ሩሲያ በግዛቷ ላይ የአሜሪካ ሚሳኤል ጥቅም ላይ ከዋለ እርምጃ እወስዳለሁ ስትል ዛተች
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ ዩክሬን የአሜሪካንን ሚሳኤሎች ተጠቅማ ሩሲያ ምድር ላይ ጥቃት መሰንዘሯ ተጨባጭ እና ተገቢ ምላሽን ያስከትላል ብሏል።
ሚኒስቴሩ በመግለጫው፤ እንዲህ አይነት ጥቃቶች በሩሲያ ምድር የሚሰነዘሩ ከሆነ አሜሪካ እና አጋሮቿ በቀጥታ ከሩሲያ ጋር ግጭት ውስጥ የሚያስገባቸው ነው ሲልም አስጠንቅቋል።
ከሰሞኑ ተሰናባቹ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሀገራቸው ለዩክሬን የለገሰቻቸው ረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤሎች ሩሲያ ውስጥ ጥቃቶችን ለመሰንዘር ጥቅም ላይ እንዲውሉ ፈቅደዋል።
ይህን ተከትሎም በሁለቱ ሀገራት መካከል ውጥረት እንዲነግስና ትልቅ የፖሊሲ ለውጥ እንዲከሰት አስችሏል ተብሏል።
የአሜሪካው ውሳኔ የተሰማው ከአስር ሺህ በላይ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ከሩሲያ ሀይሎች ጎን ሆነው ለመፋለም ኩርስክ ግዛት መድረሳቸው ከተሰማ በኋላ ነው።
ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሩስያ እና የዩክሬን ጦርነት እንደሚያስቆሙ ቃል በመግባታቸው በዚህ ውሳኔ ላይ ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር መማከራቸው ግልፅ አለመሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
ትክክለኛውን የሪፖርተር የቴሌግራም ቻናላችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ✅
📢🔴https://t.me/ReporterET