም ግን ዳግም ጓደኛዬ ብለሽ አጠገቤ እንዳትደርሽ አለቻት ኤቤጊያ ደነገጠች እሺ በቃ እሄዳለው የቱ ጋር ነው ያለው አለቻት ሰምሃል ተናዳ ስለነበር እነሱን ጠይቂያቸው ብላ ወደነራኬብ ጠቁማት አልጋዋ ውስጥ ተጠቅላላ ገባች ራኬብ በመስኮት ናኦድ የቆመበትን ቦታ አሳየቻት እሺ ያው እየሄድኩ ነው ሰሙ በድጋሚ ይቅርታ ሁሉንም ነገር አስተካክለዋለው ብላት በፍጥነት ከዶርሙ ወጣች።
ይቀጥላል.....
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot