ንጉሱ ሚኒሊክና ጨዋዉ የኢትዮጵያ ህዝብም ይሄን ሰማ፤ ጣልያንም ቅድሚያም ያስዋሸዉ ሰይጣን አሁን ደሞ አደፋፈረዉና ማትደፈረዋን የባለግርማዋን ኢትዮጵያን ባለግርማዎቹን ህዝቦች ታላቆቹን ህዝቦች ጨዋዎቹን ሰዉ ወዳጆቹን አባቶቻችን ሊወጉ ተነሱ።
እንዴት ! እኮ ኢትዮጵያ ልትደፈር ! ያለ ይህ ታላቅ ሀገሩን እና ንጉሱን አክባሪ ህዝብ በክብር እና በፍቅር እንግዳ መቀበል እንጂ ወራሪ መቀበል ማያቅ ህዝብ ክተቱን በደስታ ሰማ ከተተለት፤ ወዮ ለጣልያን።
ከቤቱ ሲወጣ ታንክ አልነበረዉም ወይም ዘመናዊ መሳርያ አልነበረዉም ወኔ ግን ነበረዉ ንጉሡ እቀየምሀለዉ ብሎታል በእናቱ ማርያም ምሏልኮ እንዴት ይቀራል በርግጥ መኪና የለም ምናልባትም ከደቡብ አድዋ ድረስ መሄድኮ አልችልም ማለት ይችል ነበርኮ ከቤንሻንጉል አድዋ እንዴት ይኬዳል ማለትም ይችል ነበር እኔ የጦር ልምድ የለኝም ማለትም ይችል ነበር ግን ሀገር ናታ ምትደፈረዉ በአንዴ እናት, ልጅ, ሚስት, ዘዉድ ሲደፈር ምን ምክንያት ያስፈልጋል ይከተታል እንጂ አንድም ወደ ጦር አንድም ወደ ጠላት ሆድ ሳንጃ።
እናማ ይሄ ታላቅ ህዝብ ማነዉ አትሉም የኔና የእናንተ አያት በእዉነት የኛ አያት ታሪክ ነዉ ዘርህን/ሽን ብትቆጥር/ሪ በዚ ጦርነት ደሙ የፈሰሰ በእርምጃ እግሩ የዛለ በጠላት ደም ጎራዴዉ የራሰ አያት አለህ አለሽ አለን።
እና እንኳን አደረሰን ለአያቶቻችን ቀን፣ እንኳን አደረሰን ለሰዉ ልጅ እኩልነት ቀን፣ ለአለም የጥቁር ህዝብ የነፃነት ቀን ለድምቀት ቀናችን እንኳን አደረሰን አደረሳቹ።
ዛሬ አንገታችንን ቀና ያረግነዉ ያንተ ያንቺ የኛ አያቶች ባፈሰሱት ደም ነዉኮ፤ የሞቀ የሞላ ቤት ጎጆዋቸውን ትተው ለወጡት ለአያቶቻችን ቀን እንኳን አደረሰን።
እንግዲ እኛስ ለልጅ ልጆቻችን ምንድነዉ የምንጠዉ እሱስ ከመቶ አመት ቡሀላ ስለዚ ትዉልድ ሲያወራ ምን ያዉራ ?
ዛሬ አድዋ ነዉ እኛ ደሞ ኢትዮጵያ ክተቱ ልጆቼ ከሰዉ ሁአላ ቀረዉ ያለመድኩት ልመና የሰዉ እጅ ማየት መጣብኝ ክተቱልኝ ትለናለችና እንክተት ፀሀፊ ብዕሩን ይዞ፣ ሙዚቀኛ ማይኩን ይዞ፣ ነጋዴ ብሩን ይዞ፣ ባለስልጣን በቅንነት ለማገልገል ይክተት። ብቻ ሀገር ክተቱ ትለናለችና በየተማራንበት ሁላችንም ለሰላሟ እና ለእድገቷ እንክተት።
ምንጭ @ETHIO_PDF_BOOKS
አድዋ የኔ ነዉ።
አድዋ ለኔ ነዉ።
#አድዋ
#ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ
#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ
@RvcClub