ሌላ ልዩ ምዕራፍ!
ነቀምቴ እና አዋሳኝ ከተሞችን በፈጣኑ እና አስተማማኙ 4G ኔትወርካችን የ07 ሳፋሪኮም ቤተሰብ አድርገናል። ይህ የኔትወርክ ማስፋፊያችን ወደ ምዕራብ ኢትዮጵያ ለምናደርገው የአገልግሎት ማስፋፊያ እና መላውን ኢትዮጵያ ከዳር እስከ ዳር የማዳረስ ሕልማችን ቁልፍ ሚና ይኖረዋል።
በነቀምቴ ከተማ እና ዙርያ የምናቀርበው አገልግሎት በ32 ዘመናዊ የኔትወርክ ማማዎች እና ፋይበር መሰረተ ልማት የሚደገፍ፤ በተጨማሪም 250 የሥራ ዕድሎችን በ5 የሽያጭ ወኪሎች በኩል የሚፈጥር እንዲሁም ቢዝነሶችን እና ደንበኞቻችንን በM-PESA የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት አቅርቦት የሚያገለግል ነው።
ከኔትዎርክ ማስፋፊያ ሥራዎቻችን በተጨማሪም የትምህርት ዘርፉን በዲጂታል ለማገዝ ዋጋው አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመት ላፕቶፖች እና ራውተሮችን ከ6 ወራት ገደብ አልባ ዳታ ጋር በነቀምቴ ከተማ ለሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አበርክተናል።
ለምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደር፣ ለነቀምቴ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም ሥራችን እንዲሳካ አስተዋጽኦ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን።
ዳር እስከዳር በተግባር!